የአፍሪካ ቲቪ ፕሮግራም መሪዎች ምናለ አላህን ብትፈሩ?
‹‹አፍሪካ ቲቪ ላይ የምናውቃቸው ወንድሞች አፍሪካ ሲኒማ መድረክ ላይ ምናሳያችሁ ነገር አለን ብለውናል››
ተብሎ ማስታወቂያ በፌስቡክ ሲለቀቅ እንኳን መልስ አትሰጡም ወይንስ እናንተም ቲቪ አፍሪካ ላይ ተው ብትባሉ አልሰማ ያላችሁትን ድራማ አሁን ደግሞ ሙስሊሙ ወደ ሲኒማ ቤት እንዲጠራ ፈልጋችኋልን?
ተው አላህን ፍሩ፡፡ አላህን ፍሩ ከመባል ውጭ ምን እንድንላችሁ ትፈልጋላችሁ?
ሀሺም ሙዘይን ምናለ አላህን ብትፈራ?
‹‹ልብ አንጠልጣይ ኢስላማዊ የቤተሰብ ቲያትር›› ብላችሁ ሙስሊሙን ወደ ሲኒማ ቤት ስትጠሩት አላህን አትፈሩም?
የሴት ምስል አብሮ የቲያትሩ ማስታወቂያ ላይ ተለጥፏል፡፡ ሴት ልጅ እኮ መሰተር እንጂ በየመድረኩ አይደለም እንደማስታወቂያ እቃ ብቅ ማለት ያለባት፡፡
እስቲ ይህን ልብ ብለን እናንብብ
የምዕመናን እናት አኢሻን የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሚስት እና ማንም ሊያገባት ካለመቻሉም በተጨማሪ እሷ ግን ስታስተምር ከመጋረጃ በስተጀርባ ሆና ነበር የምታስተምረው፡፡ ታድያ ሌሎች ሴቶች ማንም ሊያገባቸው እየቻለ አብረው ድራማ እና ፊልም በኢስላም ስም የሚሰሩት ወንድ አጅነቢ ሆኖ ሳለ ለምን ትታያለች?
ለምን አላህ አይፈራም?
ማስታወቂያው ላይ
‹‹ጥበብን ጉዷን ስናፈላው ኑ ተመልከቱ….›› ይላል
ሱብሃነላህ ጥበብ ማለት እኮ ሱናን መከተል ከጥመት መንገዶች መራቅ ነው እንጂ መስጂድ፣ ቁርዓን፣ ቂርዓት የተጠማውን ሙስሊም ቲያትር፣ ነሺዳ፣ ድራማ እያሉ ማባከን አይደለም፡፡
ያው እንዲህ አይነት ማስጠንቀቂያዎች ሲለቀቁ የሚከተሉት የተለመዱ ቅጥፈቶች እና ማስደንበርያዎች ይሰማሉ
1) ለምን በድብቅ አትመክሯቸውም
በአደባባይ እንዲህ ከዲን ጋር የሚጋጭ ነገር እያስተዋወቁ ሰዎችን ወደዚህ የተሳሳተ አካሄድ እየጠሩ በአደባባይ ልክ አለመሆኑን እና ሙስሞች እንዳይታለሉ ካልተደረገ ምኑ ላይ ነው ምክክሩ፡፡ በድብቅ የተሰራ እና ሰው ጋር ያልደረሰ ከሆነ በድብቅ ይመከራል አለበለዚያ ሰው ይጠነቀቀው ዘንድ በአደባባይ ይፋ ይሆናል፡፡
2) ሙስሊሙ ኡማ ጠላት እያሰቃየው እናንተ ልትበታትኑን ነው
ይቼ ምስኪኑን የሚሰሩትን ጥፋት እንዳያጋልጥ የታወቀባት አፍ ማስያዣ ናት፡፡ ሙስሊም ኡማ ጠላት እያሰቃየው ነው ብለው ነው እንዴ እንዲህ አይነት ከሸሪዓ የወጣ ስራ የሚሰሩት፡፡ ከመቼ ጀምሮ ነው በፈተና ግዜ ደግሞ አላህ የሚታመፀው?
በል እንዲያውም አሁን ሁላችንም ወደ አላህ ዲን በተውበት የምንመለስበት እንጂ ሲኒማ ቤት በኢስላም ሽፋን ድራማ የምናይበት አይደለም፡፡
አንድነታችን በፍፁም በባጢል ላይ ሊመሰረት አይገባውም አላህ አይረዳውምና፣ በል እንዲያውም ውርደት ያጋጥመዋል፡፡
3) የሰው አይብ መለቃቀም አይሰላቻችሁም
አይብ ማለት ምን ማለት ነው?
አይብ ስለሆነ ነው እነሱ ይህን ማስታወቂያ በአደባባይ የለቀቁት ወይንስ ‹‹ኢስላማዊ›› ብለው ለሰው የሚያስተዋውቁት?
ታድያ በዲን ስም ጥፋት በአደባባይ ሲጠፋ እያየን ዝም እንላለን በፍፁም፡፡ አላህ ኢኽላስ ይስጠን፡፡
4) አንድ አለን በምንለው አይናችን አፍሪካ ቲቪ መምጣት የጠላት ሴራ ነው እና የመሳሰሉት
ጥያቄ አፍሪካ ቲቪ ብቸኛው ቻናል ነውና ድራማ፣ ነሺዳ እንዲያሳይ የፈቀደለት ማን ነው?
ህዝባችን አልከሶ፣ አብሬት፣ ቃጥባሬ፣ ጀማ ንጉስ፣ ዳንግላ፣ ኑር ሁሴን እና የመሳሰሉት ቦታ ይሄዳል፡፡ ቁርዓን መስማት እና መቅራት ይፈልጋል፡፡ ታድያ የነብያት ተልኮ ተውሂድ ተደጋግሞ ሊነገር ሲገባው፣ ሽርክን የማውገዝ ትምህርት በግልፅ ሊሰጥ ሲገባው፣ ለምን ይሆን እንዲህ ድራማ እየተባለ የፕሮግራም ሰዓት የሚሻማው?
ስለዚህ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሰዎች በሃቅ ይለካሉ እንጂ ሃቅ በሰዎች አይለካም፡፡
አላህ ሆይ! ሃቅን በሃቅነቱ አሳየን የምንቀበለውም አድርገን፣ ባጢልን በባጢልነቲ አሳየን የምንርቀውም አድርገን፡፡

0 Comments