Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዐይንን መገደብ ልቦች እንዳይሸፍቱ መድሃኒቱ ከሠለፎች አንደበት


📗ከሠለፎች አንደበት

ዐይንን መገደብ ልቦች እንዳይሸፍቱ
መድሃኒቱ

ሁሉን ነገር በጥበቡ ያስቀመጠውና የሚበጀንም ሆነ የሚጎዳንን አዋቂ የሆነው ፈጣሪያችን አላህ
« قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّـهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ ﴿٣٠﴾ وَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ … {٣١}»
النور: [30-31]
«ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነውና፡፡ ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጦቻቸውንም ከእርሷ ግልፅ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡» ይላል።
【አል-ኑር: 30-31】

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢብነል-ቀይይም [ረሂመሁላህ]
قال ابن القيم رحمه الله : -
"جعل الله سبحانه العينَ مرآةَ القلب، فإذا غضَّ العبدُ بصَرَه غضَّ القلبُ شهوتَه وإرادتَه، وإذا أطلقَ بصرَه أطلقَ القلبُ شهوتـه ".
📚 المصدر :[إغاثة اللهفان:47/1]
«ምንም አይነት እንከን የማይደርስበት አምላካችን አላህ … ዐይንን የልብ [ማሳያ] መስተዋት አድርጓታል። ስለዚህም አንድ የአላህ ባርያ አይኑን ሰበር ሲያደርግ ስሜቱም ፍላጎቱም ሰበር ይላል። ዐይኑን ልቅ ሲያደርገው ደግሞ ልብም ስሜቱን ልቅ ያደርገዋል።» ብለዋል።
【ኢጋሰቱ-ልለህፋን: 1/47】

ስለሆነም ለፈታኙ በሽታ ከመዳረጋችን በፊት መከላከያው ቅርባችን ነውና አይናችንን ቆጠብ እናድርጋት።
※::::::፨::::::::※::::::::※:::::::※

20Sefer1437- 04Dec15
www.fb.com/tenbihat
ከተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ
https://telegram.me/tenbihat