Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በአጋጣሚ ሕክምናን ፈልጋቹ ከታች ወደተገለፁት ሰዎች ከሄዳቹ ፊታቹን አዙራቹ ወደመጣቹበት ተመለሱ ።


በአጋጣሚ ሕክምናን ፈልጋቹ ከታች ወደተገለፁት ሰዎች ከሄዳቹ ፊታቹን አዙራቹ ወደመጣቹበት ተመለሱ ። ሌሎችንም ወደዚህ ቦታ እንዳይሄዱ አስጠንቅቁ!
★ ስማቹን፣ የእናታቹን ስም ወይንም የትውልድ ቀናቹን ከጠየቃቹ
★ ፎቶዋቹን ወይንም ከልብሳቹ (ቁራጭ ወይንም ሙሉ) ከጠየቃቹ
★ ከፀጉራቹ ፣ ከጌጣ ጌጣቹ ወይንም ከናንተ ጋር የተዛመደ መጠቃቀሚያቹን ምንም ነገር ከጠየቃቹ
★ የእርድ እንስሳ (ለመስዋትነት) ይዛቹ እንድትመጡ ከጠየቃቹ
★ የሚጠለቅ ነገር ወይንም የሚንጠለጠል ሂርዝ ነገር እንድታደርጉ ከሰጣቹ
★ ወደርሱ ስትሄዱ ከናንተ ጋር አብራቹ ሕፃን ልጅ እንድታመጡ ከጠየቃቹ
★ እናንተ በማታውቁት ለየት ያለ ቋንቋ ሲያንሾካሹክ ከሰማቹት
★ ከቁርአን ወይንም ከሱና ዱዐዎች ውጪ ሲያነብ ካያቹት
★ ሊነካካቹ ከሞከረ (ሴት ከሆናቹ)
★ “በዚህን ያክል ገንዘብ ካልሆነ አትድኑም” ካላቹ
★ ከመጠን ያለፈ የተጋነነ ገንዘብ ከጠየቃቹ
★ እጃቹን ወደ ውሃ ውስጥ ስደዱ ካላቹ ወይንም በውሃ ማቅረቢያ እቃ ውስጥ “ጂኒውን ያዙት” ካላቹ
★ ዶቃ፣ ጨሌ፣ ሉል ወይንም ድንጋይ እንድትይዙ ወይንም በቀለበት እንድታደርጉት ከጠየቃቹ
★ ስላሳለፋቹት ክሰተት ካወራቹ ወይንም “የወደፊቱን አዋቂ ነኝ” ካላቹ
★ ጭሳ ጭስ ካጤሰባቹ (ብዙውን ጊዜ በጨለማ ውስጥ ቁጭ ብሎ)
★ስለ ‘ስኬታምነቱ’ ከፎከረ ወይንም ጉራ ከነዛባቹ
እነዚህና መሰል ምልክቶች የጥመት ሰዎች መለያዎች ናቸው ። ከጋኔን (ጂኖች) ጋር የሚተባበሩ ወይንም ጥንቆላን የሚተገብሩ ሰዎች በመሆናቸው ወደነዚህ ሰዎች ሕክምናን ፍለጋ መሄድ አይቻልም ። የሚሄዱ ሰዎችንም የምናውቅ ከሆነ ማስጠንቅ ይኖርብናል ።
ከሽርክ እንጠንቀቅ፣ እንራቅ !