Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል~ 👉🏾የሸይጣን ተንኮል በስድስት ነገሮች ላይ መጠቅለል ይቻላል።

👉🏾 ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ይላል~
👉🏾የሸይጣን ተንኮል በስድስት ነገሮች ላይ መጠቅለል ይቻላል።
1.  የክህደት፣ ሺርክ እና አላህንና መልእክተኛውን የመጻረር ተንኮል
2. የአዲስ ፈጠራ (ቢድዓ) ተንኮል~ ቢድዓ ሸይጣን ዘንድ ከሀጢአትና ከአላህ መንገድ ከመውጣት (ፋሲቅ ከመሆን) ተወዳጅ ነው። ምክንያቱም ጉዳቱ በዲኑ ላይ ሲሆን እሱም ተሻጋሪ ሀጢአት ነው።
3. ታላላቅ ወንጀሎች በተለያዩ ዓይነቶቹ
4. እነዛ ሀጢአቶች ሲሰባሰቡ ባለቤቱን የሚያጠፉ የሆኑ ታናናሽ ሀጢአቶች
5. ምንዳም ሆነ ቅጣት የሌለባቸውን በተፈቀዱ ነገሮች ላይ ውጥረት ውስጥ ማስገባት ሲሆን ከዚህ የባሰው ደግሞ ውጥረት ውስጥ በገቡበት ጊዜ ያጠፉትን የመልካም ስራን ምንዳ ማሳጣት ነው።
6. በደረጃው ዝቅ ያለውን ስራ በላጭ ከሆነው ስራን ውጥረት ውስጥ እንዲገባ በማድረግ ሊያገኘው የነበረውን ከፍተኛ ደረጃና ምንዳ ማሳጣት ናቸው።
📙ምንም:  [በዳኢዕ አልፈዋኢድ 3/ 799–801]