Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ታዳጊ በሆነች ልጅ አገረድ ሴት ላይ ፆም ግዴታ የሚሆንበትን ግዜ ሸይኽ ዐብደላ ኢብን ጅብሪን (ረሂመሁላህ) ተጠይቀው ተከታዩን ምላሽ ሠጥተዋል ።

ታዳጊ በሆነች ልጅ አገረድ ሴት ላይ ፆም ግዴታ የሚሆንበትን ግዜ ሸይኽ ዐብደላ ኢብን ጅብሪን (ረሂመሁላህ) ተጠይቀው ተከታዩን ምላሽ ሠጥተዋል ።
ጥያቄ፦ አንዲት ታዳጊ ልጅ አገረድ ፆም መጀመር ያለባት ጊዜ መቼ ነው?
ሸይኹ ሲመልሱ ፦ ታዳጊ የሆነች ልጅ አገረድ ፆም መጀመር ያለባት ሌሎች ግዴታ የሆኑ የአምልኮት (ኢባዳ) አይነቶችን መጀመር በሚኖርባት ግዜ ነው።
አንድ ልጅ አገረድ ለ አቅመ ሔዋን ደረሰች የሚባለው አንድ አስራ አምስት አመት ሲሞላት የመራቢያ አካላቱዋ አካባቢ ፀጉር መውጣት ሲጀምር ፤ የወር አበባዋ መፉሰስ ሲጀምር ወይም ስታረግዝ ነው።
ስለዚህም ከነዚህ ከተጠቀሱት ነገሮች አንዱ በተከሰተ ጊዜ ልጅ የ አስር አመት ልጅ ብትሆን እንኳን ለአቅመ ሔዋን ደርሳለችና ፆም በእርሱዋ ላይ ግዴታ ይሆንባታል ።
አሁን አሁን እንደሚታየው ብዙ ልጃገረዶቹ የመጀመሪያ የወር አበባቸውን የሚያዩት በ አስር ወይም በ አስራ አንድ አመታቸው ነው ቢሆንም ወላጆቻቸው ይህንን ሁኔታ ችላ እያሉና ልጆቻቸውን አሁንም ገና ለ አካለ መጠን እንዳልደረሱ እያሰቡ እንዲፆሙ አያደርጓቸውም።
ይህ ፈፅሞ ስህተት ሲሆን ታዳጊ የሆነችው ልጅ አገረድ የመጀመሪያ የወር አበባዋን ካየችበት ግዜ ጀምሮ ለ አቅመ ሔዋን መድረሱዋ እና ሙሉ ሴት መሆኗ ተረጋግጦ ግዴታ የሆኑ የ አምልኮት ተግባራት ሁሉ በእርሱዋ ላይ ይፀኑበታል።

Post a Comment

0 Comments