እኛ ደግሞ እንዲህ እንላለን አንድ ጿሚ ከቀኑ ክፍለ ጊዜ አንስቶ እስከ ሌሊት ዱዓ ቢያደርግ ተቀባይነት እንዳለው የሚገልጹ በርካታ ሰሒህ የሆኑ ሐዲሶች አሉ:: ከነዚያም ውስጥ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል::
“ሶስት ዱዓዎች ተቀባይነት አላቸው::ጾመኛ የሚያደርገው ዱዓ የተበዳይ ዱዓ የመንገደኛ ዱዓ ናቸው::” አልባኒ ሐሰንብለውታል:: ፍጡር ሰዓት ላይ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይሉት የነበረውን በል::እርሱም “ዘሀበ ዘመኡ ወብተለት አልዑሩቅ ወሰበተል አጅር ኢንሻላህ::”ይን ነበር የነብዩ
ሱና ሲያፈጥሩ:: (ማስታወሻ) ይህ ዱዓ የሚባለው ከፍጡር በኋላ ነው ምክንያቱም “ወብተለቲል ዑሩቅ” የሚለው የደም ቱቦዎች ረጠቡ ማለት ነውና የደም ቱቦዎች ረጠቡ የሚባለው ከተበላ እና ከተጠጣ በኋላ ነው::ጾመኛ ከማፍጠሩ በፊት ምን አይነት ዱዓ ያድርግ የሚለው ይህ መባል አለበት በሚል መልኩ የመጣ ነገር የለም:: ሙስሊም የሆነ ሰው የገራለትን ዱዓ ያድርግ በተለይ ሊያፈጥር ሲል “ለጾመኛ ሲያፈጥር የማይመለስ ተቀባይነት ያለው ዱዓ አለው::”
ሸይኽ ረቢዕ ቢን አል ሃዲ አልመድኸሊ( ሀፊዘሁላህ)
ሸይኽ መሐመድ ቢን ሳሊሕ አል-ዑሰይሚን ይህ ጥያቄ ቀርቦላቸው ነበር::
ጾመኛ የሆነ ሰው ዱዓ ማድረግ ያለበት ከፍጡር በኋላ ነው ወይስ በፊት??
እንዲህ በማለት መለሱ “ጾመኛ የሆነ ሰው ዱዓ ማድረግ ያለበት ከፍጡር በፊት ከመግሪብ በፊት ነው::ምክንያቱም ነፍስ በጣም ደካማነቷን የምታሳይበት እና እራሷን ዝቅ የምታደርግበት ሰዓት ነው:: ይህ ሁሉ ዱዓን ተቀባይነት ከሚያስገኙ ሰበቦች መካከል አንዱ ነው ጾመኛ ካፈጠረ በኋላማ ነፍሱ እረፍት ትፈልጋለች ምናልባትም እንቅልፍ እንቅልፍ ሊላት ይችላል::ነገር ግን ከአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሰሒህ ከሆነም አንዱ ዱዓ ተገኝቷል እርሱም ቢሆን ከፍጡር በኋላ ነው::እርሱም “ዘሀበ ዘመኡ ወብተለት አልዑሩቅ ወሰበተል አጅር ኢንሻላህ:: አቡ ዳዉድ ዘግበውታል አልባኒ ሐሰን ብለውታል:(2066) ይህም ቢሆን ከፍጡር በኋላ ቢሆን እንጂ ሌላ አይደለም::
0 Comments