የጁምዐ ፈትዋ፦
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ )እንዲህ ይላሉ፦
"በጁምዓ ሆነ በዒድ ኹጥባ ፣ለኢማሙም ሆነ ለመእሙሙ(ሰጋጁ) በኹጥባ ወቅት ሁለት እጆችን አንስቶ አሚን ማለት በሸሪዓ ቦታ የለውም።
በሸሪዓ የሚፈቀደው ፦
ኢማሙ ዱኣ ሲያደርግ ፀጥ ማለትና በነፍሱና በሱ መካከል ድምፁን ከፍ ሳያደርግ አሚን ማለት ይጠበቅበታል።
እጅን በመዘርጋት ከፍ ማድረግ አይፈቀድም።
ምክንያቱም፦ የአላህ መልክተኛ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም በጁምዓም ሆነ በዒድ ኹጥባ እጃቸውን አያነሱም ነበርና።"
መጅሙዓል ፈታዋ (12/339)