Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሚሊኒየሙ ስምምነት በኢኽዋኖችና በሱፍዬች መሐል?


የሚሊኒየሙ ስምምነት በኢኽዋኖችና በሱፍዬች መሐል?
ኢኽዋኖችና ሱፍዬች የሚሊኒየሙ ስምምነት በተባለው መዘጋጃ ቤት ውስጥ ከተስማሙበትና ከተፈራረሙባቸው ነጥቦች ውስጥ ለናሙና የሚከተሉት 2ቱ ይገኙበታል፡፡
5) ‹‹በየመስጂዱ በሚሰጡ ዳእዋዎች ልዩነት የሚያስነሱ ነጥቦች ርዕስ ሆነው እንዳይቀርቡ በጋራ እናደርጋለን፡፡ ኺላፍ ባለባቸው ነጥቦች ዙርያ ጥያቄ ከተነሳም አንዱን ከሌላው በማያበላልጥ መልኩ መልስ እንዲሰጥባቸው ማድረግ እንደሚገባ ተማምነን ይህንኑ በጋራ ተስማምተናል፡፡››
ለዚህ የጥመት ስምምነት ትንሽ መልሶች
- ‹‹በየመስጂዱ በሚሰጡ ዳእዋዎች ልዩነት የሚያስነሱ ነጥቦች ርዕስ ሆነው እንዳይቀርቡ በጋራ እናደርጋለን፡፡›› ብለዋል፡
ሃቅና ባጢል እማ በፍፁም አብረው አይሄዱም ልዩነትም ያስነሳሉ፡፡ ለምሳሌ ሽርክ ሲወገዝ ሽርክ ላይ የወደቁና፣ ኹራፋት ተከታዬች ይከፋሉ፡፡ ቢድዐ ሲጋለጥ ቢድዐ አራማጆች ይከፋሉ፣ በእርግጥም በሱንይና በሙብተዲ መሃል ልዩነት ይነሳል፡፡ ታድያ መስጂድ ውስጥ የሚሰጠው ዳዕዋ ልዩነት እንዳያስነሳ በሚል የተውሂድና ሱና ስብከት፣ ሽርክና ቢድዓና ማውገዝ ሊቀር ነውን?
ዳሩ እናውቃቸዋለን ሱፍያም የመጅሊሱን ስልጣን በያዙ ጊዜ የተውሂድ ዳዕዋ እንዳይደረግ ብሎም ወደ ተውሂድ የሚጣሩ ወንድሞችን ሲያስፈራሩ ብሎም ከኢኽዋን ጋር በመመሳጠር ለደህንነት ሲያስይዙም ነበር፡፡
- በተለያያችሁ ጊዜ ወደ ቁርዓንና ሀዲስ ተመለሱ እንጂ አንዱ ከአንዱ እንዳይከፋ በሚል ሃቅን ጥላችሁ ሂዱ የሚል ሀይማኖት ኖሮን አያውቅም፡፡ መሃይማንና አውቆ አጥፊዎች ቢያውቁ ኖሮ
ማስረጃዎች
ሃቅን መከተል ግዴታችን ነው አላህ እንዲህ ይላል
فَلَا وَرَبِّكَ لَا يُؤْمِنُونَ حَتَّىٰ يُحَكِّمُوكَ فِيمَا شَجَرَ بَيْنَهُمْ ثُمَّ لَا يَجِدُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ حَرَجًا مِّمَّا قَضَيْتَ وَيُسَلِّمُوا۟ تَسْلِيمًا
በጌታህም እምላለሁ በመካከላቸው በተከራከሩበት ፍርድ እስከሚያስፈርዱህ ከዚያም ከፈረድከው ነገር በነፍሶቻቸው ውስጥ ጭንቀትን እስከማያገኙና ፍጹም መታዘዝንም እስከሚታዘዙ ድረስ አያምኑም፤ (ምእመን አይኾኑም)፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَطِيعُوا۟ ٱللَّهَ وَأَطِيعُوا۟ ٱلرَّسُولَ وَأُو۟لِى ٱلْأَمْرِ مِنكُمْ ۖ فَإِن تَنَٰزَعْتُمْ فِى شَىْءٍ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْءَاخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አላህን ተገዙ፡፡ መልክተኛውንና ከእናንተም የስልጣን ባለቤቶችን ታዘዙ፡፡ በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡
በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት እንጂ የተባለው የእኛዎቹ ዲንን አበላሾች እንዳሉት ‹‹አንዱን ከሌላው በማያበላልጥ መልኩ መልስ እንዲሰጥባቸው ማድረግ እንደሚገባ ተማምነን ይህንኑ በጋራ ተስማምተናል›› ብሎ መደስኮርና መፈራረም አልነበረም፡፡
6) ‹‹የነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መውሊድ አከባበር ሥነ-ሥርዐት ብሔራዊ በዓልነቱ ታውቆ ይከበራል፡፡ ስለ በዐሉም ሆነ የነብዩን ሲራ አስመልክቶ የሚሰጡ ትምህርቶች በሁሉም ወገኖች ያለ ተብዲዕ (ቢድዐ ነው ሳንል)፣ ያለ ተፍሲቅ (ፊስቅ ወንጀል አለበት ሳንል)፣ ያለ ተሸሪክና (ሽርክ አለው ሳይባልና)፣ ያለ ተክፊር እንዲከናወኑ ለማድረግ በጋራ እንሰራለን፡፡››
ይህቺ እርኩስ የሆነች ስምምነት ናት፡፡ የሽርክ መናሀርያ የሆነውን መውሊድ ‹‹ያለ ተሸሪክና (ሽርክ አለው ሳይባልና)፣ ቢድዐ ነው ሳንል›› ብሎ መስማማት፣ ከዚህም አልፎ ‹‹ያለ ተፍሲቅ (ፊስቅ የለውም)›› ብሎ ወንድና ሴት ተደባልቀው የሚጨፍሩበትን፣ ይህን አደንዛዥ ቅጠል ጫት የሚቃምበትን፣ ሲጋራ የሚጨስበትን አረ ስንቱ እርኩስ ነገር ያለበትን እንዲከበር መስማማታቸው በጥፋት ላይ የተሰባሰቡ ለመሆናቸው ማስረጃ ነው፡፡
አላህ በምን ጉዳይ እንድንረዳዳ እና በምን ጉዳይ እንዳንረዳዳ እንዲህ ሲል በአንድ አንቀፅ ላይ ያስቀምጥልናል
وَتَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْبِرِّ وَٱلتَّقْوَىٰ ۖ وَلَا تَعَاوَنُوا۟ عَلَى ٱلْإِثْمِ وَٱلْعُدْوَٰنِ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ
በበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ፡፡ ግን በኃጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና፡፡
ይህ ነው እንግዲህ የቢድዐ ሰዎች ሴራ ዲንን፣ ሱናን፣ ተውሂድን ስሜታቸውን በመከተል መናድ፡፡ ድንገት እኛ እኮ አሳማሪዎች ነን ይሉ ይሆናል፡፡ ታድያ ምነው በሱና ላይ መቆም አቃታቸው?
ምነው ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና) ሰሃባዎች፣ ሰለፉነ ሷሊሁን የነበሩት መንገድ ላይ ለምን መቆም አቃታቸው?
አላህ እንዲህ ይላል
وَإِذَا قِيلَ لَهُمْ لَا تُفْسِدُوا۟ فِى ٱلْأَرْضِ قَالُوٓا۟ إِنَّمَا نَحْنُ مُصْلِحُونَ
ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡
أَلَآ إِنَّهُمْ هُمُ ٱلْمُفْسِدُونَ وَلَٰكِن لَّا يَشْعُرُونَ
ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡
ኢህዋኖች ከሱፍዬም፣ ከቀብር አምላኪውም፣ ከቲጃንዩም፣ ከሺዐውም፣ ከካፊሩም ጋር አንድ ነን ይላሉ መሆንም አያቅታቸውም፡፡ እነሱ ጦርነታቸውና ጠላትነታቸውን የሚያሳዩት ሰለፍዬች፣ የተውሂድ ተጣሪዎች፣ የሱና አፍቃሪዎች ላይ ነው፡፡
ዳሩ አደለም መዘጋጃ ቤት፣ ቤተ መንግስትም ገብተው ቢፈራረሙት ባጢል ሃቅ አይሆንም፡፡
የውሸት ስምምነትና የውሸት አንድነት ሁሌም ውሸት ነው፡፡ ይሀው የውሸቱ አንድነት መዝለቅ አቅቶት አሁን እርስ በእርስ ተከዳዱ፡፡ምስጋና ሁሉ ለአላህ ይተገባ ነው፣ አላህ ዲን አበላሾችን ድባቅ መታቸው፡፡
የስምምነታቸውን ወረቀት ከነፊርማቸው ማረጋገጥ የፈለገ ከሚከተለው ሊንክ ዳውንሎድ ያድርግ፡፡
https://goo.gl/80CXch
የአላህ ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸውና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Post a Comment

0 Comments