Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አሕባሽ ቆርጦ ቀጥል!


አሕባሽ ቆርጦ ቀጥል!
አንድ በውሸት ሱስ የተለከፈ ‘እፍʼ ያለ ውሸታም “እንዳው በህይወትህ እውነት ተናግረህ ታውቃለህ?” ተብሎ ቢጠየቅ “እውነት እንዳልናገር ፈራሁ እንጂ ‘አዎʼ እል ነበር” አለ የሚል አባባል ማንበቤን አስታውሳለሁ፡፡
ነቢዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላሉ፡ “አደራ ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል፤ ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል፡፡ አንድ ሰው ሲዋሽና ውሸትም ላይ ሲያተኩር አላህ ዘንድ ውሸታም ተብሎ ይመዘገባል…፡፡”
እውነተኛ ሀይማኖት በውሸት አይታገዝም፡፡ እውነተኛ የዲን ሰዎችም ውሸት መታወቂያቸው እስከሚሆን ድረስ ይዘቅጣሉ ብሎ ማንም አያስብም፡፡ እውነት ወዳጅ የሆነም ለውሸታም አይሟገትም፣ ምናልባት እሱ እራሱ የውሸት ደቀ-መዝሙራቸው ካልሆነ በቀር፡፡ እርግጥ ነው በውሸት የሚነግድ “ሀይማኖተኛ” እጅግ ይገርማል፡፡ ነገር ግን ውሸትን የእምነቱ ክፍል የሚያደርግ የሀይማኖት ቡድን ብታገኙ ምን ትላላችሁ? እኔ በራሴ ግርምቴን የምገልፅበት ቃል አይኖረኝም፡፡ እስኪ በውሸት የሚገኘውን “ጀነት” አስቡት!!! ግን ግን በዐለም ላይ ውሸትን የእምነቱ ክፍል ያደረገ እምነት እንዳለ ቢሰሙ ምን ይላሉ? ይሄ ቡድን “ሙስሊም አይዋሽም” ያሉትን ነቢይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንደሱ የሚከተል እንደሌለ ቢነግረዎትስ ምን ይሰማዎታል? እንዲህ አይነት አንጃ እንደማይኖር ማንም ቢሆን እርግጠኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን የሺዐዎችን እምነት ከወሬ ባለፈ በመረጃ ሲያረጋግጥ ግን እርገጠኝነቱ መና ይቀራል፡፡ ሺዐዎች ውሸትን ይፈቅዳሉ ብትሉ አልተሳሳታችሁ ይሆናል፡፡ ነገርግን እነሱ ጋር ያለውን በትክክል አይገልፀውም፡፡ ለምን ቢሉ እነሱ የሚሉት በውሸት ላይ ያለንን እምነት ያልተቀበለ ከኛ አይደለም ነውና፡፡ የሚጠራጠር ካለ ብዙሃኑ ሺዐዎች ቡኻሪ እኛ ዘንድ ያለውን አይነት ደረጃ የሚሰጡትን “አልካፊ” የሚባለውንና ሌሎችንም ኪታቦቻቸውን ይመልከት፡፡
ለጊዜው ግን ማውራት የፈለግኩት ስለሺዐዎች አይደለም፡፡ ከሺዐዎች በርካታ ጥፋቶችን ስለኮረጁት አሕባሾች እንጂ፡፡ ከነዚህ ጥፋቶች ውስጥ ለጊዜው የመረጥኩት የውሸት ጉዳይ ነው፡፡ ደግሞ እነሱም ጋር ይሄ ችግር አለ እንዴ? በደንብ አለ፡፡ ባይሆን የደረጃ ልዩነት እንዳለ አምናለሁ፡፡ የቡድኑ መሪ ዐብደላህ አልሀረሪ “ቡግየቱጣሊብ” በተሰኘው ኪታቡ ላይ ከሐራም ለማምለጥ ሲባል አጉል ቅጥፈትን መጠቀምን ፈቅዷል፡፡ ሰውየው ሐራም የሆኑ ነገሮችን ለመፍቀድ፣ ሐላል የሆኑትን ለመከልከል አልፎም በተለይ በተለይ ተቃዋሚዎቹን ለማውገዝ የሚያዘንባቸውን የውሸት ዶፎች ያስተዋለ ሁሉ -ይቅርታ ጭፍን አድናቂዎቹን አይጨምርም- ይዘገንነዋል፡፡ ስራዎቹ በአብዛሀኛው በውሸት የታጨቁ ናቸው፡፡ ነገር ግን ዳጎስ ያሉ የውሸት ክምሮቹን መመልከት የፈለገ ኢብኑ ተይሚያን ለመወንጀል ሲል የከተበውን “መቃላቱሱኒያ” እና “መውሊዱነቢይ” የሚሉትን ኪታቦቹን ይመልከት፡፡ ሁለት ታላላቅ የውሸት ቁልሎችን ያገኛል፡፡ እስኪ ለናሙና ያህል ጥቂት ውሸቶቻቸውን እንይ
1. “‘አላህ ከዐርሹ በላይ ነውʼ የሚሉት ወሃቢዮች ናቸው ሙጀሲማዎች ሙሸቢሀዎች! በዚህም ሳቢያ የአይሁድና የክርስቲያን እምነቶችን ተከትለዋል” አሉ፡፡ እውነታቸውን ነው? ኢብኑ ዐባስ ሙጃሂድ… አላህ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ መግለፃቸው ቡኻሪ ላይ ተዘግቧል፡፡ ወሃቢዮች ይሆኑ?
2. ኢብኑ ተይሚያ ለዐልይ ጥላቻ እንዳለው አድርጎ ማውራቱ! ይህን የአብደላህ አልሀረሪ ቅጥፈት እራሱ ኢብኑ ተይሚያ ይመልሰው፡ “የዐልይ ታላቅነት፣ የአላህ ወልይ መሆኑን እንዲሁም ደረጃው አላህ ዘንድ ከፍ ያለ መሆኑ የታወቀ ነው፡፡ ይህን የሚመለከት አስተማማኝ መረጃ አለንና ውሸትና ያልተረጋገጡ ዘገባዎችን መጠቀም አይገባም” (ሚንሀጁሱና፡8/165)
3. የዐብደላህ አልሀረሪ ቅጥቅጥ የሆነው ኒዛር ሐለቢ “ኢብኑ ተይሚያ በተለያዩ መዛሂብ ላይ የሚገኙ ሙስሊሞችን በጅምላ የሚያከፍር የስምንተኛው ክ/ዘመን የኸዋሪጆች ቁንጮ ነው” ይላል፡፡ እውነቱን ነው? ኢብኑ ተይሚያ ይጠየቅ፡፡ “እኔ ሁሌም አንድን ሰው ለይቶ ካፊር ወይም አመፀኛ ወይም ወንጀለኛ ማለትን አጥብቀው ከሚከለክሉት ነኝ፣ ይህን አብሮኝ የሚቀመጥ ሁሉ ያውቀዋል፡፡ …” (መጅሙዑል ፈታዋ፡3/229)
የመሪያቸውን የውሸት ወሲያ በመንጋጋቸው ነክሰው የያዙት የኢትየጵያዎቹም አሕባሾች ባደባባይ መዋሸቱን ተያይዘውታል፡፡ እንዴ ህዝብን መዋሸት ይቻላል እንዴ?! እሺ ይሁን፣ ግን ስንቴ?! ሚሊዮኖችን ደግሞ ደጋግሞ መሸወድ ይቻላል?
4. “ስልጠናችን ላይ ምንም ዐይነት ማስገደድ የለም” አሉ፡፡ ስልጠናቸው ላይ የተካፈለው አንድ ሰው ሁለት ሰው ቢሆን ደጋግመው ሲዋሹ እንጠራጠር ነበር፡፡ ግን ለማን ነው የሚዋሸው? ሰልጣኞቹ እኮ የህዝብ ክፍል ናቸው!!
5. “ሙስሊሙን በጅምላ አናከፍርም” አሉ፡፡ በጀማዓ እንደ አዲስ ሸሃዳ ሲያሲዙ አልነበረም? እሄ እኮ ያደባባይ ሚስጢር ከሆነ ሰነባበተ! ምናልባት ካልዋሹ መኖር አይችሉ ከሆነ ተንኮላቸውን የሰሩበትን ህዝብ ለመዋሸት ከመሞከር ለምን ሌላ አገር ሄደው አይዋሹም?!
6. ፣ 6. ፣ 7. …
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ አላህን ፍሩ! ከእውነተኞቹም ሁኑ” ይላል ጌታችን፡፡
ረሒመሁላህ ኢብኑ ተይሚያ “ውሸትን ፈጥሮ የጠላቶቹ መለያ ያደረገው ጌታ ጥራት ይገባው!” ማለቱ ምንኛ የሚደንቅ አባባል ነው፡፡