Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በኢኽ ዋኖች የተጻፉት ኪታቦች የመቃጠል ዜና ማንን አስደሰቶ ማንንስ አስከፋ ? ለምን ?



بسم الله الرحمان الرحيم
በዚህ በክፍል ሁለት የምንመለከተው ፤ የሙርሲን ሀቅነት በመማረጋገጥ እሱን የነካ ኢስላምን የነካ ነው በማለት የሀቅና የባጢል
መመዘኛ የተደረገበት ye Ummu lij ከንቱና ከሀቅ የራቀ ነጥብ ይሆናል አላህ ካለ ።
ye Ummu lij ምን ብሎ ያስቀምጣል ።
(( የሙስሊም ድል ህመማቸው ነው፡፡የከሀዲያን ደል ሰርግና ምላሻቸው ፡፡ቁርዐን ህገ-መንግስታችን ነው የሚለው ሙርሲ ሲያሸንፍ ተከፍተዋል ፡፡እርሱን ለመጣል በሚደረገው ትግል ሁሉ ተሳታፊም ነበሩ ))
የትኛው የሙስሊሙ ድል ነው የምታወራው? የትኛው ድል ነው እያገኙ ያሉት ? ደማቸው በየቀኑ እንደጎርፍ የሚጎርፈውን ነው እንዴ ድሉ?
በኢኽዋኖችና በተክፊር ኡለማ ተብዮው ፈትዋ ፤ ሙስሊም መሪ ላይ አመፅ ማንሳት ይፈቀዳል ብለው በየሙስሊሙ ሀገር አለመረጋጋት ተፈጥሮ ከካፊሩ በፊት ሙስሊም ለሙስሊሙ እርስ በርሳቸው እንዲጨፈጨፉ እይተደረገ ያለ ነው እንዴ ድሉ? እስኪ ጦቁሙን የትኛው የሙስሊም ሀገር ነው በመሪያቸው ላይ አመፅ አንስቶ በተረጋገ ሁኔታ ያለው ?
ሙርሲ ሲያሸንፍ ተደሰተው ሲያወርዱት የተከፉት ሰዎች ለምን ይሁን? እውን ለሸሪዓ ብለው ነው ወይስ ለኢኽዋናዊ ፖለቲካ ።ይህ የሚያረጋግጥልን ሙርሲ ምረጡኝ ሲል በሸሪዓ ነው የማስተዳድረው ነው ያለው? ስልጣኑን ሲረከብ በቁራን ምሎ በሸሪያ አስተዳድራቸዋለ ብሎ ነው ዋይስ በሰው ስራሽ ህግ አስተዳድራለው በሎ ነው በአላህ የማለው ? እስከሚወርድ ድረስስ ሲያስተዳድር የነበረው በሸሪዓ ነበር? የዚህ ሁሉ መልስ ማንኛው ሙስሊም አላህ ጆሮና አይን የሰጠው ይመሰክራል ።
ቁርዓን ህገ መንግስታችን ነው ያለው ስልጣን ስይዝ ምን በላው ? ይህ ቃልማ ኢኽዎኖች ሙስሊሙን ለ80 አመት በላይ የማታላያ ቃል አንዱ መሆኑ አላህ በሙርሲ መሪነት ሙስሊሞን አሳይቶታል ።
ሙርሲ ሊመረጥ ሲል ከልባቸው ደግፎት በየሞሃደራችህው ምረጡት ብለው ሲያሞግሱት የከረሙት የኢክዋኖች አጭብጫቢ የተክፊርና የኹሩጅ ( ሙስሊም መሪ ላይ ማመፅ ) ማምረቻ ፋብሪካ የሆኑት እንድነ መሀመድ ሃሳንና ሁሴን ያቁብና ኣቡ ኢስሃቅ ሁዌይኒ የመሳሰሉት ፤ ሙሪሲ ስልጣን ከያዘ ቦሃላ የምን ሸሪዓ ነው የምታወሩት ሲል ፤ ከሺዓ ጋርም እጅና ጋንት ሆኖ ሺዓዎችን ወንድሞቻችን ናቸው በየ ዓመቱ ባዕላቸውን ማክበር ይችላሉ ብሎ በግብፅ ለስንት መቶ አመት ያለተደረገውን እንዲደረግ ሲያፀድቅ ። ምን ብለው ነው የተናገሩት

ሁሴን ያቁብ ፤ ምን አለው ለ ሙርሲ ፤ በሸሪኣ አስተዳድራለው በሎ አታለለ ••••. ከዚህ የመልከቱ ቪዶን https://www.youtube.com/watch?v=1RLOR4wTToo

ሙስጠፋ አደዊ ፡ ምን አለ ለሙርሲና ኢክዎኖች ፤ አላህ ይድረስልን ኢኽዋኖች ቃል ገተውልን ከዛ የካዱን ናቸው ። ከዚህ ይመልከቱ ቪዶዮን https://www.youtube.com/watch?v=gd1mDXO-EOY

መሀመድ ረግቢይ ፡ ሙርሲ ወደ አላህ ተውባ ተመለስ ሺዓዎችን ወደ ግብፅ ከመጣትህ ፡ ከዚህ ይመልከቱ ቪዲዮን https://www.youtube.com/watch?v=S-3kfxBkNPM

አቡ ኢስሃቅ ሁዌይኒ ፡ ለሙርሲ ምን አለው ፡ ሙርሲ ሆይ ከአንተ በፊት የነበሩት መሪዎች ያላደረጉትን ሺዓዎችን ማስተናገዱ ላይ ሀጥያት እንዳትሰበስብ በቪዲዮ ከዚህ ይመልከቱ ፦ https://www.youtube.com/watch?v=HwurmS6X_9Q

መሀመድ ሃሳን ፡ ሙርሲ ከአላህ ምንም እርዳታ እንዳትከጅል ሺዓዎችን ወደ ግብፅ በመጋበዝህ ፤ በቪዺዮ ይመልከቱ ፡ https://www.youtube.com/watch?v=uTDlHC7lI_w

ይህንን ሁሉ ማመጣው ፤ ኢኽዋኒው ሙርሲ የደገፈ ሁሉ ማሽሃላህ ጥሩ ሙስሊም ለሸሪዓ የሚቆረቆር ፤ እሱን በክፉ ያነሱት ሁላ የኢስላም ጥላት ተብሎ መመዘኛ አለመሆኑ ለማስቀመጥ ነው ። እንዲሁም ለሙርሲ የሚቆረቆሩ ሁላ ለኢኽዋንነትና እንጂ ለሸሪዓ እንዳልሆነ ሙስሊሙ እንዲረዳ ነው ። እንዲሁም ለሰይድ ቁጥብና ለቀርዳዊም የሚቆረቆሩት ለሸሪዓ ሳይሆን ለተክፊርነታቸውና ለኢክዋነታችው መሆን አንድ ላይ ይምናይ ይሆናል አላህ ካል ።
በመጨረሻም ግልፅ ማድረግ የምፈልገውን ዋናው ነጥብ ። ሲሲና ሌሎችም ሙርሲን የጠሉበት ምክንያትና የአህሉ ሱና በሙርሲ ላይ ያላቸው ነቀፌታ ሊለያይ ይችላል ሲሲስ ለፖለቲካው ሊሆን ይችላል እሱ እኛን አይመለከትም ። እንዲሁም ሲሲሲ የነኢኽዋኖችና ተክፊሮች ኪታብ ማቃጠል የራሱ የሆነ አጅንዳ ሊኖረው ይችላል ፤ እኛ በድርጊቱ የምደሰተው ሲሲሲ ሲለሚያደርገው አይደለም ፤ ኪታቦቻቸው የፊትና በር ስለሆኑ ነው እንዴት እንደሆነ እንመጣበታለን ። አላህ ሃቅን በህቅነቱ አውቀይ የሚከተሉ ባጢልም በባጢልነት አውቀው የሚርቁ ያድርገን ክፍል ሶስት ይቀጥላል አላህ ካለ።