Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እስኪ አትኩረን እናንበው .አጋንንት ምንድናቸው

እስኪ አትኩረን እናንበው፣
1.አጋንንት ምንድናቸው? ጅኖች እንደ ሰው ልጆች ሁሉ ከአላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ዘንድ እሱን የማምለክ ግዴታ የተጣለባቸው፣ የአእምሮ ባለቤት የሆኑ፣ ህይወት ያላቸው ፍጡራን ናቸው። ቁሣዊ ከሆኑ የሰው ልጅ አካላት ነፃ መሆናቸው ከሰው ልጆች ለየት እንዲሉ ያደርጋቸዋል። ከሰው ልጅ የስሜት ህዋሣቶች እይታ ውጭ መሆናቸው ሌላው ባህሪያቸው ሲሆን በመጨበጥና በመዳሠስ
አይደረስባቸውም። በተፈጠሩበት ሁኔታ ላይም ሆነ በእውነተኛ ቅርፃቸው እነሱን ማየት አይቻልም።
በነገሮች የመመሰል ልዩ ችሎታም ተሠጥቷቸዋል።
2.መኖራቸውን እንዴት ልናውቅ እንችላለን? የአጋንንት ዓለም መኖሩን የምናውቅበት ብቸኛው
መንገድ መለኮታዊው ራእይ /ወህይ/ ነው። ቁርኣንም ሆነ ሀዲስ የጅኖችን መኖር፣ ከምን እንደተፈጠሩ፣ የተለያየ ጭፍሮች እንዳሏቸው፣ የአምልኮ ግዴታ ያለባቸው መሆኑን፣ ከአላህ
መልእክተኛ ዘንድ ቁርኣንን ስለማዳመጣቸውንና ስለ ሌላም ሌላም ነግረውናል።
3.ከምን ተፈጠሩ? አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ ጅኖች /አጋንንት/ ከምን እንደተፈጠሩ ሲነግረን እንዲህ ይላል፡-
ﻭَﻟَﻘَﺪْ ﺧَﻠَﻘْﻨَﺎ ﺍﻟْﺈِﻧﺴَﺎﻥَ ﻣِﻦ ﺻَﻠْﺼَﺎﻝٍ ﻣِّﻦْ
ﺣَﻤَﺈٍ ﻣَّﺴْﻨُﻮﻥٍ ﻭَﺍﻟْﺠَﺎﻥَّ ﺧَﻠَﻘْﻨَﺎﻩُ ﻣِﻦ ﻗَﺒْﻞُ
ﻣِﻦ ﻧَّﺎﺭِ ﺍﻟﺴَّﻤُﻮﻡِ
“ሰውንም ከሚቅጨለጨል ሸክላ ከሚገማ ጥቁር ጭቃ በእርግጥ ፈጠርነው። ጃንንም (ከሰው)
በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው።” (አል-ሂጅር 15፤26-27) ከተጠቀሱት ሁለቱ የቁርኣን አንቀፆች የምንገነዘበው ነገር የሰው ልጅ በመጀመሪያ የተፈጠረው ከአፈር ሲሆን ከዚያም በውሃ ተደባልቆ ጭቃ ሆነ፤ ጭቃው ጠረኑን እስኪለውጥ ድረስ ቆየ፤ ይሀው ጠረኑን የለወጠው ጭቃ ደረቀና እንደ ደረቅ ሸክላ ድምፅ ያለው ሆነ። ጅኖችም እንዲሁ በመጀመሪያ ላይ የተፈጠሩት ጭስ አልባ ከሆነ እሣት ነው። “ሰሙም” ማለት ከጭስ ንፁህ የሆነ እሣት ነውና። ጅኖች ከሰው ልጆች ቀድመው የተፈጠሩ መሆኑንም እንረዳለን።
4.ጅኖችና ጭፍሮቻቸው ጅኖች እንደ ሰው ልጅ ሁሉ የተለያዩ ጭፍሮች ስብጥር ናቸው። ሙስሊም እና ካፊር አላቸው። ከነሱ ውስጥ በመልካም ነገር ላይ የተሠማሩና በዚያውም ላይ የፀኑ አሉ። ከዚህ ውጭ የሆኑም አሉ። የተዘናጉና በቸልተኝነት ውስጥ የሠጠሙም እንዲሁ አሉ። ከነሱ ውስጥ በአላህ የካዱት / ካፍር የሆኑት/ አብላጫውን ቁጥር ይይዛሉ። አላህ ሱብሃነሁ ወተኣላ ቁርኣንን ስለዳመጡት
ጅኖች ሲናገር እንዲህ አለ
ﻭَﺃَﻧَّﺎ ﻣِﻨَّﺎ ﺍﻟﺼَّﺎﻟِﺤُﻮﻥَ ﻭَﻣِﻨَّﺎ ﺩُﻭﻥَ ﺫَٰﻟِﻚَ ﻛُﻨَّﺎ
ﻃَﺮَﺍﺋِﻖَ ﻗِﺪَﺩًﺍ [ ٧٢ : ١١ ]
“እኛም ከእኛ ውስጥ ደጎች አልሉ። ከኛም ከዚህ ሌላ የኾኑ አልሉ። የተለያዩ መንገዶች (ባለ ቤቶች)
ነበርን።” (አል-ጅን 72፤ 11) ይህም ማለት ከነሱ ውስጥ ሙሉ ለሙሉ በአላህ መንገድ ቀጥ ያሉና የተስተካከሉ አሉ። ባነሠ ደረጃ ማለትም በከፊል መልኩ የተስተካከሉም እንዲሁ። በሰው ልጅ ውስጥ እንደምናየው ሁሉ ጅኖችም የሚከተሉት የየራሣቸው የሆነ አመለካከትና መንገድ አላቸው። አላህ እንዲህ አለ
ﻭَﺃَﻧَّﺎ ﻣِﻨَّﺎ ﺍﻟْﻤُﺴْﻠِﻤُﻮﻥَ ﻭَﻣِﻨَّﺎ ﺍﻟْﻘَﺎﺳِﻄُﻮﻥَ ﻓَﻤَﻦْ
ﺃَﺳْﻠَﻢَ ﻓَﺄُﻭﻟَٰﺌِﻚَ ﺗَﺤَﺮَّﻭْﺍ ﺭَﺷَﺪًﺍ ﻭَﺃَﻣَّﺎ
ﺍﻟْﻘَﺎﺳِﻄُﻮﻥَ ﻓَﻜَﺎﻧُﻮﺍ ﻟِﺠَﻬَﻨَّﻢَ ﺣَﻄَﺒًﺎ
“እኛም ከእኛ ውስጥ ሙስሊሞች አልሉ። ከእኛም ውስጥ በዳዮች አልሉ። የሰለሙም ሰዎች እነዚያ
ቅንን መንገድ መረጡ። በዳዮቹማ ለገሀነም ማገዶ ኾኑ።” (አል-ጅን 72፤ 14-15) ከዚህ አንቀፅ የምንረዳው ከጅኖች ውስጥ ለአላህ እጅ የሠጠ ሙስሊም እንዳለ ሁሉ በክህደት እራሱን የበደለም መኖሩን ነው። የሠለመና ለአላህ እጁን የሠጠ በርግጥም በእውቀቱ ትክክለኛውን ጎዳና አገኘ። እራሱን የበደለ ደግሞ እሱ በርግጥም የጀሀነም ማገዶ
መሆኑ ግድ ነው።
5.ጅኖች እንደ ሰው ልጅ ሁሉ ግዴታ አለባቸው ጅኖች እንደ ሰው ልጅ ሁሉ ሙከለፍ /ግዴታ
ያለባቸው/ ፍጡራን ሲሆኑ ወደነሱ የተላኩ መልእክተኞችም ከሰው ልጆች ናቸው። አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ እንዲህ አለ
ﻳَﺎ ﻣَﻌْﺸَﺮَ ﺍﻟْﺠِﻦِّ ﻭَﺍﻟْﺈِﻧﺲِ ﺃَﻟَﻢْ ﻳَﺄْﺗِﻜُﻢْ ﺭُﺳُﻞٌ
ﻣِّﻨﻜُﻢْ ﻳَﻘُﺼُّﻮﻥَ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻢْ ﺁﻳَﺎﺗِﻲ ﻭَﻳُﻨﺬِﺭُﻭﻧَﻜُﻢْ
ﻟِﻘَﺎﺀَ ﻳَﻮْﻣِﻜُﻢْ ﻫَٰﺬَﺍ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺷَﻬِﺪْﻧَﺎ ﻋَﻠَﻰٰ
ﺃَﻧﻔُﺴِﻨَﺎ ﻭَﻏَﺮَّﺗْﻬُﻢُ ﺍﻟْﺤَﻴَﺎﺓُ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴَﺎ ﻭَﺷَﻬِﺪُﻭﺍ
ﻋَﻠَﻰٰ ﺃَﻧﻔُﺴِﻬِﻢْ ﺃَﻧَّﻬُﻢْ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻛَﺎﻓِﺮِﻳﻦَ [ ٦ :١٣٠ ]
“የጋኔንና የሰዎች ጭፍሮች ሆይ! ‘አንቀጾቼን በእናንተ ላይ የሚተርኩ የዚህንም ቀናችሁን
(ቅጣት) ማግኘትን የሚያስፈራሩዋችሁ ከእናንተው የኾኑ መልክተኞች አልመጧችሁምን?’ (ይባላሉ)። ‘በነፍሶቻችን ላይ መሰከርን፤ (መጥተውልናል)’ ይላሉ። የቅርቢቱም ሕይወት አታለለቻቸው። በነፍሶቻቸውም ላይ እነርሱ ከሓዲዎች የነበሩ መኾናቸውን መሰከሩ።” (አል-አንዓም 6፤130)
ﺳَﻨَﻔْﺮُﻍُ ﻟَﻜُﻢْ ﺃَﻳُّﻪَ ﺍﻟﺜَّﻘَﻠَﺎﻥِ ﴿٣١﴾ ﻓَﺒِﺄَﻱِّ ﺁﻟَﺎﺀِ
ﺭَﺑِّﻜُﻤَﺎ ﺗُﻜَﺬِّﺑَﺎﻥِ ﴿٣٢﴾ ﻳَﺎ ﻣَﻌْﺸَﺮَ ﺍﻟْﺠِﻦِّ ﻭَﺍﻟْﺈِﻧﺲِ
ﺇِﻥِ ﺍﺳْﺘَﻄَﻌْﺘُﻢْ ﺃَﻥ ﺗَﻨﻔُﺬُﻭﺍ ﻣِﻦْ ﺃَﻗْﻄَﺎﺭِ
ﺍﻟﺴَّﻤَﺎﻭَﺍﺕِ ﻭَﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻓَﺎﻧﻔُﺬُﻭﺍ ﻟَﺎ ﺗَﻨﻔُﺬُﻭﻥَ ﺇِﻟَّﺎ
ﺑِﺴُﻠْﻄَﺎﻥٍ ﴿٣٣﴾ ﻓَﺒِﺄَﻱِّ ﺁﻟَﺎﺀِ ﺭَﺑِّﻜُﻤَﺎ ﺗُﻜَﺬِّﺑَﺎﻥِ ﴿
٣٤﴾ ﻳُﺮْﺳَﻞُ ﻋَﻠَﻴْﻜُﻤَﺎ ﺷُﻮَﺍﻅٌ ﻣِّﻦ ﻧَّﺎﺭٍ ﻭَﻧُﺤَﺎﺱٌ
ﻓَﻠَﺎ ﺗَﻨﺘَﺼِﺮَﺍﻥِ ﴿٣٥﴾ ﻓَﺒِﺄَﻱِّ ﺁﻟَﺎﺀِ ﺭَﺑِّﻜُﻤَﺎ ﺗُﻜَﺬِّﺑَﺎﻥِ
﴿٣٦﴾
“እናንተ ሁለት ከባዶች (ሰዎችና ጋኔኖች) ሆይ! ለእናንተ (መቆጣጠር) በእርግጥ እናስባለን።
ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? የጋኔንና የሰው ጭፍሮች ሆይ! ከሰማያትና ከምድር ቀበሌዎች መውጣትን ብትችሉ ውጡ። በስልጣን እንጅ አትወጡም። (ግን ስልጣን የላችሁም) ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ? በሁለታችሁም ላይ ከእሳት ነበልባል፣ ጭስም ይላክባችኋል። (ሁለታችሁም) አትርረዱምም። ከጌታችሁም ጸጋዎች በየትኛው ታስተባብላላችሁ?” (አር-ረህማን 55፤31-36) ከላይ በተጠቀሰው አንቀፅ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ አጋንንትና የሰው ልጆች ከባድ እና ጥልቅ የሆነ ምርመራ እንደሚጠብቃቸው ያሣሰባቸው መሆኑን እንረዳለን። የቁርኣን አንቀፁ ሌላ ትልቅ ማስጠንቀቂያም አዝሏል። እናንተ ሰዎችና አጋንንቶች ሆይ! ከአላህ ምርመራ ከአንዱ ክልል ወደ ሌላው የሰማይ አሊያም የምድር ክልል በመሸሽ ማምለጥ የሚቻላችሁ ከሆነ ሽሹ ከቻላችሁም አምልጡ፤ ነገር ግን ፈፅሞ አይቻላችሁም፤ የአላህን ሀይልና ጥንካሬ በሚበልጥ ሀይል ካልሆነ በስተቀር ይህ ፈፅሞ የማይሞከርምና ነው። የአላህን ሀይል የሚበልጥ ነገር ይኖራል ብሎ መገመት ደግሞ ፈፅሞ የማይታሰብ ነው።
6.ጅኖች ከአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ቁርኣንን ስለ ማዳመጣቸው በአንድ ወቅት ከአጋንንት የሆኑ ልኡካን መጥተው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባላዩበትና ባላውቁበት ሁኔታ ቁርኣን አዳምጠው ነበር። ይህንንም
በማስመልከት አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ አለ
ﻭَﺇِﺫْ ﺻَﺮَﻓْﻨَﺎ ﺇِﻟَﻴْﻚَ ﻧَﻔَﺮًﺍ ﻣِّﻦَ ﺍﻟْﺠِﻦِّ ﻳَﺴْﺘَﻤِﻌُﻮﻥَ
ﺍﻟْﻘُﺮْﺁﻥَ ﻓَﻠَﻤَّﺎ ﺣَﻀَﺮُﻭﻩُ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ ﺃَﻧﺼِﺘُﻮﺍ ﻓَﻠَﻤَّﺎ
ﻗُﻀِﻲَ ﻭَﻟَّﻮْﺍ ﺇِﻟَﻰٰ ﻗَﻮْﻣِﻬِﻢ ﻣُّﻨﺬِﺭِﻳﻦَ ﴿٢٩﴾ ﻗَﺎﻟُﻮﺍ
ﻳَﺎ ﻗَﻮْﻣَﻨَﺎ ﺇِﻧَّﺎ ﺳَﻤِﻌْﻨَﺎ ﻛِﺘَﺎﺑًﺎ ﺃُﻧﺰِﻝَ ﻣِﻦ ﺑَﻌْﺪِ
ﻣُﻮﺳَﻰٰ ﻣُﺼَﺪِّﻗًﺎ ﻟِّﻤَﺎ ﺑَﻴْﻦَ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻳَﻬْﺪِﻱ ﺇِﻟَﻰ
ﺍﻟْﺤَﻖِّ ﻭَﺇِﻟَﻰٰ ﻃَﺮِﻳﻖٍ ﻣُّﺴْﺘَﻘِﻴﻢٍ ﴿٣٠﴾ ﻳَﺎ ﻗَﻮْﻣَﻨَﺎ
ﺃَﺟِﻴﺒُﻮﺍ ﺩَﺍﻋِﻲَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻭَﺁﻣِﻨُﻮﺍ ﺑِﻪِ ﻳَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻜُﻢ ﻣِّﻦ
ﺫُﻧُﻮﺑِﻜُﻢْ ﻭَﻳُﺠِﺮْﻛُﻢ ﻣِّﻦْ ﻋَﺬَﺍﺏٍ ﺃَﻟِﻴﻢٍ ﴿٣١﴾ ﻭَﻣَﻦ
ﻟَّﺎ ﻳُﺠِﺐْ ﺩَﺍﻋِﻲَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻓَﻠَﻴْﺲَ ﺑِﻤُﻌْﺠِﺰٍ ﻓِﻲ
ﺍﻟْﺄَﺭْﺽِ ﻭَﻟَﻴْﺲَ ﻟَﻪُ ﻣِﻦ ﺩُﻭﻧِﻪِ ﺃَﻭْﻟِﻴَﺎﺀُ ﺃُﻭﻟَٰﺌِﻚَ
ﻓِﻲ ﺿَﻠَﺎﻝٍ ﻣُّﺒِﻴﻦٍ ﴿٣٢﴾
“ከጋኔን የኾኑን ጭፍሮች ቁርኣንን የሚያዳምጡ ሲኾኑ ወዳንተ ባዞርን ጊዜም (አስታውስ)። በተጣዱትም ጊዜ ዝም ብላችሁ አዳምጡ ተባባሉ። በተጨረሰም ጊዜ አስጠንቃቂዎች ኾነው
ወደ ሕዝቦቻቸው ተመለሱ። አሉም ‘ሕዝቦቻችን ሆይ! እኛ ከሙሳ በኋላ የተወረደን መጽሐፍ በፊቱ
ያለውን (መጽሐፍ) የሚያረጋግጥ ወደ እውነትና ወደ ቀጥተኛ መንገድ የሚመራ የኾነን ሰማን።
ወገኖቻችን ሆይ! የአላህን ጠሪ ተቀበሉ። በእርሱም እመኑ። (አላህ) ከኀጢአቶቻችሁ ለእናንተ
ይምራልና። ከአሳማሚ ቅጣትም ያድናችኋልና። የአላህንም ጠሪ የማይቀበል ሰው በምድር ውስጥ
የሚያመልጥ አይደለም። ከእርሱም ሌላ ለእርሱ ረዳቶች የሉትም። እነዚያ በግልጽ ስሕተት ውስጥ
ናቸው’ (አሉ)።” (አል-አህቃፍ 46፤ 29 -32) ለዚሁ የቁርኣን አንቀፅ ማብራሪያ ዐብዱላህ
ኢብኑ ዐባስ እንዳለው፡- “የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም ለጅኖች ቁርኣንን አላነበቡላቸውም፤ እንዲያውም አላዩዋቸውም ነበር። በአንድ ወቅት ከተወሰኑ ሰዎች ጋር በመሆን ከቤታቸው ወደ ዑካዝ ገበያ ሄዱ። በሰማይ ወሬና በሸይጧኖቸ መካከል ግርዶ ተፈጥሮ ነበር። ሸይጧኖች ሺሃብ /የተቀጣጠለ የእሣት ነበልባል ችቦ/ ስለተለቀቀባቸው አፈገፈጉና ወደ ወገኖቻቸው ተመለሱ። እነሱም / ወገኖቻቸው/ “ምነው ምን ሆናችሁ ነው?” አሏቸው። “በኛና በሰማይ ወሬ መካከል ግርዶ / መረጃ እንዳናገኝ/ ተፈጠረ፤ ሺሃብ /የተቀጣጠለ የእሣት ነበልባል ችቦ/ ተላከብን” አሏቸው። “ይህ የሆነው አንድ አዲስ የተከሠተ ነገር ቢኖር ነውና እስቲ በምድር ውስጥ በምሥራቅና በምእራቡ
ዳርቻዎች በሰፊው ተበተኑና ሁኔታውን አስሱ።” አሏቸው። ከተንቀሣቀሱት ውስጥ የተወሰኑት
የአላህ መልእክተኛ ሰለላሁ ዐለይህ ወሠለም የሱብሂ ሰላትን ሰሃቦቻቸውን በማሰገድ ላይ እያሉ
መጡ። ቁርኣንን ሲቀራ በሰሙ ጊዜ አዳመጡ። እንዲህም አሉ “ወገኖቻችን ሆይ! እኛ ወደ ቀና
መንገድ የሚያመላክት፤ የሚደንቅ ቁርኣን ሰማን። ከአሁን ወዲያ በጌታችን አናጋራም” አሉ። በዚህም የተነሣ አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ በመልእክተኛው ላይ
ﻗُﻞْ ﺃُﻭﺣِﻲَ ﺇِﻟَﻲَّ ﺃَﻧَّﻪُ ﺍﺳْﺘَﻤَﻊَ ﻧَﻔَﺮٌ ﻣِّﻦَ ﺍﻟْﺠِﻦِّ
ﻓَﻘَﺎﻟُﻮﺍ ﺇِﻧَّﺎ ﺳَﻤِﻌْﻨَﺎ ﻗُﺮْﺁﻧًﺎ ﻋَﺠَﺒًﺎ
‘(ሙሐመድ ሆይ!) በል ‘እነሆ ከጂን የኾኑ ጭፈሮች (ቁርኣንን) አዳመጡ። ‘እኛ አስደናቂ የኾነን ቁርኣን ሰማንም’ አሉ ማለት ወደእኔ ተወረደ።’ (አል-ጅን 72፤1) የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ አወረደ።” (ቡኻሪ፣ ሙስሊም፣ ቲርሚዚ፣ ነሳኢን በይሃቂ የዘገቡት) ሃፊዝ አል በይሀቂ ኢብኑ ዐባስን በመጥቀስ እንደዘገቡት ጅኖች ቁርኣንን ለመጀመሪያ ጊዜ በሰሙና ሁኔታውንም ባወቁ ጊዜ በወቅቱ የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ቁርኣንን አላነበቡላቸውም፤ እንዲያውም አላዩዋቸውምም ነበር። ኋላ ላይ ግን ጅኖች ነቢዩን ጋበዟቸው፤ ሄደውም ቁርኣንን አነበቡላቸው። ወደ ሀያሉ ጌታ አላህ (ሱ.ወ)
መንገድም ጠሯቸው። ኢማም አህመድ ሙስሊም አቡዳውድና ቱርሙዚ በዘገቡት ተመሣሣይ ሀዲስ ዒልቀማህ ለኢብኑ መስዑድ፡- “ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ጅኖችን ባገኙበት ለሊት ከናንተ ውስጥ ከነቢዩ ጋር የነበረ ሰው ነበረ ወይ? በማለት ጠየቅኩት አለ። እሱም ‘ከርሣቸው ጋር ማንም አልነበረም። ነገር ግን እርሣቸው መካ በነበሩበት በዚያች ለሊት አጣናቸው። ተገድለው አሊያም የሆነ ነገር ተደርጎባቸው ይሆናል ብለን በማሰብ ‘ምን ሆነው ሆነው ይሆን?’ ብለን ሠጋን። ሁላችንም ለሊቱን የተከፋን ሆነን አደርን። ሲነጋ አሊያም ሊነጋጋ አካባቢ ከሒራእ በኩል ሲመጡ አየናቸው። ሰዎች ያደሩበትን የሥጋት ድባብ ነገሯቸው። እርሣቸውም አንድ የጅን ጋባዠ መጥቶ ወደነሱ ዘንድ ሄድኩኝ። ቁርኣንም አነበብኩላቸው’ አሉ። ከዚያም ሄድን፤ ፋናቸውንና እሣት ያነደዱበትን አካባቢ ፋና አሣዩን። ስንቅ /ምን እንደሚበሉ/ ጠየቋቸው። እርሣቸውም የአላህ ሥም የተወሣበትና በእጃችሁ የገባ አጥንት ሁሉ ሥጋ ይሆንላችኋል። በዕራህ (ኩስ/ፋንዲያ/እበት) ለእንሠሶቻችሁ ቀለብ ይሆናል’ አሏቸው።”ሱለላህ አለይሂ ወሰለም ምርጡ የአላህ ነብይ።

Post a Comment

0 Comments