Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሸይጧን አንድን የአላህ ባሪያ እንደምንም ጥሮ ተንጠራርቶ የሽርክ ማኖ ሊያስካው ይታገላል።

ሸይጧን አንድን የአላህ ባሪያ እንደምንም ጥሮ ተንጠራርቶ የሽርክ ማኖ ሊያስካው ይታገላል።
በዚህ ዙር ብዙ ሰዎች ፈተናውን ይወድቁና ለሸይጣን የደስታ ጮቤ መርገጫ ሰበብ ይሆኑታል!
ነገር ግን “ሞኝህን ፈልግ አጅሬ!” ብሎ በተውሒድ ላይ ሙጭጭ ያለን የአላህ ባሪያ በመጀመሪያው ዙር ማለትም ሽርክ ሊጥለው ስላልቻለ ወደሁለተኛው ዙር ይሸጋገራል ። ይህም ቢድዐ ነው!
በዚህም ብዙ ሰው ይወድቃል! ይፈጠፈጣል! ። እንደውም ብዙ ጊዜ ሸይጣን በዚህ ዙር ከሚጠቀማቸው መሳሪያዎች ውስጥ የታንክና የኒውክለር ቦምቡን ድርሻ የሚይዙት ሙስሊም የሆኑ አንዳንዴም በ‘ሸኽ’ ስም የሚታወቁ አሊያም በ‘ሙጃሒድነታቸው’ አገር ያወቃቸው የጥመት ተጣሪዎችን ነው። ሕዝቤ አፉን ከፍቶ ‘O’ ብሎ ሲሰማቸው በሚጣፍጠው አፍዝ አደንግዝ ንግግራቸው መሃል ያቺን ለስላሳ ቢድዐ ጉርስ ያደርጉታል ። ሕዝቤም አብሮ ቢድዐዋን አጣጥሟት ዋጥ!
ከዚያማ ‘አረረ! ይቺ አብረህ የዋጥካት ነገር እኮ መርዝ ናት’ ስትል አለቀልህ! ያኔ ሸይጧን ወየው ደስታው!

ሶስተኛና አራተኛ ዙርም አለ!
አንዳንድ አላህ ያዘነላቸው (እነኚህ በቁጥር ብዙውን ጊዜ አነስተኞቹ ናቸው) ባሮቹ ‘እምቢኝ! ተውሒዴና ሱናዬንማ ለሽርክና ቢድዐ አሳልፌ አልሰጥም! ’ ሲሉ ሸይጧን ተስፋ ከመቁረጡ ጋርም አርፎ ግን አይቀመጥም! ከምን ይጀምራል መሰላቹ?
ከትላልቅ ወንጀሎች (ነፍስ ማጥፋት፣ዝሙት ...)
ይህ አልሳካ ካለው ወደትናንሾቹ ይቀጥላል እንጂ ተስፋ አይቆርጥም!
አንባቢ ሆይ! አደራህን በቅድሚያ አበክሬ የምመክርህ በመጀመሪያው ዙር እንዳትወድቅ! ምክንያቱም እሱ የፍርዱ ቀን የአላህን ማህርታ የማያስገኝ ታላቅ በደል ነውና!
ቀጥሎም ሁለተኛው ዙር ታላቅ አደጋ አለው እንደየአይነቱ አንዳንዴም ከመጀመሪያው ዙር ጋ ሊቆራኝም ይችላል! ከሱም አልፎ የታላቁ የሰው ልጆች አለቃን ሃውድ ከመጠጣትና ነጃ ከመውጣት ያሳግድሃል! አስኪ በህይወትሕ ስንት ጊዜ ይሄን ሃዲስ ሰምተሀዋል? “ረሱል እያለቀሱ (ወይንም ተክዘው መሬቱን ጫር ጫር እያደረጉ) ‘ወዳጆቼ ናፈቁኝ’ ባልደረቦቻቸው ጠየቁ “እኛስ ወዳጆቾት አይደለምን?” “እናንተ ጓዶቼ ናቹ! ወዳጆቼማ ሳያዪኝ ያመኑት ናቸው! ” አሉ ። ታዲያ ይህን ሃዲስ ስተሰማ በደስታ አልፈነጠዝክም? ሃቢቢ ብለህ አልዘለልክም?
ግንማ .... ስማኝማ! ሱና ላይ ከሌለህ፣ ቢድዐ ላይ ካለህ መርዶ ልንገርህ! እኚው የናፈቁህ የሰው ልጆች አለቃ ያኔ በፍርዱ ቀን ጥማት አናትህ ላይ ወጥቶ እሳቸውን ወደጎንና ወደፊት ሩቅ የሚያስኬደው ሃውዳቸው (ኩሬ) አጠገብ ቆመው “ዑመቴ ዑመቴ ኑልኝ ወደኔ!” ሲሉ አይተህ እኚው የናፈቁኝ ታላቅ ሰው ከሃውዳቸው ያስጠጡኝ ብለህ ብትጠጋ በመላዒካዎች ድርሽ እንዳትል ትከለከላለህ! አዎ! ረሱልማ እያዪህ ነበር (ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም) ደግሞ ጠየቁልህ! “ለምን ከለከላቹት እናንተ መላዒካዎች ሆይ! እሱኮ ከዑመቴ ነው” ሲሉ አብጠርጥረው የሚያውቁህ መላዒካዎች ምን ይመልሱላቸዋል መሰለህ? “ተወው! እሱን አታውቀውም! አንተ ከሄድክ በህዋላ እምነቱ ላይ ምን አዲስ ነገር (ቢድዐ) እንደፈጠረ አላወቅክም” ሲሏቸው ይሄኔ ቆጣ ብለው የፋጢማ አባት “አርቁልኝ! አርቁልኝ!” ይሉሃል! ታዲያ የናፈቁት ማንን ነው? የናፈቁትማ ሱናቸውን ቀጥ አድርጎ የያዘ ቢድዐን የራቀውን ነዋ!
ታዲያ ምን ጠበቅክ ጃል?
ዛሬ ‘ቢድዐ ነው አትስራው’ ስትባል ‘እከሌን ዳዒያህ’ ብለህ የገባህበት ማጥ የኚህን ታላቅ ሰው ናፍቆት ሊያሳጣህ?
አረረ ጥንቅር ብሎ ይቅር ይሄ ቢድዐ የሚሉት ጉድ!
ለዚያም ነው ታላቁ ቀደምት ዓሊም ጉዳጉዱን ቢያውቁት እንዲህ ብለው ክፋቱን የነገሩን ...
«ቢድዐ ሸይጧን ዘንድ ከወንጀል የበለጠ ተወዳጅ ነው! »
ታዲያ ወንጀልም ቀላል እንዳይመስልህ! ከላይ ላሉት መረማመጃ ድልድይ ነውና ድልድዩን በመልካም ስራዎችህ ሰባብረህ ጣለው!

Post a Comment

0 Comments