Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አሕባሽ፡ የጀህሚያ ወራሽ፣ ከኸዋሪጅ የከፋ አፍራሽ!


Taju Nasir
አሕባሽ፡ የጀህሚያ ወራሽ፣ ከኸዋሪጅ የከፋ አፍራሽ!



" አላህ ከዐርሹ በላይ ነው " የሚለው አቋም ቁርአናዊ እና ሐዲሳዊ መሠረት ያለው፣ የነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ምርጥ ሶሐቦች፣ የታቢዒዮች፣ የአትባዑትታቢዒን፣ የነሱ መልካም ምትኮች፣ የአራቱ የፊቅህ መዝሀብ ኢማሞች፣ የቁርአን ሙፈሲሮች አልፎም የብዙሃኑ ሙስሊም አቋም እንደሆነ በዝርዝር አሳልፈናል። እንዳውም በዚህ ርእሰ-ጉዳይ ላይ ውዝግብ ከመነሳቱ በፊት የነበሩ ምሁራን ዘንድ ወጥ የሆነ ስምምነት እንጂ አንድም የተለየ ሃሳብ እንደሌለም አይተናል። ልክ ዛሬ አሕባሾች እንደሚያደርጉት " አላህ ከዐርሹ በላይ ነው " የሚሉ ሰዎችን በጅምላ እንደ ከሃዲ መቁጠር ከጥንት እስከ ዛሬ፣ ከመሀይም እስከ ምሁር ሙስሊሙን ኡማ በጅምላ ማክፈር እንደሆነ ይስተዋል። ይሄ ምነኛ አደገኛ የሆነ አካሄድ እንደሆነ ተመልከቱ! ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም { አንድን አማኝ በክህደት የወነጀለ ልክ እንደገደለው ነው } ይላሉ። [ ቡኻሪ፡ 6105]

ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላል፦
" ደግሞ እነዚህ ከጥቅል ቃላት የፈጠሩትን ፈሊጥ ሃይማኖት ያደርጉታል። በሱም ሰበብ ይወዱበታል፤ ይጠሉበታል። አልፈውም ፈጠራቸውን የተቃወማቸውን ያከፍሩበታል። " በመሰረታዊ የሃይማኖት ጉዳዮች ላይ የተሳሳተ ይከፍራል " ይላሉ። መሠረታዊ የተባሉት ጉዳዮች ፈጠራዎቻቸው ይሆናሉ። ኸዋሪጅ፡ አፈንጋጭ ሙብተዲዖች እንደሆኑ ስለሆኑም እንደተወገዙና እንደተተቹ በበርካታ የነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ንግግሮችና በሶሐቦች ወጥ ስምምነት እንደተረጋገጠ ይታወቃል። ነገር ግን እነሱ ያደረጉት የተወሰኑ የቁርአን አንቀፆችን ከሚያምኑት አቋም ጋር በሚስማማ መልኩ መተርጎም ነው። ከዚያም ይህን አቋማቸውን የተቃወመን ማክፈር ነው። ለምን? ቁርአንን ተቃውሟል ብለው ስላመኑ። ጭራሽ ቁርአን ውስጥ መሠረት የሌላቸውን አዳዲስ ፈሊጦችን ፈጥሮ እነዚያን ፈሊጦች የተቃወመውን የሚያከፍር ሰው ግን አቋም ከኸዋሪጅም አቋም የከፋ ነው። ለዚህም ነው ቀደምቶችና ታላላቅ መሪዎች የጀምህያን አቋም ከኸዋሪጅ አቋም የከፋ እንደሆነ ወጥ ስምምነት ላይ የደረሱት። "
[ደርእ፡ 1/49]

ተውሂድ የሁለት ሃገር የስኬት ቁልፍ ከሚለው የኢብኑ ሙነውር መፅሐፍ ከገፅ 137-138 የተወሰደ

Post a Comment

0 Comments