Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጋምቢያው ፕሬዚደንት የሕያ ጃሜህ ግብረ ሰዶማውያኑን

የጋምቢያው ፕሬዚደንት የሕያ ጃሜህ ግብረ ሰዶማውያኑን “እዚህ (ጋምቢያ) ፈፅሙትና አሳያችኋለሁ፡፡ ጉሮሯችሁን ነው የምሰነጥቀው!” ብለው ዛቱ፡፡ አክለውም “በዚች ሀገር ውስጥ ወንድ ሆነህ ሳለ ሌላ ወንድ ልታገባ ብትፈልግና ብንይዝህ ማንም መቼም ባንተ ላይ አይን አይገጥምልህም፡፡ የትኛውም ነጭ ሰውም በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ሊያደርግልህ አይችልም!” ብለዋል፡፡
በነገራችን ላይ አሜሪካ እና አውሮፓ ይህን እርኩስ ምግባር ለማስፋፋት በሰብአዊ መብት ስም እስከ ደም ጠብታ እየታገሉ ነው፡፡ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችን ለዚህ እርኩስ ምግባር እውቅና የሚሰጥ ህግ “ካላፀደቃችሁ” እያሉ ከፊሉን እርዳታ አቋርጠውባቸዋል፣ ከፊሉን ደግሞ እያስፈሯሯቸው ነው፡፡ ታዲያ አንዳንዶቹ “እርዳታችሁ ገደል ይግባ” እያሉ በግልፅ ተቃውሟቸውን እያሰሙ ሲሆን አንዳንዶቹ ግን በግልፅ አፅድቀው ህዝባቸው ጋር የመረረ ጥል ውስጥ መግባት ባይደፍሩም ጌቶቻቸውን ማስከፋት አይፈልጉምና ከመጋረጃ ጀርባ የሚሰሩት ነገር እጅጉን አስጊ ሆኋል፡፡
ግብረ-ሰዶም አላህ በሱ ሰበብ የሉጥ ህዝቦችን ያጠፋበት እጅግ አስቀያሚ ስራ ነው፡፡ ግብረ ሰዶም በእንስሳት አለም እንኳን የማይፈፀም እጅግ የዘቀጠ ምግባር ነው፡፡ ምእራባውያኑ ይህን ቆሻሻ ተግባር ለማስፋፋት መነሳታቸው ምን ያክል ማህበራዊ እሴቶችን ለማፈራረስ፣ ልቅ ማህበረሰብ ለመገንባት ቆርጠው እንደተነሱ ያሳያል፡፡ “እንስሳ ናቸው” እንዳትሉ፡፡ እንስሳ እንዲህ አይነት ነገር አይፈፅሙም፡፡ በሀገራችን እራሱ የህፃናት ማሳደጊያ እያሉ ስንቶችን እንዳበለሹ የሚታወቅ ነው፡፡
አላህ ከጂንም ከሰውም ሸይጧኖች ተንኮል ይጠብቀን፡፡