Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የባጢል ጥሩምባ ከመሆን እንጠንቀቅ!






የባጢል ጥሩምባ ከመሆን እንጠንቀቅ!

ማንኛውም ሀገር እርኩሳንንና ቅዱሳንን ያቀፈ ነው። በጥቂት ሰዎች መጥፎ ስራ አንድን ህዝብ በጥቅሉ መጥላትና ማጥላላት ፍርደገምድልነት ነው። የሳውዲ አረቢያን መልካም ነገሮችን ሁሉ በመጥፎ መተርጎምና የተለየ አላማ እንዳለው በማስመሰል ማቅረብ፤ ከባዶ ጥርጣሬ በመነሳት የስም ማጥፋት ዘመቻ ላይ መሳተፍ ከሙስሊም የማይጠበቅ አስቀያሚ ተግባር ነው።
ሳውዲ አረቢያን በመልካሙም በመጥፎዉም ክስተት ማጥላላት የዘውትር ስራቸው የሆነ ኩፋሮች፣ ሺአዎችና አህባሾች እንዲሁም ተክፊሮችና ኸዋሪጆችን ፕሮፖጋንዳ የሚያስተጋባ ማስተዋል የተሳነው ብቻ ነው።
በወረኞችና በኩፋሮች ፕሮፓጋንዳ የማይበጣጠሰውን ኢስላማዊ አንድነታችንን ቅድሚያ መስጠት ግድ ይለናል።
ሁሉም ሰው ስለሚናገረውና ስለሚፅፈው አላህ ዘንድ ተጠያቂ ነውና ጥንቃቄ እናድርግ። አለዚያ ወደድንም ጠላንም የባጢል ጥሩምባ እንሆናለን።

{وَلَا تَقْفُ مَا لَيْسَ لَكَ بِهِ عِلْمٌ ۚ إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا} [الإسراء : 36]

«ለአንተም በርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል (አረጋግጥ)፡፡ መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም እነዚህ ሁሉ ከእነሱ (ለምን እንደተጠቀመባቸው) ተጠያቂ ነውና፡፡»
አል ኢስራዕ 36

የመልእክተኛውንና የሰሀቦችን ሀገር፤ የቅዱስ ሀረመይን መገኛ፤ የተውሂድና ሱና ሀገር ሳውዲ አረቢያን አላህ ይጠብቃት። ሰላምና ብልፅግናን ይጨምርላት በተውሂድና በሱና ላቅ ያደርጋት ዘንድ አላህን እንለምነዋለን።

አሚን!

© ተንቢሀት