‹‹የአላህ ያለህ፣ የነቢ ያለህ፣ በአላህ በነቢ››
ይሄ እኮ ነው ሽርክና ኩፍር ማለት፡፡
ይሄ እኮ ነው ሽርክና ኩፍር ማለት፡፡
‹‹የነቢ ያለህ›› ማለት (ያ ነቢ) ብሎ እሳቸውን (እርዳታ ፍለጋ) መጥራት ሲሆን፣ በነቢ ማለት ደግሞ በአላህ ብቻ ተብሎ የሚለመነውን በነቢ ብሎ ለእሷቸው የአላህን መብት አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ታላቁ ሽርክ ነው፡፡
ሰዎች አደጋ ሲያጋጥማቸው በተለይ ከአላህ ጋር ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹ያአላህ ያለህ የነቢ ያለህ›› ብለው አጋር ወይንም ሸሪካ አድርገው ይጠራሉ ይሄ ሽርክ ነው፡፡
ሰውን ሲለምኑ ደግሞ ‹‹በአላህ›› ብቻ ማለት ሲገባቸው አሁንም ‹‹በአላህ በነቢ››፣ አንዳንዶች እንዲያውም በአላህ ሳይሉ ‹‹በነቢ›› ብቻ በማለት ታላቁን ሽርክ ይፈፅማሉ፡፡
አማኞች ሱረቱል ፋቲሃ ላይ ቃል የሚገቡት እንዲህ ሲሉ ነው
إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን (እናመልካለን)፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
إِيَّاكَ نَعْبُدُ وَإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ
አንተን ብቻ እንግገዛለን (እናመልካለን)፤ አንተንም ብቻ እርዳታን እንለምናለን፡፡
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ለአብደላህ ኢብን አባስ (ረድየላሁ አንሁም) እንዲህ ብለውታል ‹‹ስትጠይቅ (ስትለምን) አላህን ብቻ ጠይቅ (ለምን)፣ ስትታገዝ በአላህ ብቻ ታገዝ፡፡››
አንተን ብቻ የሚሉት ይሰመርባቸው፡፡ እርዳታም አላህን ብቻ መጠየቅ፣ አላህን ብቻ ማምለክ ዋጂብ (ግዴታ) ሲሆን ተውሂድ ይባላል፡፡
የዚህ ተቃራኒው ደግሞ አላህ እርም ያደረገው እርኩስ ተግባር፣ ታላቁ በደል ሽርክ ይባላል፡፡ በአላህ ላይ የሚጋሩት (ደባል፣ ሸሪካ ተደርገው የተያዙት) ምርጡ ፍጡር ነብዩ (ሰለላሁ አይሂ ወሰለም) ቢሆኑም፣ ወይንም የመላእክቶች አለቃ ጂብሪል (አለይሂ ሰላም) እናም ሌሎችም ፍጡራን ቢሆኑ ይህ ተግባር ሽርክ ይባላል፡፡ አላህ ደግሞ ከሸሪካዎች (ከአጋር) የተብቃቃ ነው፡፡
አላህ ሆይ! እውቀትን ጨምርልን ከዚህ እርኩስ ተግባር ሽርክ ጠብቀን፣ የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ትክክለኛ ሱና ተከታይ አድርገን፣ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይሁን በሷሊሆች ላይ ድንበር ከማለፍ አንተው ጠብቀን፡፡
0 Comments