Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከብርቂዬዎች አንደበት

ተንቢሃት የዋትሳፕ ግሩፕ
📗ከብርቂዬዎች አንደበት
ከዓለማችን ታላላቅ ሊቃውንቶች መካከል በድንቅ እውቀታቸው፣ አቋማቸውና የማስተማር ብቃታቸው ዓለምን በማካለል ያስደመሙት ሸይኽ ሙሀመድ አማን አልጃሚ ስለረመዳን አጠቃቀም ቀጣዩን ይመክሩናል [ረሂመሁላህ]
قال العلامة محمد بن أمان الجامي ـ رحمه الله ـ:
💥በዚህ ረመዷን የሰው ልጅ [ፆመኛው] እንቅልፉን ዝቅ አድርጎና መብልንና መጠጥንም በመቀነስ የአኗኗር ሁኔታውን ቀለል ማድረግ ይገባዋል።
በመሆኑም:- ለፆሙ፣ ለሌሊት ሰላቱና ሃያሉ አምላኩን ለማወደስ [ለዚክር] ሀይል እንዲያገኝ የሚረዳውን ያህል ብቻ መጠቀሙ በቂው ነው።
ነገር ግን የሚያበዛቸው ከሆነ ጌታውን የመታዘዝ ጣዕሙ ይጠፋበትና ትዕዛዛትን እየጣመው የመፈፀም ስሜትን ያጣል። ልቦናውም መረጋጋት ያጣና ውጥር ያለ ልብ ሆኖ [የሚበሉና የሚጠጡ ነገሮችን] እንዴት እንደሚሰበስብ፣ እንዴት እንደሚበላና እንደሚመገብ ያሰላል።
ጭንቀቱ ሁሉ ለነዚህ ይሆናል። በመሆኑም እዚህ ደረጃ የደረሰ ሰው [ዋናው ግቡን መብልና መጠጥ በማድረጉ] ከእንስሳ ባህሪ ተጋርቷል።💥
ምንጭ ☞【ዛዱል መዓድ ኪታብን ሲያስተምሩ ከሰጡት አስተያየት】
” المفروض في هذا الشهر [رمضان] أن يقتصر الإنسان على الكفاف من العيْش وعلى تخفيف النوم والتقليل من الأكل والشرب والاقتصار على ما يستعين به على الصّيام والقيام وذكْرِ الله تعالى، وأمّا الإكثار من ذلك فيذهبُ بلذّة الطاعة، لا يحسّ للطاعة لذّةً ولا يجدُ في نفسه انشراحاً مشغول البال كيف يجمع وكيف يتناول وكيف يغذي ، هذا كل همه، ومن وصل إلى هذه الدرجة اشترك مع البهائم! “.
[ التعليق على زاد المعاد]
---------------------------
www.fb.com/tenbihat
🎐ረመዳን 04/1436
ጁን 21/2015

Post a Comment

0 Comments