=====================================
አምልኮ በጠቅላላ የሚገባው ለነብያትም ተዓምራቱን የሰጠው፣ ለወልዬች ከራማውን ለለገሰው የሁሉ ባለቤት ሸሪካ የሌለው አላህ ብቻና ብቻ ነው፡፡
መልክተኞች የተለያየ ታዓምርን በአላህ ፍቃድ ይፈፅማሉ፡፡ ለምሳሌ ነብየላህ ኢሳ (አለይሂ ሰላም) ለምጣምን ማዳኑ፣ የሞተን መቀስቀሱ ይህ ሁሉም በአላህ ፍቃድ ብቻና ብቻ ነው የተከሰተው፡፡ ነብየላህ ሙሳም (አለይሂ ሰላም) ብትራቸው በአላህ ፍቃድ ታዓምር ማሳያ ሆናቸው፡፡ ነብዩ ሙሐመድም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከአላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ይህን ዘመን የማያልፍበት ተዓምር ቁርዓን (ፉርቃን) አወረደላቸው፣ ከእጃቸው ውሃ እንዲፈስ አደረገ፣ ጨረቃ እንድትከፈልላቸው አደረገ እና ሌላም ሌላም፡፡
ከዚህ
የምንወስደው ታላቅ ትምህርት አለ፡፡ ነብያት በአላህ ፍቃድ እንጂ በራሳቸው ምንም ማድረግ እንደማይችሉ፡፡ ከነብያት
ጋር ጭራሽ ሊወዳደር የማይችል አላህ ለወልዬች የሰጠው ከራማ አለ፡፡ የአላህ ወልዬች ማን እንደሆኑ ደግሞ
የሚያውቃቸው አላህ ብቻ ነው፡፡ ነብያት ይህን ሁሉ ተዓምራት ከአላህ የተሰጣቸውን በእጃቸው ይዘው ምንም አይነት
አምልኮ ለነሱ አይገባቸውም፡፡ ታድያ አንዳንዶች ዘንድ ከራማ አለው ተብሎ ሰዎች በመገመታቸው ብቻ የአላህን መብት
አሳልፈው ሲሰጧቸውና አምልኮን ሲፈፅሙላቸው ይታያል፡፡ ይሄ ታላቁ በደል ሸርክ ነው፡፡ አምልኮ በጠቅላላ የሚገባው
ለነብያትም ተዓምራቱን የሰጠው፣ ለወልዬች ከራማውን ለለገሰው የሁሉ ባለቤት ሸሪካ የሌለው አላህ ብቻና ብቻ ነው፡፡
ሌላው ለአንዱ መልክተኛ የተሰጠውና የተመረጠለት ታዐምር ለሌላው መልክተኛ ላይሰጥ ይችላል፡፡ አላህ ለእያንዳንዱ መልክተኛ የመረጠለትን ተዓምር ይለግሰዋል፡፡ ለመልክተኞች ከተሰጡ ተዓምሮች ሁሉ በላጭ አላህ ለነብያት ሁሉ መደምደሚያ ሙሐመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያወረደው ቁርዓን ነው፡፡
አላህ የመልክተኞች ተዓምር ከእርሱ የተሰጠ መሆኑን እንዲህ ሲል ይነግረናል
وَلَقَدْ أَرْسَلْنَا رُسُلًا مِّن قَبْلِكَ وَجَعَلْنَا لَهُمْ أَزْوَٰجًا وَذُرِّيَّةً ۚ وَمَا كَانَ لِرَسُولٍ أَن يَأْتِىَ بِـَٔايَةٍ إِلَّا بِإِذْنِ ٱللَّهِ ۗ لِكُلِّ أَجَلٍ كِتَابٌ
ከአንተ በፊትም መልክተኞችን በእርግጥ ልከናል፡፡ ለእነርሱም ሚስቶችንና ልጆችን አድርገናል፡፡ ለማንኛውም መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ ተዓምር ሊያመጣ አይገባውም፡፡ ለጊዜው ሁሉ ጽሑፍ አለው፡፡
አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላን በታላቁ ውድ ነብያችን ላይ ዘመን የማይሽረው ታላቁን ተዓምር ቁርዓንን ስላወረደልን እናመሰግነዋለን፣ ሃቁን የምንጠብቀውም ያድርገን፡፡ የፀጋዎች ሁሉ ሰጪ አላህ ብቻና ብቻ መሆኑን አውቀው አምልኮዋቸውን ለእርሱ ብቻ ከሚያደርጉት በእርሱም ላይ ምንንም ማንንም ከማያጋሩት ባርያዎቹ ያድርገን፡፡
የአላህ ሰላትና ሰላም ታላቁ ታዓምር ቁርዓን በወረደባቸው ነብይ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡