Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስንቶቻችን ነን ይህን እያወቅን ችላ ብለን “ጆሮ ዳባ ልበስ” ብለን ዝም ብለን ከአላህ ነስር ኧምንጠብቀው??

'ስንቶቻችን ነን ይህን እያወቅን ችላ ብለን “ጆሮ ዳባ ልበስ” ብለን ዝም ብለን  ከአላህ ነስር ኧምንጠብቀው??
 አንድ ወንድሜ ከሰሞኑን ከጻፈው ጽሁፍ ትዝ ብሎኝ ይህን ለማለት ፈለክ በአይኔ በብረቱ ከታዘብኩት ነገር ሳነጻጽር እጅግ አሳስቦኝ  ነው፡፡
በተለይ በጉራጌና በስልጤ ማህበረሰብ አካባቢ አብዛኛው ሃገር ቤት ላይ ኧሚታዩ ችግሮች  ቢሆኑም ከተማም ያለ ሰው   ይመለከተዋል ምክንያቱም ከተማ ኧሚኖረው ሰው ሁኔታዎች ስላልተመቻቸለት እንጂ  ከመተግበር  ወደ ኋላ ኧሚል እንዳልሆነ በተመቻቸለት ሰዓት ሲሰራው እየታዘብን ነው ፡፡እነዚህ ቦታዎች የመረትኩት በቅርብ ስለማውቃቸው እንጂ ለሎችም ቦታዎች የዚህ ተቃዳሽ ይሆናሉ ብዬ እገምታለህ፡፡
ከችግሮቹ መካከል በዋናነት ከሚተቀሱት
1,እዚህ አካባቢ ከሚሰሩ ወንጀሎች ሁሉም ትልቁ  ፊትና እየሆነ እና በላ እያመጣ ያለው ሙሲባ ችርክ(በአላህ  በአምልኮው ማጋራት ነው)፡፡የአላህ ህግ እየገፈፉ ፣ለወንዝ፡ለፏፏቴ፣ለጂን፣ለወልይ፣ሼህ ለሚባሉት,,,ብቻ የቱን ተጠቅሶ ለፍጡር አሳልፎ  ኧሚሰጥበት ቦታ ነው፡፡ከበደሎች ሁሉ ትልቁ በደል የሆነውን ሽርክ የተንሰራፋበት ቦታ ነው፡፡
• አብሬት ሄዶ በአብሬትዬ አባት መቃብር የተገነባው የቁባ መስጅድ ላይ እየተዞረ ጧፍ ይደረጋል፣እየተዞረ በመሬት እየተደፋህ ስጁድ ይደረጋል፡፡ አላህ ከእንዲህ አይነት ዝቅጠት እኛንም ቤተሰባችን ይጠብቀን ይህ አቅል ካለው ሰው ኧማይጠበቅ ተግባር ነበር
• በየጠንቋይ ቤት ደጅ ኧሚጠናውም ሃብት እንዲመጣልኝ፣ልጅ ከሌለ ልጅ ስጠኝ፣ልጅ ኖሮት ካላገቡ ባለትዳር አድርግልኝ ወዘተ በማለት አሁንም ቁጥር ስፍር የለውም፡፡በየሰፈር ተደብቀው ካሉት ውጭ አይና ያወጡት ደግሞ በሰውና በ እንሰሳ አንገት እርዝ ለማሰር በወረፋ ተጨናንቆ በየመንደሮ ኧሚዞሩም ሞልቶዋል እነዚህ ደግሞ የእንትን ሼህ የእንትን ሼህ እየተባሉ ይደሰኮርላቸዋል፡ሌላው ወደ ቡታጀራ ይሴኖ ኧሚባለው ጣንቃይ ንብረት ከጠፋህ እናም መሰል ለሆኑ ድርጊቶች ማን እንደፈጸማቸው ኧማይታወቁ ወንጀሎች እሱ ለይቱ ያውቃል ይባላል ይህ ጠንቃይ ፖሊስም ዳኛም ነው በጣም ኧሚያጅበው አንድ ዘመዴ የሆነ ንብረት ይጠፋዋል ወደዚህ ጠንቃይ ይሄድና ወስዶዋል ለተባለ ሰው መጥሪያ ይዞ አመጣለት መጥሪያው እንግዲህ ከፖሊስ ጣቢያ ሳይሆን ከጠንቃይ ቤት እሴኖ ከሚባለው ግለሰብ ነው፡፡ይህ ጠንቃይ ከፖሊስ ሁላ ይበልጣል አቅሙ የተጠራው ግለሰብ ተጠርቶ ካልሄደ ይገድለኛል ብሎ ስለሚያስብ ወድያውኑ ይሄዳል ታድያ ተጠርጣሪውም ዘመዴ ነበርና አልሄድም ብሎ ጸብ ተነሳ ከዛም ከቆይታ በኋላ ተጠርጣሪው በጣም በጠና ታመመ ይሄኔ ህዝቤ ወሬው ሁሉ የእከሌ ንብረት እከሌ ወስዶታል እናም ሊሞት ነው፣ ማመን አለበት ንብረቱ መውሰዱ፣ ኧሚሉ መሰል ወሬዎች ወደ ቤተሰቡ ይጎርፋሉ፡፡ እየተባለ እየተባለ ሰውዬው ማንንም ያውራ እኔ ንጹህ ነኝም የኔም ነፍስ በ አላህ ነው ብሎ ዝም አለ እየተባለ እየተባለ አላህ ፈዋሽ ነውና ሰውዬው ከበሽታው ተፈወሰ የጣንቃይ የሴኖ ህግ ፉርሽ ሆነ፡ ፡ሌላው በስልጤ ዞን ወደ ሌራ አካባቢ የሌራ ሼህ ኧሚባሉት ወደዚህ ሼህማ ሱብሃነላህ ከስንት እርቀት በቀን በጠዋት ይመላለሳሉ፡፡በየአትክልቱ፡ በየበጉ፡በየፍየሉ እንደየአቅሙ እያየ ሂድና እረድ ብሎ ይሸኛቸዋል፡፡ሌላውም በየገበያውም እንደ ሸቀጥ ነጋዴ ቁጭ ብሎ እርዙን ምናምኑ ይሸጣል፡፡
ሌላው ሚያስገርመው በማታ ጅብ ለየት ባለ ጩኸት ጮኸ፡ቁራ ጮኸ እያለ ያለ እንቅልፍ ኧሚያድረው ነው፡፡ለምን የፈራ መሰላቹ የሆነ ሰው ይሞታል እያለ እኮ ነው  እንደው አጂብ እኮ ነው  ብቻ ባጠቃላይ ሽርክ በእግሩ እየሄደ ነው  ለዛውም በቀስታ ሳይሆን በሩጫ ነው እንጂ
• እናት አላህ የአብራክ ክፋይ ከሰጣት በሃላ ስምንት(8) ልጅ ወለድክ አስር(10) ልጅ ወለድክ አስራ ሁለት(12) ወለድክ ብላ ስምንት የወለደችው አሮጌ ብዙ ግልገል የወለደች በግ ታርዳለች፣ከዛ በላይ ከሆነ አሮጌ ብዙ ጥጃ የወለደች ላም ታርዳለች ይህ ውሳኔ ኧሚተላለፍላት በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ  የጎር በሚባል አካባቢ ላይ ሳምር ኧምታስጨርሰዋ ሴት ነች፡፡ሳምር የድርጊቱ ስም ነው፡፡የሷን ቤት ኧሚሄዱ ሴቶች የሃገር ቆጮ ፣ቅቤው፣አይቤው ሌላውም ተሸክመው ለብዙ ሰኣታት ኧሚፈጅ ጉዞ  ይሄዳሉ፡፡ ይርቃል የተባለው ገጠር እስከ 7፡00 ሰአት ከአዲስ አበባም ኧሚሄዱ እንዳሉ ሰምቻለህ፡፡ ለሴቷ ይህን ሁላ ይገበርላታል አጂብ እዛ የሄደ 1ወንድሜ እንዲህ አለኝ ያን ሁላ ተሸክመን ሄደን ለሷ ገበርን ግን ልጆቿ ሲታዩ ምግብ የበሉ ይቅርና ስሙን ሚያውቁ አይመስሉም አለኝ ምን ያድርጉ ለጅን እየገበሩ!!!
• ምንም መሰረት የሌለው ማክሰኞ እና ሃሙስ ቀን ለየት ያለ ቆጮ(ዳፗ) ተጋግሮ አዲስ አበባ ቆጮ ከሌለ ሩዝ በምትኩ በማድረግ በሳምንቱ ለየት ያለ ምግብ ተዘጋጅቶ ኢድ ተደርጎ ይያዛል ከበሮው ሲመታ ለይሉን ያነጋዋል፡፡የዛን ቀን ይህ ካልተደረገ በላ ይመጣል የሞቱ አሟቶቻችን በረሃብ ዋሉ በራፍ ላይ መተው ሲጠብቁ አደሩ ኧረ እንደው አቅል ሚባል የለም ሌላው ሚያጅበው በዚህ ምግብ ቅመሽ ተብላ ኧምትሰጥ ጎረቤት ካለች ከቀረባት በጠዋት መታ በር ታንኳኳና ለምን የማክሰኞ ወይም የሃሙስ ቡና አልተፈላም ብለው አሟቶች ላኩኝ ትላለች ኧይ ሆዳሞች አስቸገሩ እኮ፡ሌላው ከገጠመኝ ሃገር ቤት ላይ ስለዚህ ቀን ሁሌ ዳዋ ያደርግ ነበር ከዛም ይህ የሰማ ሆዳም (ዳፗ የጀነት ምግብ ነው ብሎ እርፍ) እንደው ለዚ ሰው ምን ይባል አላሁ ሙስተዓን፡፡ ሁሉም ቀን ይከበራል ሰኞ እስነይን(ሊቃ)፣ማክሰኞ የአባታችን ቀን(የአሬት)፣እረቡ የአብድልቃድር ጅላል፣ሃሙስ የፋጢማ፣ቅዳሜ የሰይድና ኸድር በለው ጋዳቸው ስንገባ አሉ ሸህ ሙሃመድ ወሌ አላህ ይርኸማቸው፡፡
2,የወላጅ ሃቅ ኧሚባል በጭራሽ የለም ማለት ይቻላል ትላንት ልጄ ልጄ  እያለ ነጋ ወይ እያለ ወቶ ጸሃይ የለ፡ዝናብ የለ፡ ድካም የለ፡ዛሬ አሞኛል ህመሜን ላስታግስ ሳይል ቀን ሙሉ እየሰራ፣ብጣሽ ጨርቅ እላዩ ላይ አድርጎ፣ ጫማ ኧሚባለው ስሙ ሳያውቅ፣ላንተ/ቺ ብሎ ከሰው እርቆ፣ከሌላ ሰው ልጅ የበታች እንዳትሆን የሰው ፊት ገርፎት ስንቴ ተዘልፎ፣ተደብድቦ አልቅሶ፣ ክብሩን አቶ ያንተ/ያንቺ ክብር ለማስከበር፣ከቀዬው ተሰዶ፣እሱ ሳይበላ ልጄ ብሎ  ዳቦ እና እንጀራ አንጠልጥሎልህ/ሽ ሲመጣ፣ያለ እንቅልፍ ሲያድር፣ሳይማር እያስተማረህ ሳይቀራ እያስቀራህ፣ ብቻ የቱን ተጠቅሶ ይህ ለሆነው አባት ይህ ነው ኧሚገባው?ኧረ ልድገመው ይህ ለሆነው አባት ይህ ነው ኧሚገባው?
 ዘጠኝ ወር በሆዷ ህመሙ ቁርጠቱ እንደው የከባዱስ ምጥ ኧሚሉት የሞት የሽረት ሂደት ይህን ሁላ ያለፈቿ እናት፣ሽንትህ/ሽ እየጠረገች፣እየበላች፣አንዴ ጀርባዋ ላይ፣አንዴ እግሯ ላይ፣አንዴ ደረቷ ላይ ተሸክማ አሳድጋህ/ሽ፣ያንተን/ሽ የእግር እሳት ለሷ በሽታ እየሆነባት፣ስንት አሷራን የበላች እናትስ ይህ ነው ኧሚገባት?ኧረ ልድገመው ይህ ለሆነችው እናት ይህ ነው ኧሚገባት?
ለአባት እና ለ እናት ዱላ,,,,,,,,,ስድብ,,,,,,ግልምጫ,,,,,ነው ሚገባቸው ያረቢ አቅል ስጠን ዛረ እኮ ህጻን ልጅ አፉን በምን እንደ ሚፈታ ታውቃላቹ  መቼም በአላህ ቃል እንደማትሉኝ አስባለህ ህጻን ልጅ አፉን ኧሚፈታው እናትህ እንዲህ ትሁን እናትሽ እንዲህ ትሁን ኧረ ጊዜው በጣም እኮ ነው ኧሚያስፈራው
ሌላው ሚያጅበው አባት እናቱ ቤታቸው እሳት አተው እሱ ለዚህ ያደረሱትን ወላጆቹን ችላ ብሎ ከሚስቱ ከልጆቹ ቤቱ ዘግቶ ደሰታል እነሱ በርሃብ እየተቸገሩ፣ለላው ወታት ነኝ ባይ በሱስ ተጠምዶ የነሱ ላብ እየሰረቀ እያታለለ በቀን የመቶ የሁለት መቶ ጫት ይቅማል እነሱ ለ እግራቸው ኤር ገንዶ አተዋል፣እሱ ገብቶ ይጨፍራል፣
3,ጉርብትና ቀረ ሁሉም እርስ በርስ መመቃኘት ከዚህ በፊት አሉ አንድ ቤት እራት ከሌለ ያንዱን በጋራ ይበላ ነበር ዛሬ ሃብት ሲመጣ እንካን ለምግብ መገናኘት ሳይገናኙ ሳምንት ሊቆዩ ይችላሉ፡፡መተባበር የለም፣መተዛዘን ቀረ በቃ ድንበሩን ታልፎ አይመጣም የአደጋ አጥር አለ ኧሚያጅበው ኧሚገናኝ ጎረቤት እንኳን ቢኖር ለሃሜት እንጂ ጎርብትና ለማጠንከር አይደለም ወይም ሃላል ያልሆነ ጉርብትና ለማጠንከር ሂስድ ለማጠናከር ነው
4,ዝምድና ስሙም የለም ድሮ በአራተኛ አያት ኧምንገናኝ ሰዎች እንደ እናት ልጅ እንተያይ ነበር ይላሉ አባቶች ሲተየቁ አሁን የገዛ ወንድም እና እህት ዘመድ አይደሉም በትዝብት ሲያወሩ እውነታቸውን ነው፡፡ዝምድናን ተቆርጦዋል እንደው አዲስ አበባ ብሶበታል በቃ ሳምንት ሙሉ መርካቶ ይውላል በሳምንት አንድ ቀን ለዚህ ትልቅ ኸይር ስራ አይሰጥም፡፡ኧረ ረጋ እንበል እና እናስብበት ይቺ ዱንያ አታጥፋን
5,ወለድ እየታጨደ ነው በባህላዊም በዘመናዊም የወለድ አሰራር በዚህ በርካታ ሰው እየታመሰ ነው ወለድ በብር ብቻ አይደለም የጎሳ እድር  እየተባለ በከተማ በገጠር ከካፊር ጋር ተቀላቅሎ ብሩን በወለድ ያበላሻል ገና ለገና ሰው የሞተ ቀን ይተቅመኛል እቀብርበታለህ እያልክ አንተ እራስህ ሞት ይቀድምና እንኳን ሌላው ልትቀብርበት እሳትን ወርሰህበት ነው ኧምትሄደው እና ከሞት በኋላ ላለው ህይወትህ ዱንያ ላይ ኧምትሰራው ኸይር ስራ እና የሰራኸው ሸር ስራ ነው ኧሚዳኙህ፣ስለዚህ የጎሳ እድር ምናምን እያልን አሄራን አናበላሽ፣፣ሌላው በንብረት የሆነ ምርት ከተበደረ ጨምሮ ማስከፈል ይህም ወለድ ነው ፡፡
6,ሌላው የዘመኑ ሰለጠን እያሉ መሰይጠንን የተጠናወታቸው ወጣቶች ወንዶችም ሴቶች በየቦታው፡በገበያ፡በትምህርት ቤት፡በጭፈራ ቤት በዝሙት እየተጨማለቁ ስሜታቸው ተከትለው ስንቶቹ ክብር እያጡ ይገኛሉ፡ለጥቂት ሰዓታት ስሜታቸው ለማብረድ የዘላለም ጦስ እየሆኑ ከራሳቸው አልፈው መዘዙ ለቤተሰብ መትረፉ፡ለብዙችግር እየዳረጉ እያየን ነው ፡፡ይህ ደግሞ በአሁን ሰዓት ጆሮ እስከሚሰቀጥጥ ድረስ በየመንደሩ እንደ ሚዘወተር  ንግግር  ደህና አደርክ ደህና ዋልክ እንደሚባል ቀለል ተደርጎ ይወራል፡፡
እናም እነዚህ ሁላ ወንጀሎች እየተሰሩ ዱንያም አሄራችን እያበላሸን ነው በዚህ አላህ በላ እንዳያመጣብን ምን ያህል ሰግተናል የአላህ ቅጣት ሲመጣ ሷሊህ ነው ዟሊም ነው የለም ጥርግርግ ነው ኧምትለው ይሀው አሁን በዚህ ሰዓት ስንት ነገር እየሰማን ነው እያየን ነው ዝናብጠፍቶ ሰው እና እንሰሳ ኧሚጠጣው ተቸገረ፣ለመጠጥ በእድሜ የገፉ አባቶች እስከ ሁለት ሰኣት ይጋዛሉ እሱም ለወረፋ ስንት ሰዓት ተደቅነው፡ከብቶች ኧሚበሉት ኧሚጠጡት የለ አልኸምዱሊላህ ትናንትና አዲስ አበባ መዝነቡ ሰምቻለህ አላህ በራህመቱ በሁሉም ቦታ ዝናቡን ለሚፈልጉ ያዝንብልን፣በየቦታ የቤት ቃጠሎ እንሰማለን በሰፈር መደዳ በቃ በቁጥር 20፣30፡50 ምንም አይመስለን በቅርብ ሃይለኛ የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በስልጤ ዳሎቻ ወረዳ እና እስከ ጉራጌ ምስራቃዊ ክፍል በቃ አውርተን መተው ምንድነው?ለምን ይሆን?ምን ይሆን ወንጀላች?ታድያ ለማን ነው አቤት ኧምንለው?
አንዱ ምን ሲል ሰማህ ከዚህ በፊት ዝናብ ሲጠፋ የሆነ ቦታ ይሰበሰቡና ሙስሊሙም ካፊሩም አላህን ይለምኑ ነበር ግን አላህን ነበር ሚያጹት እንደለመደው እዛ ቦታ ቁጭ ብለን ዱዓ ስላላደረግን ነው አለ፡፡የ አምስት ወክት ሰላት በትክክል እንኳን አይሰግድም እዛጋ ስላልበላ ስላላረደ፣አሁን ህዝቡ ትንሽ አቅሉን ተጠቅሞበት ይሁን የዝናብ ሴት ትሙት አላቅ በፊት እሷን ብር ይከፈልላት ይባል ነበር ምክንያቱም ዝናብ ኧምታዘንበው ሴት ግቦኛ ነች እና ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን ብር ይሰጣት እና ታምቧቧው ይባል ነበር አሁን ይቅር አይቅር አላቅም ከጥቂት አመት በፊት ነበር 
እንዴት ነው በንደዚህ ሁኔታ አላህ ዱዓችን ኧሚቀበለን 
     ነብዩ ሰለላሁአለይሂ ወሰለም አንድ ሰው አስታወሱ መንገድ የረዘመበት ነው አሉ፡፡ጸጉሩን የተንጨባረረ አቧራ የነፈሰበት ይመስላል ይህም ሰውዬ እጁን ወደሰማይ አንስቶ ያረቢ ያረቢ ያረቢ እንዲህ,,,,,,,,,አድርግልኝ ብሎ ይለምናል አሉ፡፡ ቀጥለው እንዲህ አሉ ኧሚበላው ሃራም፣ኧሚጠጣው ሃራም፣ኧሚለብሰው ሃራም፣ሰውነቱ የተገነባው በሃራምነው አሉ ታድያ እንዴት  አላህ የዚህን ሰው ዱዓ ይቀበላል ፡፡ሙስሊም ዘግቦታል ፡፡
     ሽርክ በየቤቱ እየተሰራ፣የቢድዓ ማት እየተንሰራፋ፣የወላጅ ሃቅ ተጥሶ፣ዝምድና ተቆርጦ፣ጉርብትና ጠፍቶ፣በየመንደሩ ዝሙት እየተሰራ ታድያ እንዴት ነው ነስር ኧምንጠብቀው፡፡እንዴት ነው የአላህ እርዳታ ኧሚመጣልን
       አላህ በህዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ  በነፍሶቻቸውን ያለውን (ሁኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለውም፡፡ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸውም፡፡(አር-ረዕድ ቁጥር 11)
   ሁላችንም ወደ አላህ እንመለስ ሁሌም ወደ ተውሂድ እንጣራ እንጥራ ፣ከሽርክ  እናስጠንቅቅ እንጠንቀቅ፣ ሱናን እናስተምር እንከተል፣ ከቢዳ እናስጠንቅቅ እንጠንቀቅ፣የወላጅ ሃቅ እናስተምር እንጠብቅ፣ዝምድና እንቀጥል፣የጎረቤት ሃቅ እንውጣ፣ከፈሳድ እንራቅ፣ከተማ ያለኸው/ሽው ወንድሜ እህቴ ስሙኝ ብዙ ኔእማ በጃቹ አለ ባላቹ ኒዓማ ቤተሰባቹ አስተምሩ፣የዳዕዋ ስራ እንዲሰራ አድርጉ፣የዲን ትምህርት በየሰፈር እንዲኖር አድርጉ መልክቴ ነው፡፡
          ያረቢ ወደ አንተ ቅን መንገድ በሃቅ ኧሚጣሩ ዳዕዋት አብዛልን እኔና መሰሎቼ ሃቅ የሆነውን እውቀት አሳውቀን የምንቀበለው አድርገን
        ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ'

ወሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ