Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢባዳ : የኢባዳ መስፈርቶች Part 2

የኢባዳ መስፈርቶች
☞ አንድ ሠው አንድ ኢባዳን ከመስራቱ በፊት ሶስቱ ነገሮችን ቀደም ብሎ ማስተካከል ይኖርበታል
① በአላህ ማመን
በአላህ ማመን ከ ኢማን መሰረቶች ሁሉ ወሳኙ የላቀ ደረጃ ያለውና የአእማዶች ዋና ምሰሶ ሲሆን የተቀሩት የኢማን መሰረቶች የእርሱ ቅርንጫፍና በርሱ ውስጥ ተካታቾች ናቸው፡፡ በአላህ ማመን አላህ በጌትነቱ ፣በአምላክነቱ ፣ በስሞቹና ባህሪያቱ ብቸኛ መሆኑን ማመን ሲሆን እነዚህ ሶስቱ በአላህ
ለማመን ዋና ዋና መሰረቶች ናቸው፡፡
እንዲያውም ከግድፈት የፀዳው የእስልምና ሃይማኖት “ተውሂድ ” የተሰኘበት ምክንያት አላህ በንግስናውና በጌትነቱ አጋር
የሌለው ፣ በአካሉ ፣በስሞቹና ባህሪያቱ አምሳያ የሌለውና እንዲሁም በአምልኮ ቢጤ የሌለው ብቸኛ መሆኑን በማመን
የተመሰረተ በመሆኑ ነው፡፡ በዚህ መሰረት የነብያትና የመልዕክተኞች ተውሂድ በሶስት
እንደሚፈልግ ግልፅ ይሆናል፡፡
አንደኛው ክፍል “ተውሂድ ሩቡብያ” ፡- አላህ የሁሉም ነገር ጌታ፣ ንጉስ፣ ፈጣሪና ሲሳይ ለጋሽ መሆኑን ፣ ህይወት ሰጭ ፣ ገዳይ ፣
ጠቃሚ፣ ጎጂ፣ በጭንቅ ጊዜ ሲጠራ አቤት ባይ ፣የነገሮች ሁሉ ገዥ ፣የመልካም ነገሮች ባለቤት ነገሮችን ሁሉ ወደርሱ መላሽና
በእነዚህ ነገሮች ሁሉ አጋር የሌለው መሆኑን ማመን ነው፡፡
ሁለተኛው ክፍል “ተውሂዱል ኡሉሂያ” ፡-ራስን ዝቅ ብሎበመተናነስ ፣ በመውደድ፣በመፍራት፣ በማጎንበስ፣በግንባር በመደፋት፣ በማረድ፣ስለትን በማቅረብና በሌሎችም የአምልኮ ዘርፎች አላህን ብቸኛ ማድረግና አጋር እንደሌለው ማመን ማለት ነው፡፡
ሶስተኛው ክፍል “ተወሂዱል አስማኢ ወሲፋት”፡- አላህን በቁርአኑና በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሀዲሶች እራሱን በሰየመባቸውና
በገለፀባቸው ስሞችና ባህሪያት እርሱን ብቸኛ በማድረግ ፣ከጉድለት ፣ ከነውርና የእ
የእርሱ መለያ የሆኑትን ባህሪዎች
ከፍጡራን ጋር ከማመሳሰል መጠንቀቅ ፡፡ እንዲሁም አላህ ሁሉን ነገር አዋቂ፣ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ፣ህያው፣ ራሱን ቻቀይ፣
ማንጎላጀትም ሆነ እንቅልፍ የማይዘው፣ ተፈፃሚ የሆነ ፍላጎትና የላቀ ጥበብ ባለቤት፣ሰሚ፣ተመልካች፣አዛኝ እንደሆነ ፣ ከዐርሽ በላይ ስልጣኖችን ተቆጣጣሪ፣ ንጉስ፣ቅዱስ የሆነና ሌሎችም
እጅግ በጣም ያማሩ ስሞችና የላቁ ባህሪዎች ያሉት መሆኑን ማመን ማለት ነው
✔ በአላህ ሳይታመን የሚሠራ ኢባዳ ፋይዳ አይኖረውም ይህን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላል "(ከሀዲያን) ከስራ ወደ ሚሠሩት ስራ አሰብን የተበተነ አብዋራም አደረግነው "
②(ኢኽላስ) ፍፁማዊነት ይህም ማለት የሚሠራውን ኢባዳ ፍፁም ለአላህ ብቻና ብቻ ማድረግ (ስራን ከእዩልኝ እናከይሰሙላ የፀዳ ማድረግ ማለት ነው)አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ፦ "ለሡ ሀይማኖትን ጥርት አድርገው እንዲገዙት እንጂ አልታዘዙም "
☞ ይህ ጉዳይ በርካታዎቻችን የምንፈተንበት ከባድ በሽታ ነው ። ወደ አንድ ሠው ልብ ዘልቆ ሲገባ ፍፁም ረቂቅ በሆነ መንገድ መሆኑ ነገሩን ከባድ ያደርገዋል ።
☞ በዚህ በሽታ የተለከፈ ሠው የሚሠራው ስራ ፈፅሞ ተቀባይነት አይኖረውም አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ይህን አስመልክቶ በሀዲሰ አል ቁድስ እንዲህ ይላል ። "ከኔ ጋር አጋርቶ አንድን ስራ የሠራ ሠው ስራውንም ሰውዬውንም እተወዋለሁ "
☞ እስቲ እራሳችንን እንፈትሽበት ዘንዳ እነዚህን ጥያቄዎች እራሳችንን እንጠይቅ
1) ፌስቡክ ላይ ስንፅፍ ምን ፈልገን ነው፡፡ የ ላይክ ብዛት ለመቁጠር ከሆነ አላህ ይጠብቀን መክሰራችንን አውቀን ዛሬውኑ ስራችንን እናስተካክል፡፡
2) ዳዕዋ ስናደርግ፤ ‹‹ብቃት አለው›› መባል ፈልገን ነው ወይንስ የአላህን ፊት ፈልገንበት??? ኢኽላሳችን ችግር ካለው አሁንም ቢሆን ሳይረፍድ ዛሬውኑ፤ አሁኑኑ ለአንድ አላህ ብቻ
ስራችንን እናጥራ፡፡
3) ለቤተሰባችንም ይሁን ለሌሎች መልካም ስንውል ምን ፈልገንበት ነው???
☞ የአላህ ፊት ያልተፈለገበት ኢባዳ ፋይዳ የለውም!!
③ ሙታበአ(ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለምን መከተል) ፦ በአላህ ያመነ እንዲሁም ስራውንም አላህ ይመነዳኛል ሢል አስቦ ኢባዳ
የሚሠራ ሠው የሚሠራውን ኢባዳ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም
ሠርተውታል አልሠሩትም ብሎ መፈተሽ ይኖርበታል አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ እንዲህ ይላል ፦ ""መልዕክተኛው ያመጣላችሁን ያዙት ፣ ከከለከላችሁም ተከልከሉ ""
⇑ ከእነዚህ (ከላይ ከተጠቀሡት ሦስት መስፈርቶች) አንዱን ያጎደለ ኢባዳው
ተቀባይነት አይኖረውም!!!
☞ ሙስሊም ያልሆነ ሠው የሠራው ስራ ዋጋ የለውም
☞ ኢቲባእ የሌለው ስራ ቢድአ ነው
☞ የአላህ ፊት ያልተፈለገበት ስራ እዩልኝ እና ስሙልኝ ነው
(ትንሹ ሽርክ ነው)
ይቀጥላል
https://m.facebook.com/kedmia.letewhid/