Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እራስን "ሰለፊ" ብሎ መጥራት ይቻላል ወይ?
______________
እራስን "ሰለፊ"ብሎ መጥራት ሁለት አይነት ነው::
1)ልክ እኔ ሙስሊም ነኝ ብለን እንደምንናገረው ከሙስሊሞች
መካከል ያለህን ትክክለኛ አቇም ለሰዎች ለመጥቀስ ሲያስፈልግ
ልብ በሉ {ሲያስፈልግ}ችግር የለውም::እንዲያውም አስፈላጊ
ግድ እሚሆንበት ቦታ አለ ምክንያቱም ቁርኣንና ሐዲስ ነው
ምንከተለው ብትል ሁሉም ምቁርኣንና ሐዲስ ነው ምንከተለው
ይልሃል ኻታ ሺዓ ከሱና ተከታዮች በጣም የደከሙ እንኯ ሆነው::
መጨረሻ ላይ እምንለየው እንክርዳዱን ከስንዴ "እኔ ሙስሊም
ነኝ ሱኔ በሰለፎች አረዳድ" ከምትል እረጅም ወሬ ከምታወራ
እንደው መቼም ከቇንቇ አንፃር "ኸይሩል ከላም ማቀለ ወደለ"
አይደል?ጥሩ ንግግር እሚባለው አጠር ብሎ መልፅክቱን
እሚያስተላልፍ ነው ባጭሩ ምን ትላለህ "ሰለፊ"ነኝ ብለህ
ትገላገላለህ!ሰለፎችን የተከተለ እንደማለት ነው::ወይ የነሱን
ግንዛቤ መሠረት ያደረገ ቁርኣንና ሐዲስ እንዳለ ሆኖ::የአንድ
የሁለት ሰለፊን አይደለም ሀንበሊ ነን ሶፊያኒ ነን ሀማሪ ነን
አንልም ምንድነው እምንለው "ሰለፊ"የሁሉም ማለት ነው ይሄ
ደግሞ ከኢጅማ አንፃር ካየናቸው /መዕሱም/ጥብቅ ናቸው
ሁሉም አንድ ላይ አይሳሳቱም ሁሉም ስህተት ውስጥ ይወድቃሉ
እንዴ?በግለሰብ ደረጃ ሊሳሳቱ ይችላሉ ማንኛውም ሰው ቢሆን
ይሳሳታል ከረሱል /.../ በስተቀር::
ይሄ በድሮም ጊዜ የነበረ ነው::"ሰለፊ"የሚለው ቃል አሁን የመጣ
እንዳይመስላችሁ ከድሮ ጀምሮ ዑለሞች ይጠቀሙበት
ነበር::ሰምዓኒ በ5-6 ክፍለ ዘመን የነበረ ዐሊም /አል-አንሷር/
እሚል ኪታብ አለው "ሰለፍ" እሚለው በደንብ በ"ፈታ" "ሲን"
"ወላም" ብሎ ይሄ ማለት ከሰለፎች እራሱን ያስጠጋ ነው ይላል::
ኢብኑል አሲር የሱን ኪታብ ታዐሊቅ ሲያደርግበት በ7 ክፍለ ዘመን
የነበረ ዓሊም ነበር ምን ይላል ብዙ ሰዎች ታውቀዋል በዚህ ስም
ድሮ እኮ ነው!ገባችሁ አይደል አል-ኢማሙ ዘሀቢ የተለያየ
ኪታቦቹ ላይ ጠቅሷል ኢብኑል ሐሰን ዳሩል ቁጥኒ
"ሰለፍ"እሚለውን ቃል ተጠቅመዋል ኢብኑ ተይሚያ:-"በኢማሙ
አህመድ ዘመን ሰዎች ብዙ ጣኢፍ አልነበሩም ጀህሚያ እና
ሰለፍያ" ይላል::ከቀደምቶች ብዙ ሰዎች መጥቀስ ይቻላል
እሚዘረዘር አይደለም:: ከዘመናችን ካሉ ዑለሞች መካከል ይሄ
ችግር እንደሌለበት በተለያየ አጋጣሚ አበክረው የተናገሩ
በርካቶች ናቸው::ግን አንዳንድ ሰዎች እሚያነሱት ምንድነው ይሄ
መከፋፈል አይሆንም ወይ? ከተባለ አይሆንም!ሙስሊሞች
ተከፋፍለዋል ከሺዓውም ከምኑም አንድ ነኝ ከምትል ማንነትህ
እንዲታወቅ ስትፈልግ ባጭር ቃል መናገር ነው::ሌላ ምንም
ትርጉም የለውም አይ ይሄ /ተዝኪያ/ነው እራስን አጥርቶ ሌላውን
መናቅ ነው ካለ አይሆንም ካላሰብክበት በስተቀር በትትክክል
ከሆነ አልሃምዱሊላህ! "ከጌታህም ፀጋ አውራ /ግለፃት/"
93:11
ኩራተኛ እንዳልባል ብለህ ጀህሚ ነኝ ትላለህ እንዴ? ይሄ ተዝኪያ
ነው ከተባለ ሙስሊም ነኝ ማለትስ ተዝኪያ አይደል መጥፎ ነገር
ነው እንዴ? ይሄ ተዝኪያ አይባልም ሊታወስ እሚገባ ርዕስ
ነው::እሚያጨቃጭቅም አይደለም:: በምን ግንዛቤ ተገንዝበውት
ቢድዓ ነው ሲሉ አልፎም ተርፎ ሙስሊሞች በዚህ መጠሪያ
መጠራት የለባቸውም እሚሉት አንዳንዱ ምን ይላል አላህ
በቁራኑ ውስጥ "ሙስሊም" ነው ያለን ይላል ጠይብ"ሰለፊ"ነን
ያሉ ካፊር ነን ብለዋል? ሙስሊም አይደለሁም የሚል ሰለፊ
የለም!::አንድ ሰው ሙስሊም አይደለሁም ካለ ካፊር
ነው::ሙስሊሞች በዝተዋል ሀቅን የተከተለው የትኛው ነው
ከተባለ በሰለፎች መንገድ የተጏዘው ነው::ለምን
ከተባለ=>"ከስደተኞቹና ከረዳቶቹም ሲኾኑ የመጀመሪያዎቹ
ቀዳሚዎች እነዚያም በበጎ ሥራ የተከተሏቸው አላህ ከነሱ ወዷል
እነርሱም ወደዋል..."/9:100/
ያ ማለት ነው እንደመጠሪያ ነው ሲያስፈልግ::
2)ራስን በማጥራት መልኩ ሳይጠየቅ ማነው ስምህ ሲባል ፉላን
ኢብኑ ፉላን ኢብኑ ፉላን- አሰለፊ ይላል በያጋጣሚው ኪታብ
ሲፅፍም እንዲሁ
ጥሩ አላማ ሊኖራቸው ይችላል ግን እራስን የማጥራት ሽታ
ሊኖረው አይገባም ወይም ሰውን ለመከፋፈል ታስቦ መሆን
የለበትም::አለበለዚያ ግን ሃቁን ከሃቅ ከማስቀመጥ አንጻር ምንም
ችግር የለውም::!ከድሮ ዑለሞች የተገኘ ነው::
__________
ኡስታዝ ኤልያስ አህመድ ከሰጠው ደርስ የተወሰደ ሃፊዘሁላ
ወረዓ!!! —

Post a Comment

0 Comments