Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የኢማሙ አህመድ የፈተና ዘመን

የኢማሙ አህመድ የፈተና ዘመን
ኸሊፋዎች:
1, መህድይ
2, ሀዲ
3, ረሺድ
4, አሚን
እነዚህ ኸሊፋዎች በሰለፎች መንገድ ላይ ነበሩ
5, መእሙን
6, ሙእተሲም
7, ዋሲቅ
እነዚህ ፊትናው(ቁርአን መኽሉቅ) የጀመሩትና ሰዎችን ያስሩ፣ ይገርፋ ነበር።
8, አል ሙተወኪል
ሀዘንን አስወገደ፣ ቢድአን አጠፋ፣ ፊትናን አበረደ ረሂመሁሏህ ።

የፊትናው መጀመር ምክኒያት
የፋሪስ ፣ የሮም ፣ ዮናንን ፣ የህንድ መፅሀፎች ወደ አረበኛ መተርጎማቸው እና በዘመኑ የነበረው ኸሊፋ( መእሙን) ለቢደአ አራመጆች መፅሀፉን መስጠቱ።
ከአባሲዮች ኸሊፋ ፊትናው የጀመረው መእሙን ነው።
የፊትናው ዋና መሪ አህመድ ኢብኑ ዱአድ
ፊትናው የጀመረበት አመት 218 አ•ሂ
ቁርአን መኽሉቅ አይደለም የአላህ ንግግር ነው የሚሉ ሰዎች( አሊሞች) የሚቀጡት የቀጣት አይነት:
# በእስር
# በማስቸገር
# ከስራ ማባረር
# ከበይተልማል የሚገባቸውን(ሀቅ)መከልከል
በፊትናው ዘመን የነበሩ ታዋቂ አሊሞች
1, መሀመድ ሰኢድ
2, የህያ ኢብኑ መኢን
3, አቡ ኸይሰማ
4, አቡ ሙስሊም
5, ኢስማኢል ኢብኑ ዳውድ
6, አህመድ አደውረቅይ
7, ኢብኑ አቢ መስኡድ
እዚህ ሰይፍ በመፍራት የተቀበሉ ታላቅ አሊሞች ናቸው ። ረሂመሁምሏህ
ኢማሙ አህመድ እንድህ አሉ : " እነዚህ የአገሪቱስመጠር ታወቂ አሊሞች ናቸው በአቋማቸው ቢፀኑ ነገሩ ይቋጭ ነበር እሱ ወደ ኋላ ተመለሱ። ሰውዬው(መእሙ) ሲያስጠ ነቅቃቸው( ሲያስገድዳቸው)
8, ኢማሙ አህመድ
9, መሀመድ ኢብኑ ኑህ
10, ኡበይዱሏህ ኢብኑ ኡመር አልቀዋሪሪይ
11, አል ሀሰን ኢብኑ አሰጃዳህ
እነዚህ አንቀበልም ቁርአን የአላህ ነግግር ነው ብለው በአቋማቸው ፀኑ። ታሰሩ ሰጃዳህ እና ቀዋሪሪይ ሲቀሩ በኋላ ከአቋማቸው ተመለሱ የአሚሩን ትዛዝ ተቀበሉ። ረሂመሁምሏህ።
ኢማሙ አህመድ እና መሀመድ ኢብኑ ኑህ አንቀበልበም ቁርአን የላህን ግግር በማለት አስከ መጨረሻው በአቋማቸው ፀኑ። ታስረው ወደ መእሙን ተወሰዱ።
ኢማሙ አህመድ: የመእሙንን ፊት እንዳታሳዬኝ እያሉ ዱአ ያደርጉ ነበር (ሪቃ )የሚባል ቦታ ሲደረሱ የመእሙን ሞት ሰሙ። ወደ በግዳድ ተመለሱ በመንገድ ለይ እያሉ መሀመድ ኢብኑ ኑህ ሞተ ረሂመሁሏህ ኢማሙ አህመድ ሰገዱበት ቀበሩትም። በኢማሙ አህመድ ላይ የሚወሰደው እርምጃ በሙእተሲም የኺላፋ ዘመንም ቀጠለአ( 218 )አ, ሂ ። ኢማሙ አህመድ ረሂመሁሏህ ይደበደቡ ነበር እጃቸው እስከ ሚወልቅ ድረስ። ከገራፊዎቹ አንዱ "ኢማሙ አህመድን 80 ግዜ ገረፍኩት፣ ዝሆን እንድህ ተደርጎ ቢገረፍ ይወድቅ ነበር ። ኢማሙ አህመድ ለ 28 (30) ወራት ያክል የተለያዩ ችግሮችን በትግስት እያለፈ እየተወያያ ቁይቷል አለ ፣ ተከራካሪዎቹን ዝም ያስብላል በጠንካራ ማስረጃ ፣ በጠንካራ እምነቱ እና በሀቅ ላይ በመፅናቱ። በ 221 አ• ሂ በረመዳን ወር ከ2 አመት ከ4 ወር የእስር ቤት ቆይታ በኋላ ተፈቱ ። ከድብደባው ህመም ካገገሙ በኋላ : ማስተማር ፣ ፈትዋ፣ ጀምአ እና ጁምአ ጀመሩ ። ሙእተሲም እስከ ሚሞት ድረስ (227)። በ231 ዋሲቅ የሚባለው ኸሊፋ ማስተማር ፣ ጀምአ እና ጁምአ ከለከለው። ኢማሙ አህመድም እንድህ አሉ "በችግረም ፣በሰላምም፣ በሚያአስቸግሩንም ፣ በሚአስደስቱንም አሚሮችን መታዘዝ እዳለብኝ አለብኝ ይሉ ነበር። ከሶላተተል ጀምአ እና ጁምአ እንድሁም ከማስተማር በመታገዴ ባዝንም። ረሂመሁሏህ 232 አ• ሂ አልሙተወኪል ኸሊፋ ሆነ።
# አለህ ሀዘንን አስወገደ
# ሱና ግልፅ ሆነ
# ቢድአ ጠፋ (ተወገደ)
# ፊትናውም ቆመ።
ኢማሙ አህመድን አከበረው ፣አቀረበው፣ ማንንም አይሾምም ኢማሙ አህመድን ያማከረ ቢሆን እንጅ ።
ቢሽር ኢብኑ ሀረስ አንድህ አለ: " ኢማሙ አህመድ እሳት ወናፍ ውስጥ ገባ ቀይ ወረቅ ሆኖ ወጣ።"
ኢብኑ መደንይ: በሪዳ ዘመን አላህ ዲንን በሲድቅ( አቡበክር ሲዲቅ) ከፍ አደረገው።
በፊትናው ዘመን በኢማሙ አህመድ።"
መይሙንይ እንድህ አለ: " አልይ ኢብኑ መደንይ እንድህ አለኝ ማንም ለእስልምና የቆመ የለም ኢማሙ አህመድ አንደቆመው! በንግግሩ በጣም ተገረምኩና ወደ አቢ ኡበይድ አልቃሲም ኢብኑ ሰላም ሂድኩኝ ኢብኑ መደንይ ያለኝን ነገርኩት እወነቱን ነው አለኝ አቡበከር በሪዳው ዘመን ከጎኑ የቆሙ ረዳቶች ነበሩት። ለኢማሙ አህመድ አንድም ከጎኑ የቆመ ረዳት አልነበረውም ። በኢስላም ታሪክ እሱ የሚመስል አለውቅም"
ምንጭ( አልሚህነቱ ወአሳሩሀ ፊ ሚንሀጂ ኢማሙ አህመድ)
ከአረበኛ ፊስቡክ ላይ የተወሰደ።

Post a Comment

0 Comments