Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሺዓዎችን አሏህ የስራቸውን ሰጣቸው! «ንፁሀንን መወንጀል እንዲህ ያስቀጣል!!» የ1437 ዓሹራእ መልእክት


✔ ሺዓዎችን አሏህ የስራቸውን ሰጣቸው!
«ንፁሀንን መወንጀል እንዲህ ያስቀጣል!!»
የ1437 ዓሹራእ መልእክት
بسم الله الرحمن الرحيم
الحمد لله رب العالمين والصلاة والسلام على النبي الأمين وعلى آله وصحابته أجمعين أما بعد
በስድስተኛው ዓመተ ሂጅራ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም " ከበኒል ሙስጠሊቅ " ዘመቻ እየተመለሱ እጅግ በጣም አስደንጋጭ ክስተት ተከሰተ ይህንንም ክስተት እናታችን ዓዒሻ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ስትል ትገልጸዋለች፥
" ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደ አንድ ቦታ መጓዝ ሲፈልጉ እጣ በማውት ከሚስቶቻቸው መሀል አንዷን ይዘው ይጓዙ ነበር ከዘመቻዎቻቸው መሀል በአንዱ ዘመቻ ጊዜ ( ገዝወቱ በኒል ሙስጠሊቅ ) እጣው ለኔ ወጣና ከነቢዩ ጋር ተጓዝኩኝ ይህም ኢስላማዊ ሒጃብ ግዴታ ከተደረገ በኋላ ነበር ለሴቶች በተዘጋጀ ልዩ የግመል ኮርቻ ላይ ሆኜ ጉዞ ጀመርኩኝ ስጓዝም ይሁን ሳርፍ እዛው ውስጥ ነበር የምሆነው ዘመቻው ተጠናቆ እየተመለሰን ሳለ ከመዲና ቅርብ የሆነ ቦታ ላይ አረፈን መጸዳዳት ፈልጌ ራቅ ብዬ ሄድኩኝ ጨርሼ ስመለስ አንገቴ ላይ የነበረውን ጌጥ አጣሁት ወደ ቦታው ተመልሼ በመሄድ ስፈልገው ቆይቼ አጥቼው ስመለስ ነቢዩና ባልደረቦቻቸው (ሰራዊቱ በሙሉ) ከቦታው ተንቀሳቅሰዋል። እኔም እንደተለመደው እዛው ኮርቻዬ ውስጥ ያለሁ መስሏቸው ባዶውን ኮርቻ ግመሉ ላይ ጭነው ተጉዘዋል! ያኔ እንደዛሬ ሴቶች ወፍራም ስላልነበሩኩ የኮርቻውን መቅለል ብዙም ልብ አላሉትም። እኔም ደግሞ ገና ወጣት ነበርኩኝ ስለሆነም እዛ ውስጥ ያለሁ መስሏቸው ትተውኝ ተጓዙ።
ቦታው ላይ ስደርስ ምንም ሰው የለም መጀመሪያ የነበርኩበት ቦታ ላይ በመሆን መጠበቅ እንዳለብኝ ወሰንኩ። ምናልባት የሆነ ሰዓት ላይ አለመኖሬን አውቀው ወደዛ ሊመለሱ ይችላሉ በማለት እዛ ስመለስ ጌጡንም አገኘሁት ( ከግመሉ ስር ነበር የተደበቀው ) እዛ ቁጭ ብዬ ሳለ እንቅልፍ ጣለኝና ተኛሁ። ሰፍዋን ኢብኑ አልሙዐጢል የሚባለው ሰሓቢይ ከሰራዊቱ ተነጥሎ ከኋላ እየተጓዘ ነበረና ካለሁበት ቦታ ደርሶ የተኛ ሰው ጥቁር ልብስ ተመለከተ። ሒጃብ ግዴታ ከመደረጉ በፊት ያውቀኝ ስለነበረም ተኝቼ አይቶኝ ማንነቴን አወቀ። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን! ሲል ድምጹን ሰምቼ ከእንቅልፌ ነቃሁ ቶሎ ብዬም ፊቴን ሸፈንኩኝ። ወላሂ... ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ከሚለው ውጪ አንዲትንም ቃል አልተነጋገርንም። ከሱ ሌላ ቃልም አልሰማሁም። የራሱን ግመል አንበርክኮልኝ ግመሉ ላይ ወጣሁና እሱ ከፊት እየተጓዘ ነቢዩና ሰራዊቱ ካሉበት ደረስን።
ይህንን ሲመለከቱ የጠፉና የተዋረዱ ሰዎች ውራዳ ተግባር መፈፀም ጀመሩ (ስሜን አጠፉ ለማለት ነው -እሷ ያወቀቸው ኋላ ላይ ነው ) የዚህን ሴራ ትልቁን ድርሻ የተሸከመው የሙናፊቆች አለቃ ኢብኑ ኡበይ ኢብኑ ሰሉል ነበረ ( ቢሆንም ከሰሓባ ወንድና ሴቶችም ጥቂት ሰዎች ወሬውን ተቀባብለው ነበር ) ።
መዲና እንደደረሰን ለአንድ ወር ታምሜ ተኛሁ። ሰዎች ለካ ስሜን እያጠፉ ነው እኔ ምንም የማውቀው ነገር የለም! ትንሽ ውስጤ ላይ የሚሰማኝ ነገር ቢኖር ሌላ ጊዜ ስታመም ከነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አገኘው የነበረውን ርህራሄ ማጣቴና ወደ ቤት ገባ እያሉ እንዴት አደረች ብቻ እያሉ መውጣታቸው ነበር ይሄንንም በሸር አላሰብኩትም ነበር!
ከእለታት አንድ ቀን ምሽት ላይ ከኡሙ ሚስጠሕ ጋር ወደ ውጪ ወጥቼ እየተመለሰን ሳለ ኡሙ ሚስጠሕ ልብሷ አደናቅፏት ስትወድቅ ውርደት ለሚስጠሕ ይሁን አለች! እኔም መጥፎ ቃል ተናገርሽ! እንዴት ከነቢዩ ጋር የበድርን ዘመቻ የተሳተፈን ሰው ትሰድቢያለሽ?! አልኳት። እሷም እንዴ እሱ ያለውን አልሰማሽም እንዴ?! አለችኝ። ምን አለ ብዬም ጠየቅኳት፤ ቀጣፊዎች ያሉትን በሙሉ ነገረችኝ ((ከስፍዋን ጋር አውቀው ወደኋላ ቀርተው ዝሙት ሰርተው ነው የመጡት ተብሎ እየተወራ እንደሆነ ነገረቻት)) ይህን ስሰማ በበሽታዬ ላይ በሽታ ተጨመረብኝና ልክ ወደ ቤት ስገባ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መጡ። እንደተለመደውም እንዴት ናት ብለው ጠየቁ እኔም ጉዳዩን ከነሱ ይበልጥ ማጣራት ፈልጌ ነበርና ወደ አባት እናቴ ቤት ልሄድ ትፈቅድልኛለህ? አልኳቸው። ፈቅደውልኝም ሄድኩና እናቴን እንዲህ ስል ጠየኳት፥ እናትዬ ሰዎች የሚያወሩት ምንድነው?! እሷም ልጄ ሆይ እራስሽን አረጋጊ ብዙ ጊዜ ሴት ልጅ ባላንጣዎች ካሏትና ባሏ ዘንድም ተወዳጅ እንደሆነች ካወቁ እንደዚህ አይነት ነገር ይከሰታል አለችኝ (እሷን ለማረጋጋት ብላ የተናገረችው ንግግር ነው ) ሱብሓነሏህ! ሰዎች ይህን አውርተዋል ማለት ነው??! አልኩኝ ሌሊቱን በሙሉም ምንም ሳልተኛ እያለቀስኩ አደርኩኝ።
በጉዳዩ ዙሪያ ከአሏህ ዘንድ ወሕይ ሳይወርድ በመዘግየቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዐሊይንና ኡሳማ ኢብኑ ዘይድን ጠርተው አማከሯቸው ኡሳማ ስለኔ የሚያውቀውን ጥሩ ነገር ነገራቸው እንደወትሮው እንዲኖሩም ሀሳብ ሰጣቸው ዐሊይ ደግሞ አሏህ አላጠበበብህም ከሷ ሌላ ብዙ ሴቶች አሉ ይበልጥ ደግሞ አገልጋዩዋን ጠይቅ አላቸው ነቢዩም በሪራን ( የዓዒሻን አገልጋይ ) ጠርተው ከዓዒሻ እንድትጠረጠር የሚያስደርግ ነገር አይታ ታውቅ እንደሆነ ጠየቋት እሷም በእውነት በላከህ ጌታ አላህ ይሁንብኝ እኔ ከሷ ምንም የሚጠላ ተግባር አይቼባት አላውቅም! እንደው ልጅ በመሆኗ ሊጥ እያቦካች እንቅልፍ እየጣላት ሊጡን ፊየሎች ሲበሉባት ከማየቴ በስተቀር እሷ ላይ ምንም የማየው መጥፎ ነገር የለም አለቻቸው!
ይሄኔም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሚንበር ላይ በመውጣት (ችግሩን መቅጨትና የቤተሰባቸውን ስም የማጥፋቱንና የነቢዩን ሰላም የመንሳቱን ስራ በመሪነት ሲሰራ የነበረውን ኢብኑ ኡበይን ጉዳይ መላ ማለት ፈልገው) የሚከተለውን ንግግር አደረጉ።
"ሙስሊሞች ሆይ! ጥቃቱና ችግሩ ጓዳዬ ድረስ ዘልቆ በመመግባት አዛ እያደረገኝ ያለ ሰው ላይ ለምወስደው እርምጃ ተገቢነቱን አውቆ ማነው ኡዝር የሚሰጠኝ? ወላሂ ከቤተሰቤ (ከዓዒሻ) መልካምን ነገር እንጂ አላውቅም። ከሷ ጋር በመጥፎ ስሙን ያነሱትም ቢሆን ሰው ከሱ መልካምን ነገር እንጂ አላውቅም። ከኔ ጋር እንጂ ወደ ቤቴ ገብቶም አያውቅም አሉ። ይሄኔም የአውስ ጎሳ መሪ ኡሰይድ ኢብኑ አልሑደይር (ረዲየላሁ ዐንሁ) ተነስቶ እኔ አለሁ ይህ ሰው ከኛ ከአውስ ጎሳ ከሆነ በሰይፍ እንለዋለን ከኸዝረጆችም ከሆነ የፈለግከውን እዘዘን አላቸው።
በጊዜው የሱ ንግግር ኸዝረጆችን አስቀይሟቸው ብዙ ተጨቃጨቁ ነቢዩም አረጋግተዋቸው ተረጋጉ። ይህንንም ቀን እያለቀስኩ ዋልኩኝ።
በዚሁ ሁኔታ ላይ ከአባት እናቴ ጋር ሁነን ሳለ አንዲት ሴት ገባችና ከኔው ጋር ቁጭ ብላ ታለቅስ ጀመር። በዚህ መሀል ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መጡና አስፈቅደው ገቡ። ሰላምታ አቀረቡና ቁጭ አሉ። ይህ ወሬ ከተናፈስ ጀምሮ እኔ ጋር ቁጭ ብለው አያውቁም ነበር። አንድ ወር ሙሉም በኔ ጉዳይ ወሕይ ሳይመጣላቸው ቆይተው ነበር። ቁጭ እንዳሉም የሚከተለውን ተናገሩ፤ "ዓዒሻ ሆይ፥ እነሆ ስላንቺ ወሬዎች ደርሰዉኛል። ከወንጀሉ ንጹህ ከሆንሽ አሏህ ንጹነትሽን ያውጃል። ፈጽመሽውም ከሆነ ወደ አሏህ ተመለሺ አንድ ሰው ወንጀል ሰርቶ ከቶበተ አሏህ ይምረዋል።" ልክ ንግግራቸውን እንዳቆሙም እምባዬ ተቋረጠ። አባቴን ለነቢዩ መልስ ስጥልኝ አልኩት እሱም ወላሂ ምን ማለት እንዳለብኝ አላውቅም አለኝ። እኔም በጊዜው ገና ልጅ ነበርኩና ቁርኣን ብዙም አልቀራሁም ነበር እንዲህ ስል ተናገርኩኝ። በጌታዬ ይሁንብኝ ወሬውን እንደሰማችሁ አውቄያለሁ ልባችሁ ውስጥ እንደገባና እንደተቀበላችሁትም ተረድቻለሁ። እኔ ከዚህ የጠራሁ ነኝ ብላችሁ አታምኑኝም። ሰርቻለው ብላችሁ ደግሞ -እንዳልሰራሁት አሏህ የሚያውቅ ከመሆኑ ጋር- ታምኑኛላችሁ። በጌታዬ ይሁንብኝ ለኔና ለናንተ ምሳሌ ሆኖ ያገኘሁት የዩስፍን አባት ነው እሱም እንዲህ ባለ ጊዜ፥
[ فَصَبرٌ جميل والله المستعان على ما تصفون ]
"መበሳጨት የሌለበት ያማረ ትእግስት ከመታገስ ውጪ ሌላ አማራጭ የለኝም ችግሩን የምቋቋምበትን እገዛም የምጠይቀው ከአሏህ ነው" ሱረቱ ዩሱፍ 18
ንጹህ እንደሆንኩ አሏህ ያውቃል ከተባለውም ነገር ያጠራኛል ብዬ በማመን ፊቴን አዙሬ ፍራሼ ላይ ጋደም አልኩኝ። ነገር ግን በዚህ ዙሪያ አላህ ለኔ ብሎ ቁርኣን ያወርዳል የሚል ግምት አልነበረኝም። ቢያንስ ነቢዩ በህልማቸው አሏህ ያሳውቃቸውል ብዬ እገምት ነበር። ወላሂ እዛው እያለን ከቤት ማንም ሳይወጣ ነቢዩም ከቦታቸው ሳይንቀሳቀሱ ከሰማይ መልእክት መጣ።
ልክ ወሕዩ ወርዶ እንደተጠናቀቀ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሳቅ እያሉ ዓዒሻ ሆይ! አሏህ ከተባለው ነገር የጠራሽ መሆንሽን ተናገረ አሉኝ። ሱረቱን’ኑር ከ11 እስከ 20 ድረስ ያሉ አንቀጾችን አሏህ በዚህ ዙሪያ አወረደ።
አቡበክርም (አባቷ) ወሬውን ካወሩ ሰዎች መሀል አንዱ ለነበረው ሚስጠሕ ያደርገው የነበረውን እርዳታ ለማቆም ወሰነ። አሏህም እንዳያቆም የሚያደርግን አንቀጽ በማውረዱ ድጋፉን ቀጠለ። ነቢዩም በሸሪዓው መሰረት ንጹህ ሰውን በዝሙት የጠረጠረ ሰው ላይ መወሰድ ያለበትን እርምጃ ሰዎቹ ላይ ወሰዱ።
ይህንን ታሪክ ባጭሩ ያሰፈርኩትን የዓዒሻን ንግግር የተለያዩ ሙፈሲሮች፣ የሲራና ዘጋቢዎች ከኢኑ ሺሃብ ዘግበውታል።
ከዛ ጊዜ ጀምሮም በዚህ ዙሪያ የዓዒሻን ስም በመጥፎ የሚያነሳ ሰው አልነበረም። አሏህ የለም ያለውን ነገር አለ ማለት ስለሚሆን፤ መላው የአህለሱና ወልጀማዓ ዑለሞች ዘንድ አላህ ከተባለው ነገር ካጠራት በኋላ በዝሙት የጠረጠራት ሰው ከእስልምና እንደሚወጣ "ካፊር እንደሚሆን" ተስማምተዋል። ኢማሙ ማሊክ ደግሞ "ከሰሃቦች መሀል አንድን ሰሓቢይ የሰደበ ሰው መገረፍ አለበት ሲሉ ዓዒሻን በዝሙት የወነጀለ ሰው ግን መገደል አለበት ብለው ተናግረዋል።" ለምን ተብለው ሲጠየቁ ምክኒያቱም ቁርአንን አስተባብሏል ብለዋል።
ሆኖም ግን ነቢዩንና ቤተሰቦቻቸን እንወዳለን እያሉ የሚዋሹ የዲኑ የውስጥ ቀንደኛ ጠላት የሆኑት ሺዓዎች ከዚጌ በኋላ የጥመት አርአያዎቻቸውን በመከተል ዳግም ስሟን የማጥፋት ዘመቻ ጀምረዋል። በተለያዩ ወቅቶች በይፋ አሁንም ድረስ እናታችን ዓዒሻን በዝሙት ይወነጅላሉ። መህዲ ሲመጣ ከቀብሯ አውጥቶ ዝሙት የሰራ ሰው ላይ የሚወሰደውን እርምጃ ይወስድባታል ብለውም ይናገራሉ!
ነገር ግን አሏህ ከሰባት ሰማይ በላይ ከዚህ ነገር የጠራች መሆኗን የመሰከረላትን ድንቅ ሴት ስም የሚያጠፉ ሰዎችን አሏህ በጥበቡ ተገቢውን ቅጣት በራሳቸው እጅ በያመቱ ሙሐረም 10 (የዓሹራእ ቀን) ላይ እንድያገኙ አድርጓቸዋል!!
አጂብ አንድ ንጹህ ሰውን በዝሙት የወነጀለ ሰው አንድ ጊዜ ነበር 80 ጅራፍ ተገርፎ የሚያበቃው የነሱ ግን ወንጀላቸው በጣም የከበደና የነቢዩንም ክብር የሚነካ ስለነበረ በየዓመቱ ራሳቸውን በራሳቸው እጅ እንዲገርፉ እንዲቀጠቅጡ እንዲያቆስሉና እንዲያደሙ የዓለም መሳቂያም እንዲሆኑ አሏህ አድርጓቸዋል!
እነሱ ይህን የሚያደርጉት ሁሰይን ኢብኑ ዓለይ (የነቢዩ ልጅ የሆንችው የፋጢማ ልጅ ) በጠላቶቹ እጅ የተገደለበት ቀን ነውና በሀዘን እንዲሁም የሱ ደም እንደፈሰሰው እኛም ደማችንን እያፈሰሰን መዋል አለብን ብለው ነው። በጣም የሚገርምው ሁሰይንን የገደሉት ወይም እንዲገደል ያደረጉት እነሱው እራሳቸው መሆናቸው ነው!!
አሏህ ሊያዋርዳቸውና የዓዒሻንና የነቢዩንም ክብር በመንካታቸው በዓመቱ እራሳቸውን እንዲቀጡ አድርጓቸዋል።
ሁሰይንን አባክህን ወደ እነሱ ( ወደ ዒራቅ ሀገርሰዎች ) አትህድ የፊትና ሰው ናቸው በማለት እንደ እነ አብዱላህ ኢብኑ ዐባስ ኢብኑ ዑመር ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ አቡ ሰዒድ አልኹድሪ ሌሎችም ሰሃቦች እየመከሩት ሳይቀበል ቀርቶ ነው የሄደው። እራሳቸው የገደሉትን ሰው ሰበብ አድርገው እራሳቸውን ይቀጣሉ። በዚህም አላዋቂዎችን ለመሸንገልና በኡማው መካከል ፊትና መፍጥር እንዲሁም የሙስሊሙን ስም ማጥፋት ዓላማ አድርገዋል።
በሁሰይን መገደል እኛም ብናዝንም ሀዘናችን ከሸሪዓ የሚጋጭን ነገርና የሰው መሳቂያ እንድንሆን የእብድ ስራ እንድንሰራ አያደርገንም። ይልቁንስ ሰብር እናደርጋልን አሏህ እንዲምረውም ዱዓ እናደርጋለን ገዳዮችንም እናወግዛለን። እነደው ይሁን ቢባል እንኳ ነቢዩ አቡ በክር የሁሰይን አባት የሆነው ዐሊይ ሌሎችም ታላላቅ ሰሃባዎች የሞቱበትን ቀን ትተው ሁሰይን በሞት ቀን እንዲህ መሆናቸውና ማዘናቸው የሚገርም ነው!!
አላህ ከጥመት ይጠብቀን
ወሏሁ አዕለም ወሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱላህ
( አሕመድ ኣደም )
ቅዳሜ ሙሐረም 10 1437 ዓ.ሂ

Post a Comment

0 Comments