Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም



የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡
*************************************
ምስጋና ለአላህ ነው፤ ሁለት የመደሰቻ በአላትን የደነገገ፡፡ አሁንም ምስጋና ይገባው ይህንን ሸሪዓ ከመበረዝ እጠብቀዋለሁ ብሎ ቃል የገባው አላህ፤ የሃይማኖት ድንጋጊን ሁላ ለራሱ ብቻ ያደረገ፤ በዚህም ላይ ታላቅ ጥበቡን ያሳየ፡፡ እንደሌሎቸ ሀይማኖቶች፤ ቀሳውስት እንደበረዙት (እንደጨመሩበት እና እንደቀነሱበት) እንዳይሆን በግልፅ ሸሪዓዊ ድንጋጌን ለራሱ ብቸኛ አውጪ ያደረገ፡፡
ሱና ፆም ፆመን ዝም ብሎ ማለፍ እንጂ ከአላህ የተደነገገ በዓል የለም፡፡ ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር፤ ከነብያችንም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)፤ ከሰሃባዎቻቸው (ሪድዋኑላሂ አለይሂም)፤ ከ3 ምርጥ ትውልድ፤ ከ4 አኢማዎች አላገኘንም፡፡ ታድያ ለምንድን ነው እኛ ያልታዘዝነውን የምንሰራው???
ሰኞ እና ሀሙስ ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ 13፣14፣15 ፆመን ምንም በአል ከሌለ፤ የሸዋል 6 ከየት መጣ??? አላህን እንፍራ፡፡
አንዳንድ ቦታ ያውም ከዋናው ኢድ በላይ ይህን ቀን ያከብሩታል፡፡
እወቅ የአላህ ባሪያ ከሽርክ ቀጥሎ ሸይጧን ዘንድ የተወደደው ወንጀል ቢድዓ ነው፡፡ ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው፤ ጥመት ሁሉ ለእሳት ነው፡፡
አላህ በደነገገልን 2 ኢዶች፤ ከዛ በጁምዓ ብቻ እንብቃቃ፡፡ ሁሉ ነገር የሌለው ይቀላውጣል፡፡ አላህ ግን ይህን ዲን ሞልቶታል፤ ታድያ እንደ አህለል ኪታብ መጨማመሩ ምን አስፈለገ፤ የአላህን ቁጣ ለመውረስ ካልሆነ፡፡
የአላህ ባሪያዎች ሆይ! ትንሹ ኢድ የሚባል ነገር በሸሪዓ የለም፡፡ ተጠንቀቁ አስጠንቅቁ፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት እና ሩሱሎች ኢማም ላይ ይሁን፡፡