Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከዒድ ሰላት ብይኖች

🌹أحكام صلاة العيد 🌹
ከዒድ ሰላት ብይኖች
በሸይኽ ዐብዱል አዚዝ ቢን ዐብደላህ ኢብኑ ባዝ [ረሂመሁሏህ] 001
=================

1⃣ ሴቶች ለዒድ ሰላት በመስገጃ ስፍራው መገኘታቸው እንዴት ይሆን ?
«ሴቶች በዒድ ሰላት መስገጃ ስፍራ ሒጃባቸውን ጠብቀው በሽቶ እና በመሳሰሉት ሳይጋጌጡ ስርኣታቸውን ጠብቀው መገኘታቸው ሱና ነውና ይፈቀድላቸዋል።»
📔 مجموع فتاوى ابن باز رحمه الله ( 13 / 7 )
2⃣ የዒድ ሰላትን ወጣ ባሉ ገጠራማና በየሸለቆው መስገድስ ?
«የዒድ ሰላት የሚሰገደው በየከተሞችና ሰዎች በሚኖሩበት መንደር ነው። መንገደኛ ሆነውም ሆነ ወጣ ባሉ ባዶ ገጠራማ ስፍራዎች አይሰገድም። ከአላህ መልዕክተኛ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] የመጣልን ሱንናም በዚሁ መልኩ ነው።
ከአላህ መልዕክተኛ [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ሆነ አላህ መልካም ስራዎቻቸውን ይውደድላቸውና ከባልደረቦቹም በየሸለቆው ሰው በማይኖርበት ገጠራማ ስፍራ ሆነ በጉዞ ላይ ሳሉ የዒድን ሰላት መስገዳቸው አልተዘገበም።»
📔 مجموع فتاوى ابن باز ( 13 / 9 )
3⃣ የዒድን ሰላት ለመስገድ መነሻ መስፈርት የሚሆነው የሰጋጁ ብዛት ምን ይሆን ?
«ትክክለኛው የሊቃውንት ንግግር የሆነው ለጁምዓ ሰላትም ሆነ ለዒድ ሰላት አነስተኛው የሰው ቁጥር ሶስትና ከዚያ በላይ ነው። ከዚህ ውጪ መነሻው የሰው ብዛት 40 ሰው መሆን አለበት የሚለው አባባል ሊመረኮዙበት የሚገባው ትክክለኛ የሆነ የመረጃ መሰረት የለውም።»
📔 المصدر ، مجموع فتاوى ابن باز رحمه الله ( 12 / 13 )
4⃣ ለዒድ ሰላት መስገጃው ቦታ የመጣ ሰው ምን ይተግብር ?
«የዒድን ሰላት ለመስገጅ መስገጃው ስፍራ ለመጣ ሰው የተደነገገው ሰላቱ እስኪሰገድ ድረስ በታህሊልና በተክቢር (ላኢላሃ ኢለላህ እና አላሁ አክበር ያለባቸውን ዚክሮች በማለት) ሰላቱን መጠበቅ ነው።
የእለቱ ልዩ መገለጫም ይኸው ነው። የዒዱ እለት ኹጥባ እስኪያበቃም በመስጂዶችም ይሁን ከዚያ ውጭ የሚደረገው ይኸው ነው።»
📔 المصدر: مجموع فتاوى ابن باز رحمه الله ( 14 / 13 )
5⃣ በጀማዓ ተክቢር ማድረግን የሚቃወምስ ምን ይሆን ብይኑ ?
«ቢድዓ ወይም ፈጠራዊ የሆነው በህብረት የተክቢር አደራረግ ተክቢራውን ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ሰዎች በጋራ እኩል ጀምረው እኩል የሚያበቁበት ልዩ የሆነ የተክቢር አደራረግ ነው። ይህ ተግባር መሰረት የሌለው መረጃ ቢስ በመሆኑ ፈጠራና አላህ በዚህ መልኩ እንዲደረግ መብት ሳይሰጥ የተፈጠረ ነው።
የአላህ መልእክተኛ [ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም]
ﻟﻘﻮﻟﻪ ﺻﻠﻰ اﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﻭﺳﻠﻢ: «ﻣﻦ ﻋﻤﻞ ﻋﻤﻼ ﻟﻴﺲ ﻋﻠﻴﻪ ﺃﻣﺮﻧﺎ ﻓﻬﻮ ﺭﺩ »
" የኛ ትእዛዝ የሌለበትን ተግባር (ሃይማኖታዊ ተግባር) የፈፀመ ወደራሱ ተመላሽ ነው (ያልተደነገገ ነውና ተቀባይነት የለውም)።" ብለዋልና ይህንን የተቃወመ ደግሞ ትክክለኛ ነው።»
📔 المصدر: مجموع فتاوى ابن باز رحمه الله ( 13 / 21 )
=================
www.fb.com/tenbihat
🎐ረመዷን 27/1436
ጁላይ 14/2015

Post a Comment

0 Comments