Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወንድሜ ሆይ አትሸወድ... ፂምህን አሳድገው!!


ወንድሜ ሆይ አትሸወድ... ፂምህን አሳድገው!!
አደራህን ፂም ማሳደግ ኃላ ቀርነት አለያም አክራሪነት እንዳይመስልህ። አትጠራጠር!! ፂም የነብያት ፈለግ ኢስላማዊ መገለጫም ነው። ሁሉም ነብያት ፂም እንደነበራቸው አትጠራጠር። የምትወዳቸውና አርአያ ያደረካቸው መልእክተኛ ፂም ነበራቸው። የመልእክተኛውን አካላዊ ሁኔታ በሚገልፁ ብዙ ሀዲሶች የመልእክተኛው ፂም (ብዙና ጥቅጥቅ ያለ) እንደነበር ይገልፃሉ።
የሰሀቦችን አካላዊ ገፅታ የገለፁ ዘገባዎችም ይህንኑ ያመለክታሉ። ከሰለፎችም ይሁን ኃላ ከመጡ ትውልዶች አርአያ የምናደርጋቸው ኡለሞቻችን ሁሉ ፂማቸውን ያሳድጉ ነበር። ኢስላማዊ ታሪካንም ከሰለፎችም ይሁን ከታላላቅ ስብዕናዎች አንድም ፂሙን የላጨ ዓሊም ወይም አርአያ ሰው አይጠቅስም።
ዋጂብ ነው ሱና??? ብለህ ትጠይቅ ይሆናል። እሱ አያሳስብህ ወንድሜ... ዋጂብም ሆነ ሱና...
ተወዳጁን መልእክተኛ፣ ሰሀቦችን፣ ታቢዒዮችን፣ ሷሊህ የሆኑት ሰለፎችን... መምሰል ሊያኮራህ ይገባል።
ፂም ማሳደግ፤ ኢስላምን ማንፀባረቅ፣ ለመልእክተኛው ታዛዥነትን ማሳየትና በኢስላማዊ ማንነት መኩራትም ነው። በተለያዩ ሀዲሶች የመጡ ነብያዊ ክልከላዎች ሁሉ ፂም ባለበት ሊተው እንደሚገባ ማሳጠሩም የተከለከለ መሆኑን ብሎም የሙሽሪኮች መገለጫ በመሆኑ መመሳሰል እንደማይገባን ያስገነዝባሉ።
☞ ከአብዱላህ ኢብኑ ዑመር በተላለፈ ሀዲስ "ወፊሩ" [አብዙት]² በሚል አገላለፅ ታዘናል፦
((وفروا اللحى وأحفوا الشوارب)) رواه البخاري
«ፂማችሁን አብዙት፤ ከላይኛው ከንፈር ላይ የሚያድገውን ፀጉር ደግሞ ቀንሱት።» ቡኻሪ ዘግበውታል
☞ እንደዚሁ አል ኢማም ሙስሊም ከአብዱላህ ኢብኑ ዑመር በዘገቡት ሌላ ሀዲስ "አውፉ" [ሙሉ አድርጉት]³ በሚል ቃል ታዘናል፦
((أحفوا الشوارب وأوفوا اللحى)) رواه مسلم
«ፂማችሁን ሙሉ አድርጉት፤ ከላይኛው ከንፈር ላይ የሚያድገውን ፀጉር ደግሞ ቀንሱት።» ሙስሊም ዘግበውታል
☞ ከአቡ ሁረይራ በተዘገበ ሀዲስ "አርኹ" እና "አርጁ" በሚሉ ቃላት ታዘናል። [አስረዝሙት]⁴ የሚል መልእክት አላቸው።
((جزوا الشوارب وأرخوا اللحى)) رواه مسلم، وجاء بلفظ (أرجوا) بالجيم
«ከላይኛው ከንፈር ላይ የሚያድገውን ፀጉር ቀንሱት። ፂማችሁን አስረዝሙት” ሙስሊም ዘግበውታል
☞ በሌላ ከአብዱላህ ኢብኑ ዑመር በተላለፈ ሀዲስ ደፍሞ "አዕፉ" ፂማችሁን [እንዳለ ተዉት] በሚል ቃል ፂምን ከመቀነስ ተከልክለናል። (ታጁል ዐሩስ እና ሌሎችንም መዝገበ ቃላት ይመልከቱ)
((أنهكوا الشوارب وأعفوا اللحى)) رواه البخاري ومسلم بلفظ (أحفوا الشوارب)
«ፂማችሁን እንዳለ ተዉት፤ ከላይኛው ከንፈር ላይ የሚያድገውን ፀጉር ቀንሱት።» ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል
ከላይ እንደተመለከትነው በሁሉም ሀዲሶች እና የተጠቀሱት የትእዛዝና የክልከላ ቃላት ፂምን ማሳደግን፣ እንዳለ መተዉን እና ማብዛትን ያዛሉ። ፂምን መመናመን፣ መቀነስና መላጨትን ይከለክላሉ።
ከነዚህና መሰል መረጃዎች በመነሳት የኢስላም ሊቃውንትና የፊቅህ ጠበብቶች ሁሉ ፂም መላጨት ሀራም ስለመሆኑ ተስማምተዋል። የአራቱም መዝሐቦች የፊቅህ ድርሳናት ሁሉ ፂም መላጨትን ይከለክላሉ።
አደራህን እንዳትሸወድ!!
© ተንቢሀት