Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የዑምራ አፈፃፀም ስርዓት

የዑምራ አፈፃፀም ስርዓት

የዑምራ አፈፃፀም ስርዓት
1. ወደ ሚቃት በምትደርስበት ጊዜ እራስህን ማፅዳት፣ መታጠብ እና ከኢሕራም ልብስህ ውጪ አካልህን ሽቶ መቀባት ሱና ይሆንልሀል፡፡ በመቀጠልም የኢሕራም ልብስህን ሽርጥና ኩታህን (ሽርጥህን በማሸረጥ ኩታህን በማጣፋት) ልበስ።(የኢሕራም ልብሶችህን በተመለከተ)የተሻለ የሚሆነው ሁለቱም ነጭ መሆናቸው ነው፡፡ ሴት ልጅን በተመለከተ እስካልተገላለጠች፣ ከወንዶች እና ከካፊሮች ጋር በአለባበስ እስካልተመሳሰለች የፈለገችውን ልብስ ትለብሳለች፡፡ ከዚህ በኋላ ለዑምራ
لبيك عمرة
لَبَّيْكَ اللَّهُمَّ لَبَّيْكَ لَبَّيْكَ لاَشَرِيكَلَكَ لَبَّيْكَ إِنَّ الْحَمْدَ وَالنِّعْمَةَ لَكَ وَالْمُلْكَ لاَشَرِيكَ لَكَ
“ለበይከ ዑምረተን”
“ለበይክ አላሁመ ለበይክ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢነልሀምደ ወኒዕመተ ለከ ወልሙልክ ላ ሸሪከ ለክ” በማለት ኒያ (ኢሕራም) ታደርጋለህ፡፡
ትርጉሙም፦ «አቤት አላህ ሆይ!አሁንም አቤት የዑምራን ስርአት ለመፈፀም(ተዘጋጅቻልሁ)። አቤት አላህ ሆይ! አሁንም አቤት ለአንተ አጋር የለህም። ምስጋና፣ፀጋና ንግስናም ለአንተ ነው። አጋር የለህም።» (ቡኻሪ እና ሙስሊም የዘገቡት)
ከዚህ በላይ የተጠቀሰውን (ተልቢያን) በማለት ላይ ወንዶች ድምፃቸውን ከፍ ሲያደርጉ ሴቶች ግን ድምፃቸውን ከፍ አያደርጉም፡፡ ኒያን ካደረግክበት ሰዓት አንስቶም ተልቢያውን ሌሎች ዚክሮችን እና አላህን ምህረት መጠየቅን (እስቲግፋርን) ታበዛለህ፡፡
2. መካ በምትደርስበትም ወቅት ከሀጀረል-አስወድ ጀምረህ “አላሁ አክበር” በማለት በካዕባ ዙሪያ ሰባት ዙር ጠዋፍ አድርግ፡፡ በዚህም ወቅት አላህን ማውሳት እንዲሁም ከተደነገጉ የዚክር እና የዱዓእ አይነቶች በፈለግከው እርሱን መለመን ትችላለህ፡፡ በሩክነል የማኒ እና በሀጀረል-አስወድ መካከል ስትሆን የሚከተለውን ማለትህ (ዱዓእ ማድረግህ) ሱንና ነው። 
رَبَّنَا آتِنَا فِي الدُّنْيَا حَسَنَةً وَفِي الْآخِرَةِ حَسَنَةً وَقِنَا عَذَابَ النَّارِ
“ረበና አቲና ፊዱንያ ሀሰነተን ወፊል አኺረቲ ሐሰነተን ወቂና ዓዛበ-ንናር” 
ትርጉሙም፡- «ጌታችን ሆይ! በምድረ ዓለም ደግን ነገር (ጸጋን) በመጨረሻይቱም አገር ደግን ነገር (ገነትን) ስጠን፤ የእሳትንም ቅጣት ጠብቀን» {አል-በቀራ፡201}
ከዚህ በኋላ ከተመቸ እርቀት ላይ ብትሆን እንኳ ከመቃመ-ኢብራሂም ኋላ፣ካልሆነም በመስጂዱውስጥ በማንኛውም ስፍራ (ሁለት ረከዓ) ትሰግዳለህ፡፡
በዚህኛው ጠዋፍ ለወንድ ልጅ ኢድጢባዕ (ማለትም የኩታውን መሀል በቀኝ እጁ ብብት ስር፤ ጫፎቹን ደግሞ በማጣፋት ግራ ትከሻው ላይ ማድረግ) እንዲሁም በጠዋፉ የመጀመሪያ ሦስት ዙሮች ላይ ብቻ ረምል (እርምጃን ከማቀራረብ ጋር መፍጠን) ሱንና ነው፡፡
3. በመቀጠልም ወደ ሰፉ ኮረብታ በመሄድ (ወደርሱ ስትቀርብ) ይህንን የአላህ ቃል አንብብ፦
٥٨
ትርጉሙም፡- «ሶፋና መርዋ ከአላህ(ትዕዛዝ መፈጸሚያ) ምልክቶች ናቸው፡፡ ቤቱን (ካዕባን) በሐጅ ወይም በዑምራህ ሥራ የጎበኘ (ያቀደ) ሰው በሁለቱ (መካከል) በመመላለሱ በርሱ ላይ ኃጢአት የለበትም፡፡ መልካምንም ሥራ በፈቃደኛነት የሠራ ሰው (አላህ ይመነዳዋል)፤ አላህ አመስጋኝ(የባሮቹንም ስራ)ዐዋቂ ነውና፡፡» {አል-በቀራ፡158}
በላዩም ላይ ወጥተህ ወደ ካዕባ አቅጣጫ በመዞር ሶስት ጊዜ “አልህምዱሊላህ አላሁ አክበር” በማለት አላህን ከማመስገን ጋር አልቀው፣ ዱዓዕም የሚያደርግ ሰው እጁን እንደሚያነሳው እጅህን ከፍ አድርገህ ሶስት ጊዜ
\"لاَإِلَهَ إِلاَّاللَّهُ وَحْدَهُ لاَشَرِيكَ لَهُ لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ وَهُوَعَلَى كَلِّ شَىْءٍ قَدِيرٌ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ أَنْجَزَ وَعْدَهُ وَنَصَرَ عَبْدَهُ وَهَزَمَ الأَحْزَابَ وَحْدَهُ\"
“ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወህደሁ ላ ሸሪከ ለሁ፤ ለሁል ሙሉኩ ወለሁል ሀምዱ ወሁወ አላኩሉ ሸይኢ ቀዲር”“ላ ኢላሀ ኢለሏህ ወህደሁ አንጀዘ ወዕደሁ ወነሰረ ዐብደሁ ወሀዘመል አህዛበ ወህደሁ” በል።
ትርጉሙም፦ « ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚግባው አምላክ የለም። አንድ ነው አጋርም የለውም። ንግስና ለእርሱ የተገባ ነው። ምስጋናም ለእርሱ የተገባ ነው። እርሱ በሁሉ ነገር ላይ ቻይ ነው። ከአላህ ሌላ አምልኮ የሚገባው አምላክ የለም። ቃልኪዳኑን ሞልቷል። ባሪያውንረድቷል።የተሰበሰበውንም የጠላት ጦር ለብቻው አንኮታኩቷል።» [ሙስሊም የዘገቡት]
ይህን ከማለትህም ጋር በየመሃሉ አላህን መማፀንህ ዱዐእህንም ሶስት ሶስት ግዜ ደጋግመህ ማድረግህ ሱንና ነው፡፡ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት ዚክሮች የተወሰኑትን ብቻ ብትልም ችግር የለውም፡፡
* ከዚያም ከሰፋ በመውረድ የዑምራህን ሰዕይ ሰባት ግዜ በሰፋና መርዋ መካከል አድርግ፡፡ በሁለቱ አረንጓዴ ምልክቶች መካከል ስትሆን የቻልከውን ያክል ትፈጥናለህ(ትሮጣለህ)፡፡ ከምልክቶቹ በፊት በተለመደው እርምጃህ ትራመድ እንደነበረው ሁሉከምልክቶቹም በኋላ በተለመደው እርምጃህ(ሰዕይህን)ቀጥለህ መርዋ ላይ ትወጣለህ፤ አላህን ታመሰግናለህ ልክ ሰፋ ላይ የፈፀምከውን ድርጊት ትፈፅማለህ፡፡
* ለጠዋፍ እና ሰዕይ የተለየ እንዲሁም ግዴታ የሆነ ዚክር የሌለ ሲሆን ይልቁኑ ጠዋፉን እና ሰዕዩን የሚፈጽመው ግለሰብ ከነብዩ () በትክክለኛ ሰነድ ለተዘገቡት ዚክሮች እና ዱዓዋች ትኩረት ከመስጠት ጋር ከዚክር እና ዱዓዕ አልያም ቁርዓንን ከማንበብ የገራለትን ይፈፅማል፡፡ 
4. ሰዕይህን በተሟላ መልኩ ከጨረስክፀጉርህን ተላጨው ወይም አሳጥረው ሆኖም ሙተመተዕ ከሆንክ መላጨትህን ከሐጅ ተሀሉል ለምታደርግበት ወቅት አቆይተኸው ለአሁኑ ፀጉርህን ማሳጠርህ በላጭ ነው፡፡ በዚህ ተግባርህ ዑምራህ የተሟላ ይሆናል፡፡ ከዚህ በኋላ (ሙተመቲዕ ከሆንክ ነው ) በኢሕራም የተነሳ የተከለከልካቸው ነገሮች (መሕዙራቱል-ኢሕራም) ሁሉ ይፈቀዱልሃል።
* በተጨማሪም ሙተመተዕ ወይም ቃሪን ከሆንክ አንድ በግ (ፍየል) በግልህአልያም ከግመል እና በሬ አንዱን ለሰባት በእርዱ ዕለት (ከዚያም በኋላ ባሉ ሶስት ተከታታይ ቀናት) ማረድ ግዴታ ሲሆንብህ ይህንን ማድረግ ካልቻልክ አስር ቀን (ሶስቱን በሐጅ ላይ ሰባቱን ወደ ቤተሰቦችህ ስትመለስ) መፆም ግዴታ ይሆንብሀል፡፡

http://www.nesiha.com/index.php?option=com_content&view=articleid=285%3A2015-02-16-15-24-46&catid=34%3A2014-04-10-14-18-18&Itemid=118

Post a Comment

0 Comments