ጥያቄ ፦ እከሌ ሸሒድ ነው ብሎ መመስከር ፍርዱ ምንድን ነው??
መልስ የዚህ ምላሽ ለአንድ ሠው ሸሒድነትን መመስከር ሁለት ገፅታዎች ይኖሩታል
1 ሸሒድነትን በባህሪ መገደብ ምሳሌ ፦ በአላህ መንገድ ላይ የተገደለ ሸሒድ ነው ፣ ለገንዘቡ ሲል የተገደለ ሸሒድ ነው ፣ … እና ይህን የመሣሠሉ መረጃ ስለመጣበት ይህ ይበቃል (ይፈቀዳል),ይህ ማለት አንተ ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም የተናገሩትን ስለምትመሰክር ነው ስለዚህ ይፈቀዳል ፣ የተከለከለ አይደለም እንደውም የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሰለምን ንግግር ከማረጋገጥ አንፃር ዋጂብ ነው
2 ግለ ሠብን ሸሒድ ነው ብሎ በሸሒድነት መነጠል ምሣሌ እከሌ ሸሒድ ነው ብሎ ብሎ መመስከር ፡ ይህ መልዕክተኛው በሸሒድነቱላይ ማመላከቻ ላልሠጡት ሠው አይበቃም አልያም የኢስላም ሊቃውኖች ሸሒድ በመሆኑ ላይ ለመሠከሩለት ሠው ሢቀር ይህን አስመልክቶ ቡኻሪይ "እከሌ ሸሒድ ነው አይባልም "የሚል ርእስ ከፈቱ ይህም ማለታቸው የሚያመላክተው ነገሩ ባለመቻሉ ላይ ቁርጥ ያለ ሀሣብ ማንፀባረቃቸው ነው¹ "በወህይ ቢሆን እንጂ ወደ ኡመር ኢብኑል ሀጣብ ሀዲስ አመላከቱ ኡመር "እናንተ ሠዎች ሆይ በዘመቻዎቻችሁ ላይ እከሌ ሸሒድ ነው እከሌ ሸሒድ ሆኖ ሞተ ትላላችሁ ምናልባት እሱ መጓጓዣው ላይ የምርኮ ገንዘብ ሣይከፋፈል ጭኖ ይሆናል አዋጅ! እንደዚህ አትበሉ ነገር ግን መልዕክተኛው እዳሉት በሉ በአላህ መንገድ ላይ የተገደለ ወይም የሞተ ሸሒድ ነው በሉ "በማለት ሁጥባ አደረገ
መልሡን የሠጡት ሼህ ሦሊህ አል ኡሠይሚን ረሒመሁላሁ ተአላ ናቸው