Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከወርቃማ አንደበቶች! ቀልቡን ሰረቅነው!

ከወርቃማ አንደበቶች!
ቀልቡን ሰረቅነው!
አንድ ሌባ ወደ ማሊክ ኢብኑ ዲናር (አላህ ይዘንላቸውና) ቤት ገባ ፣ የሚሰርቀውም አንዳች እቃ ፈለገ ሆኖም ምንም ነገር አላገኘም ከዚያም ማሊክ እየሰገዱ ተመለከተ!
ማሊክም ሰላታቸውን (እንዳሰላመቱ) እንደጨረሱ ወደ ሌባው ተመለከቱና እንዲህ አሉት፦
የዱንያን መጠቃቀሚያ ጠይቀህ (ፈልገህ) መጣህ አላገኘህም ለአኼራ የሚሆን መጠቃቀሚያ አለህን? ??
ሌባውም መልስ ሰጠና በእሳቸው (ሁኔታ) እየተገረመ ተቀመጠ
ማሊክም መገሰፃቸውን ጀመሩ ሰውየው (ልቡ ተነክቶ) እስክያለቅስ ድረስ ፣ (ከዚያም) ከእርሳቸው ጋር ለሰላት ወደ መስጂድ ሄዱ ሰዎች በሁለቱ ጉዳይ በጣም ተገረሙ!
ታላቅ ዓሊም ከታላቅ ሌባ ጋር! …
ይህ የማይታመን ነው???!!!
ማሊክ (ስለ ሁለቱ ሁኔታ) ተጠየቁ እንዲህም አሏቸው፦
«ሊሰርቀን መጣ ቀልቡን ሰረቅነው!»
ምንጭ፦
[ታሪኽ አል ኢስላም ሊዘሀቢይ 2/144]
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ!
«ወደ መልካም ያመላከተ በሰራበት ሰው ልክ ምንዳን ያገኛል»
ــــــ ❁ ❁❁ ❁ ــــــ
✍ ዳሩል ኢስላህ
https://telegram.me/haiderkhedir