Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በአላህ በማረጋገጥ ማመን ከጤንነት ይበልጣል።

👌🏼በአላህ በማረጋገጥ ማመን ከጤንነት ይበልጣል።
🌴አቡበከር አስ–ሲዲቅ ለሰዎች ንግግር ለማድረግ ቆመና አለቀሰ እንዲህ አለ ~
በመጀመሪያው ዓመት የአላህ መልእክተኛ ሚንበር ላይ ቆሙና አለቀሱ ከዛ በመቀጠል " አላህን ይቅርታንና ጤንነትን ጠይቁት ማንም በአላህ በእርግጠኝነት ከማመን ቀጥሎ እንደ ጤንነት መልካም ነገር አልተሰጠውም አሉ"።
📙 [ሱናን አት–ቲርሚዚ 3558]
👉🏾 አልሚናዊ አላህ ይዘንለትና~
አልዓፍው ማለት: ሀጢአትን ማራገፍ ሲሆን
አልዓፊያ ማለት ደግሞ ከበሽታና ከችግር መዳን ማለት ነው።
🔶ከዛ በመቀጠል በዲንና በዱንያ ጤንነት መካከልን ሰበሰቡ። ምክንያቱም የአንድን ባሪያ መስተካከል በሁለቱም አገራት ሊሟላ የሚችለው በይቅርታ እና በየቂን ( እርግጠኝነት) ነው።
👉🏾 እርግጠኝነት የአኺራን ቅጣት ይከላከላል።
👉 ዓፊያ ደግሞ በዱንያ በአካልና በልብ ያለውን በሽታ ይከላከላል ።
📚 [ፈይዱልቀዲር (4/142)]
👌🏼اليقين في الله أفضل من العافية:
قام أبو بكر الصديق خطيبا في الناس ثم بكى فقال :
قام رسول الله (ﷺ) عام الأول على المنبر ثم بكى فقال <<اسألوا الله العفو والعافية ،فإن أحداً لم يعط بعد اليقين خيراً من العافية >>
📔 [سنن الترمذي:3558]
🖊قال المناوي رحمه الله
🔹معنى العفو:محو الذنب
🔹ومعنى العافية :السلامة من الأسقام والبلاء.
🔶ثم انه جمع بين عافيتي الدنيا والدين لأن صلاح العبد لا يتم في الدارين إلا بالعفو واليقين .
👈🏻فاليقين يدفع عنه عقوبة الآخرة .
👈🏻والعافية تدفع عنه أمراض الدنيا في قلبه وبدنه.
📚[فيض القدير:4/142]