Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹በተውሂድ ስም አታጭበርብሩን››፣ ‹‹በተውሂድ ስም አትከፋፍሉን››፣ ‹‹እኛ ሙስሊሞች ነን ሰለፊ ሱፊ እያላችሁ አትከፋፍሉን››፣ ‹‹የሙስሊሙ ጉዳይ መቼ ያስጨንቃቸዋል?››


‹‹በተውሂድ ስም አታጭበርብሩን››፣
‹‹በተውሂድ ስም አትከፋፍሉን››፣
‹‹እኛ ሙስሊሞች ነን ሰለፊ ሱፊ እያላችሁ አትከፋፍሉን››፣
‹‹የሙስሊሙ ጉዳይ መቼ ያስጨንቃቸዋል?››
ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን ከላይ ያነበባችሁትን አባባል ከስሜት ተከታዬችና ካላዋቂዎች ሲባልና ሲፃፍ እያየን ነው፡፡
እነዚህን እና መሰል አባባሎችን የሚናገሩት ምን ሲባሉ ይሆን ? ...
1) “ከሽርክና ከቢድዓ እንራቅ፣ ይሄ ሽርክ ነው፣ ይሄ ቢድዓ ነው፣ መውሊድ የሽርክ መናሃርያ ነው፣ ጠዋፍ ለአላህ ብቻ ነው የሚገባው ለኑርሁሴን ቀብር አይገባም፣ ሱጁድ ለአላህ ብቻ እንጂ ለቃጥባሬ ቀብር አይገባም፡፡ ሲባሉ ...
እነሱ ጥፋታቸውን እንዳያስተካክሉ ወይንም በስራቸው ያለ ሽርክና ቢድዐ ላይ የወደቀ ብዙ ሰው እንዳይስተካከል ከእውቀታቸው ማነስ ወይንም ስሜታቸውን ከመከተል የተነሳ የሚከተሉት ይላሉ ...
‹‹በተውሂድ ስም አታጭበርብሩን››
መልስ :– «አላህን በብቸኝነት እናምልክ፣ ሽርክን እንራቅ፣ ሱናን እንከተል፣ ቢድዓን እንራቅ» ማለት ማጭበርበር ከሆነ ነብያትን ሁሉ በተለይ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምን) ምን ሊሏቸው ይሆን?
2) «አንድነታችን በተውሂድና ሱና ላይ ይሁን፣ ሽርክንና ቢድዓን እንራቅ፣ ሃቅ አንድ ብቻ ናትና እሷን ብቻ እንከተል፣ እሷም ነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና ሰሃባዎቻቸው የነበሩበት መንገድ::
እነ ሱፊ፣ ሺዓ፣ አህባሽ፣ ኢኽዋን 1ዷን ሃቅ ተቃርነው የመጡ አዲስ የጥመት ቡድኖች ናቸው፡፡ ስለዚህ መጤውን “ለምን ትከፋፍላለህ የድሮው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለምና) የሰሀባዎችን መንገድ አይበቃህምን?” ብለው ይጠይቁት እንጂ የድሮውን የሰለፉነ ሷሊሂን 1 ሀቅ ብቻ እንከተል የሚለውን ለምን ተጠያቂ ያደርጉታል?
- አንድ ሰው “ሰለፊ ነኝ” ሲል እኔ ሙስሊም ነኝ ቁርዓንና ሀዲስን በሰለፉነ ሷሊሂን መንገድ የምረዳ በእስልምና ውስጥ ከመጡ የጥመት መንገዶች ሁሉ (ከኸዋሪጁ፣ ሺዓው፣ ሱፊው.....) እራሴን አጠራለሁ እያለ ነው፡፡ የጥንቱን 1 ሃቅ ብቻ ነው። የምከተለው መጤ ቡድኖችን በጠቅላላ እቃወማለሁ የሚለውን ሰው ‘መጤ ቡድኖችን ዝም በል! አለበለዚያ ከፋፋይ ነህ!’ ብሎ ስም ለማጥፋት መሞከሩ ሞኝነት ነው፡፡
- ደግሞ ሃቅና ባጢል አንድ ሊሆኑ አይችልም፡፡ ቁርዓንም ስሙ «ፉርቃን» ነው ሃቅን ከባጢል የሚለይ፡፡ ታድያ ተውሂድና ሽርክን ቀላቅሎ ለመሄድ ከሚሞክር የበለጠ ማን በታታኝ አለ?
- ሌላው አላህ በሃቅ ላይ ተሰባሰቡ አለን እንጂ ‹‹አላህ ሁሉ ቦታ ነው››፣ ‹‹የአላህ መልክተኛ ሆይ! እርዱን››፣ ‹‹የቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ››፣ ‹‹አባድር ፆም አያሳድር›› የሚሉትን ሱፈዬች ‹‹1 ነን›› በሉ አላለም፡፡ ይልቁንስ የሙስሊሞች ጉዳይ ካሳሰባቸው ሙስሊሞችን ከእምነታቸው አስፈንጥሮ የሚያወጣቸውን ታላቅ ሽርክ ሲሰሩ ከምንም በፊት ማስጠንቀቅ፣ ማስተማር ነው፡፡
3) «ኢስላማዊ ድራማና ፊልም እያላችሁ ወጣቱን አታዳክሙት፡፡ ቁርዓንና ሱና ያልገሰፀውን ትውልድ ድራማ አይለውጠውም፡፡ ነሺዳ ከምትሉ ወጣቱ ቁርዓን ይቅራበት» እና የመሳሰሉትን ሲባሉ የሚከተለውን ይላሉ ...
‹‹መቼ ይሆን የሙስሊሞች ጉዳይ የሚያሳስባቸው ሁሌ ጭቅጭቅ?›› እና የመሳሰሉትን ...
መልስ :–
- የሙስሊሞች ጉዳይ የማያሳስበው በዲን ስም መጥፎ ተግባርን የሚያስፋፋው ነው አላህ ሙናፊቆችን አስመልክቶ እንዲህ ይላል
አላህ ከኒፋቅ ይጠብቀን
ﻭَﺇِﺫَﺍ ﻗِﻴﻞَ ﻟَﻬُﻢْ ﻟَﺎ ﺗُﻔْﺴِﺪُﻭﺍ۟ ﻓِﻰ ﭐﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻗَﺎﻟُﻮٓﺍ۟ ﺇِﻧَّﻤَﺎ ﻧَﺤْﻦُ ﻣُﺼْﻠِﺤُﻮﻥَ
{{ለነርሱም «በምድር ላይ አታበላሹ» በተባሉ ጊዜ «እኛ አሳማሪዎች ብቻ ነን» ይላሉ፡፡
ﺃَﻟَﺎٓ ﺇِﻧَّﻬُﻢْ ﻫُﻢُ ﭐﻟْﻤُﻔْﺴِﺪُﻭﻥَ ﻭَﻟَٰﻜِﻦ ﻟَّﺎ ﻳَﺸْﻌُﺮُﻭﻥَ
ንቁ እነርሱ አጥፊዎቹ እነሱው ናቸው፤ ግን አያውቁም፡፡ }} [በቀራህ 11–12]
ታድያ ማን ይሆን የሽርክ መናሀርያውን መውሊድንና የአላህ ስምና ባህርያትን ቀላል ነገሮች አድርጎ ዘሏቸው በዲን ስም ሌላ አጀንዳ የሚያራግበው?
- ታድያ ማን ነው ይህን የኩፍር አባባል ‹‹አላህ ሁሉ ቦታ ነው›› የሚሉትን ሱፍዬች ጥሩ አድርጎ ለማህበረሰቡ ለማስተዋወቅ እየሞከረ ያለው?
ግርም የሚለው ግን ማህበረሰቡ ውስጥ ያለው ሽርክ በማስረጃ ሲነገርና መፈናፈኛ ሲያጡ እንዲህ ይላሉ ..
- ‹‹ባለማወቅ እኮ ነው የሚሰሩት›› የእኛ ጥያቄ፣ ታድያ ሽርክ ላይ ለወደቀ ሰው ስለሌላ አርስት ከማስተማር በፊት የሚቀደመው ሃይማኖቱን ጠንቅቆ እንዲያውቅ፣ ስራዎችን ሁሉ ከሚያበላሸው ከሽርክ እንዲርቅና ተውሂድንና ሱናን በሰለፎች አረዳድ አጥብቆ እንዲይዝ ነውን ወይንስ አይደለም?
- ሌላው አባባላቸው ‹‹እኛ ተውሂድ ከማስተማራቸው ችግር የለብንም ግን ሂክማ የላቸውም››
የእኛ ጥያቄ .. ታላቁ የሒክማ ባለቤት ጠቢቡ ሉቅማን ልጁን ሲመክረው ከምንም በፊት ‹‹ልጄ ሆይ! በአላህ ላይ አታጋራ፡፡ በአላህ ላይ ማጋራት ታላቁ በደል ነው›› ነበር ያለው ታድያ እነሱ ከነብያትና ከሷሊሆች በላይ ሂክማ ኖሯቸው ነውን?
- ሌላው ሂክማ ይጎድላል ያለ ሽርክና ቢድዐ የተንሰራፋበት ማህበረሰብ ውስጥ ጥጉን ይዞ ተቀምጦ ወይንም አንገብጋቢውን የተውሂድ አጀንዳ ትቶ ሌላ አርስት ውስጥ መግባት ሳይሆን ሌሎች ይጎድላቸዋል ያለውን ሂክማ ሸሪዐው በሚለው መንገድ ለምን አስተምሮ አያሳይም?
አላህ ሆይ!
1) እውቀትን ጨምርልን፣ ባወቅነውም የምንሰራ አድርገን
2) ከሽርክና ቢድዓ ጠብቀህ፣ በተውሂድና ሱና መንገድ ላይ አፅናን
3) የእውነት የሆነች መዋደድን፣ መተሳሰብን፣ አንድነትን ስጠን ሰላትና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፣ በቤተሰቦቻቸው፣ በባልደረባዎቻቸው፣ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Post a Comment

0 Comments