Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ዘካተል ፊጥርን በብር ማውጣት በላጭ ነው" ብሎ ለሞገተ ሰው የሼይኽ አል-አልባኒ ምላሽ




"ዘካተል ፊጥርን በብር ማውጣት በላጭ ነው" ብሎ ለሞገተ ሰው የሼይኽ አል-አልባኒ ምላሽ።
______________________________
ሼኽ አል-አልባኒ እንዲህ አሉ:
አንድ ሰው መጥቶ "አይ!!! በብር ቢሰጥኮ ለድሃ የበለጠ ጠቃሚ ነው።" ቢል ሁለት ስሕተቶችን እየተሳሳተ ነው።
አንደኛው:
ሸሪዓው የደነገገዉን ተጣረሰ። ምክንያቱም ጉዳዩ አምልኮ ነውና። በጥቂቱ ይህ ነው የሚባለው (ማለትም ከሸሪዓ ጋር ተጣርሷል።)
ሁለተኛ ግን አደገኛ ነው።
ምክንያቱም ጥበበኛው ደንጋጊ (ማለትም አላህ ሱብሓነሁ ወተዓላ) ለመልእክተኛው (ዓለይሂ አሰላቱ ወሰላም) ኡመቱን አንድ ቁና እንዲያወጡ ብሎ ሲያዝ ለድሃውና ለምስኪኑ የሚጠቅመውን ነገር አላወቀም ነበረ ልክ ይህ ሰው የሚጠቅማቸውን እንዳወቀ ሁላ።
ሲልሲሉቱ አል ሁዳ ወልኑር። ካሴት ቁ.274 ደቂቃ 12:18

Abu Meryem Sami AlJeberti

Post a Comment

0 Comments