Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥሪ ለሙስሊሙ ኡማ! (የሃይማኖቱ ጉዳይ ለሚያሳስበው ሃላፊነት ለሚሰማው ሙስሊም ሁሉ!!!)

ጥሪ ለሙስሊሙ ኡማ!
(የሃይማኖቱ ጉዳይ ለሚያሳስበው ሃላፊነት ለሚሰማው ሙስሊም ሁሉ!!!)
በአዲስ አበባ እና በአንዳንድ የክልል ከተሞች አሕባሾች ድምፃቸውን አጥፍተው በተጠናከረ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ አካሄዳቸውም ህፃናትን ከተለያዩ አካባቢዎች በመሰብሰብ ረዘም ላለ ጊዜ በማሰልጠን ስለሆነ አደጋውን ይበልጥ የከፋ ያደርገዋል፡፡ በቁርኣን ሒፍዝ ስም በሚሰበስቧቸው ልጆች ልቦና ውስጥ አደገኛ የሆነ መርዝ በመትከል ዐቂዳቸውን እየበከሉ ስለሆነ ወገናችንን ለመታደግ ከወላጆች ዘንድ አስፈላጊውን ግንዛቤ ልንፈጥር፣ የምንችለውን ሁሉ ልናደርግ ይገባናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በህዝብ እንደተተፉ የገባቸው አሕባሾች መልካቸውን ቀይረው በአንዳንድ አካባቢዎች በተብሊጎች ስም እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ሰዎችን በኹሩጅ ከሰበሰቡ በኋላ ቀስ በቀስ የራሳቸውን ብልሹ ዐቂዳ ለማስረግ እየተጉ ነው፡፡
ስለሆነም ነገ አላህ ፊት ከመጠየቃችን በፊት ዛሬ ፈጥነን ነገሮችን በሚገባ ማጤን እና ዙሪያ ገባችንን ማስተዋል የግድ ይለናል፡፡ በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች በሚገኙ የተለያዩ የቁርኣን የሒፍዝ ማእከላት ልጆቻችሁን ያስገባችሁ ወላጆች ሁሉ፡ ነገ አላህ ፊት ከመጠየቃችሁ በፊት፣ የልጆቻችሁንም ዘላለማዊ ህይወት ከማበላሸታችሁ በፊት ከወዲሁ አስፈላጊውን እርምጃ ውሰዱ፣ ያስገባችሁበትን መርከዝ ምንነት በሚገባ አስረግጡ፡፡ ያለበለዚያ ነገ ብዙ መስዋእትነት ያስከፍለናል፡፡ ከዚያ በላይ ግን ለዘላለማዊ ፀፀት ይጥለናል፡፡ ከዐርሹ በላይ ያለው ጌታችን እንዲህ ይለናል፡-
)يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنْفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا وَقُودُهَا النَّاسُ وَالْحِجَارَةُ عَلَيْهَا مَلَائِكَةٌ غِلَاظٌ شِدَادٌ لَا يَعْصُونَ اللَّهَ مَا أَمَرَهُمْ وَيَفْعَلُونَ مَا يُؤْمَرُونَ( (التحريم: 6)
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን መቀጣጠያዋ ሰዎችና ደንጋዮች ከሆነችዋ (የጀሀነም) እሳት ጠብቁ፡፡ በርሷ ላይ ጨካኞች፣ ሃይለኞች የሆኑ መላእክት አልሉ፡፡ አላህን ያዘዛቸውን ነገር (በመጣስ) አያምፁትም፡፡ የሚታዘዙትንም ሁሉ ይሰራሉ፡፡” [አትተሕሪም፡ 6]
ነብዩም ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡-
(كُلُّكُمْ رَاعٍ وَكُلُّكُمْ مَسْؤول عَنْ رَعِيَّتِهِ، الإِمَامُ رَاعٍ وَمَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ، وَالرَّجُلُ رَاعٍ فِي أَهْلِهِ وَهُوَ مَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ، وَالْمَرْأَةُ رَاعِيَةٌ فِي بَيْتِ زَوْجِهَا وَمَسْؤولَةٌ عَنْ رَعِيَّتِهَا، وَالْخَادِمُ رَاعٍ فِي مَالِ سَيِّدِهِ ومَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ، -قَالَ: وَحَسِبْتُ أَنْ قَدْ قَالَ: وَالرَّجُلُ رَاعٍ فِي مَالِ أَبِيهِ وَمَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ- وَكُلُّكُمْ رَاعٍ وَمَسْؤولٌ عَنْ رَعِيَّتِهِ) رواه البخاري ومسلم
“ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፡፡ ሁላችሁም ስለ እረኝነታችሁ (ስለ ሃላፊነታችሁ) ተጠያቂ ናችሁ፡፡ መሪ እረኛ ነው፤ ስለ እረኝነቱም ተጠያቂ ነው፡፡ ወንዱ (ባል) በቤተሰቡ ላይ እረኛ ነው፤ ስለ እረኝነቱም ተጠያቂ ነው፡፡ ሴቷም በባሏ ቤት ውስጥ እረኛ ነች፤ ስለ እረኝነቷም ተጠያቂ ነች፡፡ አገልጋይም በአለቃው ንብረት ላይ ተጠያቂ ነው፤ ስለ እረኝነቱም ተጠያቂ ነው፡፡ ‘አንድ ሰው በአባቱ ንብረት ላይ ተጠያቂ ነው፤ ስለ እረኝነቱም ተጠያቂ ነው’ ያሉም ይመስለኛል ይላል ዘጋቢው፡፡ ሁላችሁም እረኞች ናችሁ፡፡ ሁላችሁም ስለ እረኝነታችሁ ተጠያቂ ናችሁ፡፡” [ቡኻሪና ሙስሊም]
ስለዚህ ከተጠያቂነት ለመዳን፣ እራሳችንን እና ወገናችንን ለማትረፍ ሃላፊነታችንን እንወጣ፡፡ ወገን ለወገኑ ደራሽ ነው፡፡ አላህ በዲናችን የመጣውን ፈተና ያንሳልን፡፡ የተሻለውንም ይምረጥልን፡፡ ኣሚን፡፡ ይህን መልእክት በሰፊው በማሰራጨት የምንችላትን እናድርግ፡፡ የአላህ ፈቃዱ ከሆነ የሚጠቀምበት ሰው ይኖራል፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ ነሀሴ 29/2007)

Post a Comment

0 Comments