Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሰሞኑ የሃገራችን ዐቂዳ ነክ አበይት ዜናዎች

'‎የሰሞኑ የሃገራችን ዐቂዳ ነክ አበይት ዜናዎች

አንባቢ ሆይ ስማ ..!
ይህን ዜና የምለፍፍልህ ሰምተሀው እንድትደሰትበት አሊያም ከንፈርህን እንድትመጥ ሳይሆን እጅህን አንስተህ ለፈጠረህ ጌታህ ዱዓ እንድታደርግ ነው ። እንጂ እንደነ እንቶኔ «ዓላማዬ... የመረጃ ክፍተት እንዳይኖር መስራት ነው» ብዬ ዟሊም ባለስልጣን በላ፣ ፈሳ ልልህ እንዳልሆነ እወቅልኝ ። አላህ የሱን ፊት ከጅለው ከሚሰሩት ያድርገን 
መልካም ንባብ... 

① በሐረር ከተማ የሺዓዎች ቤት-አምልኮ(“መስጂድ” አልልም ብዬ ነው) መገንባቱ ተሰማ። ሆኖም .. “ለጊዜው ጎብኚ (“ሰጋጅ” አልልም ብዬ ነው) የለም” ተብሏል። ከዚህ ቀደም እዚሁ የሐረር ከተማ ውስጥ የሁሴን እና የሀሰን ሙሾ ስነ-ስርዓት ብለው በተከበረው የአሹራ ቀን ህዝቡን ሲያምታቱ የነበሩት ሐረር-አፈራሽ ሺዓዎች ከውጪ ሃይላት በሚያገኙት የገንዘብ ዕርዳታ የመጀመሪያው ነው ተብሎ የሚገመተውን የሺዓ መስጂድ አቋቁመዋል ። ከዚያ አካባቢ የሆናቹ ወንድሞችና እህቶች ወደፊት ይህን የሺዓ ቤተ-አምልኮ የሚሞሉት የናንተው ቤተሰቦች ሊሆኑ የሚችሉበት አጋጣሚ ሳይከሰት ቤተ-ዘመዶቻቹን ከወዲው አስተምሩ!! ከሺዐ መርዛማ እምነት አስጠንቅቁ!! ። ባረከላሁ ፊኩም ። ከዚህ በፊት እኔ ፀሃፊው ኢትዮ' ስለሚገኘው የሺዓ እንቅስቃሴ አጠር ያለ ባለ ሁለት ክፍል ኖት ከነማስረጃዎቹ አስነብቤ እንደነበር የሚታወስ ነው። አላህ ከሃገራችን ጠራርጎ እንዲያስወጣቸው ሁላቹም ዱዐ ማድረጉን አትርሱ ።

② በስልጤ ዞን ውስጥ የሚገኙ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ መነሳቱንና ድርቅ መከሰቱን የዞኑ ተወላጆች አሳወቁ ። በተመሳሳይ ባለፉት ሳምንታት በዞኑ ከየት እንደመጣ የማይታወቅ እሳት ከ18 በላይ ቤቶችን በተርታ አቃጥሏል።   እንደሚታወቀው የስልጤ ዞን ውስጥ ብዙ የሚመለኩ ቀብሮች የሚተገበሩ ሽርክና ቢድዐዎች መኖራቸው የሚታወቅ ነው። 
 የዞኑ ተወላጅና የብሔሩ አባላት የሆናቹ ሙስሊሞች ቤተሰቦቻቹን ከሽርክና ቢድዓ መሰል ወንጀሎች እንድታስጠነቅቁ በአላህ ስም እጠይቃለው ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህም በስልጤ ዞን የሚገኙ ገበሬ አባቶች መንግስት በቀየሰው መርዛማ የሪባ (የወለድ) ብድር አማኻኝነት ብዙዎቻቸው ተታለው መግባታቸውን ከዞኑ ከመጡ ሰዎች እየሰማን ነው። እንዲሁም የቀን አምልኮ ፣ ራጋ (ጠንቋይ) ጋር ሄዶ ልጅና ሃብት የመጠየቅ ፣ የሲሕርና የመሳሰሉት ከጀነት የሚያርቁና አላህ ይቅር የማይላቸው ወንጀሎች በጣም እየተስፋፉ እንደሆነም እየሰማን ነው። ታዲያ አላህ ለምን አይቅጣን? ስለዚህ ዱዐቶችም ወደዞኑ በመሄድ ሕዝቡ ወደ አላህ እንዲመለስ ጥሪ እንዲያደርጉ እናበረታታቸው እላለው። አላህ ከፈተና ይጠብቀን

③ በሃገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ ከተሞች በተለይም በመዲናችን አዲስ አበባ ከሌላው ጊዜ በከፋ መልኩ የጥንቆላ፣ የሲሕር (ድግምት)፣ የአይነናስ በሽተኞች እየተበራከቱ ይገኛል ። የሩቃ (በአላህ ፍቃድ በቁርአን አካሚዎች) እንደሚናገሩት ከምንም ጊዜ የበለጠ በዚህ ጊዜ በተለይም ሙሰሊም የሆኑ ሴቶች ከፍተኛ የሆነ የሲሕር በሽታ ተጠቂዎች እየሆኑ መምጣታቸውን ይናገራሉ። መንስዔውንም ሲናገሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እዚ ግባ በማይባል ዱኒያ ቅናትና ሴራ ውስጥ ሙስሊሞች እየወደቁ ይህንኑ አላህ በወንድሞቻቸውና እሕቶቻቸው ላይ በዋለው ፀጋ ተመቃኝተው ወደ ሽረኪያት የሚሰሩባቸው ቦታዎች (በአብዛኛው “ወሊይ” ተብዬ ጠንቋዮች) ጋር በመሄድ ሲሕር እንደሚያሰሩና እስከ የካፊር መዘባበቻና መሳለቂያ ድረስ መድረሳችንን የሩቃ አካሚዎች ይናገራሉ ። አክለውም ሙስሊም ሴቶች በአሁኑ ሰዓት የምዕራባውያንን ባሕል በመከተል ከሂጃብ መራቃቸው ብሎም ከጊዜ ወደ ጊዜ አለባበሳቸው እየተራቆተ መምጣቱን በጂን ለመያዝ ሁነኛ ምክንያታቸው መሆኑን ይናገራሉ ። ቀድሞውኑ አብዛኛው ጊዜ ጂን የሚገባው ተዘጋጅቶ የሚጠብቀው ሰውነት ውስጥ አይደለምን? 
 ሱብሃነላህ ! ወዴት እየሄድን ይሁን ያ ጀምዐ? 
ሁላችንም ቤተሰቦቻችንንም ወደ ተውሒድና ወደ ሱና በማስተማር ከዚህ ከባድ በደል እራሳቸውን እንዲያቅቡ ልንመክር ልንገስፅ ይገባል።

④ ሰሞኑን በተለያዩ የማሕበራዊ ደረገፆች ላይ አንድ አዲስ ነገር መስተዋሉን ብዙዎቻችን እያየን እንገኛለን ። ይህም አላህ ሱብሃነሁ ወተዓላ መርጦና ወዶ የሰጠንን እስልምና ልክ ከአናት ላይ ቆብ የማውለቅ ያክል ወይንም ከሱም በቀለለ መልኩ የሚነጥቁንና በክህደት የሚወነጅሉን ‘ተክፊሮች’ በተመሳሳይም የሱና ዑለማዎችን ከሱና ልክ እንደ ወንጭፍ አስፈንጥሮ ለማስወጣት ቅንጣት የማይከብዳቸው ‘ሓዳዲዮች’ ከወትሮ በተለየ መልኩ ያላቸውን አቅም በመጠቀም በጥምረት ሕዝቤን ከኢስላምና ከሱና ለማስወጣት እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ ። «ግም ለግም አብረህ አዝግም»
 ስለነዚህ ሰርጎ-ገብ የጥመት ቡድኖች በዱዓቶች የተላለፉ ሙሃደራዎችን በማዳመጥ እራሳችንን ከነዚህ ሰዎች እንጠብቅ ዘንድ መልዕክቴን አስተላልፋለው ።  

⑤ ከላይ ከጠቀስናቸው መጤ ቡድኖች ትይዩ ደግሞ በ“አንድነት” ስም ሕዝቡን ለሽርክና ቢድዓ አሳልፈው በመስጠት የተካኑት ‘ኢኽዋኖች’ እና በዟሊም ኩፋር ሐይሎች እገዛ ሙስሊሙን በሽርክ ጨለማ ለመዋጥ ቀን ከሌት ከሚሯሯጡት ‘አሕባሾች’ ጋር  «የጠላቴ ጠላት ወዳጄ ነው» በሚለው መርሕ ተዛምደው በቅርቡ የእውቀት አድማሱን አስፍቶ  ተደራሽነቱን አጎልብቶ ሕዝብን በተውሒድና በሱና እውቀት ለማንቃት ከፍተኛ ስራ እየሰራ የሚገኘው የሱና ብርሐን ድረ–ገፅ ላይ የትብብር ጥቃታቸውን ከጀመሩ ሰንበትበት ብለዋል ። አላሁል ሙስተዓን
እየተጠቀሙት የሚገኘው የማደናበሪያ መርሆ «ሱና ብርሐን» አይወክለንም የሚል ሲሆን .... እስኪ ቢላሂ ዐለይኩም አንዴ ይሄን ዜና አቋርጬ እንደራሴ ላውራ ። ለነዚህ የሱና ጠላቶች የምላቸው ስላለኝ ነው ። እሺ እናነተዋ! ወላሂ ቢላሂ ተላሂ “የሱና ብርሓን ት/ቤት ይወክለናል” ብላቹ ብታውጁ እንኳን እንደማይወክላቹ ከወዲው ልንገራቹ!!! እራሳቹን አታስጠቁሩ!!! 
የሱና ብርሐን ድር ገፅ የቢድዓ አራማጆችን አ... ይ... ወ... ክ... ል... ም !!!
ጨርሻለው!!!

⑥ በመጨረሻም አሉ የተባሉ የማሕበራዊ ድረ–ገፅ አቀንቃኞች እና ‘የሙስሊሙ ልሳን’ ነን ብለው የሚሞግቱ ራዲዮዎች “ሕዝባዊ እምቢተኝነት” እናስተምራለን በማለት ተውሒድን ገሸሽ አድርገው ለሱና ጀርባ ሰጥተው ዛሬም በምስኪኑ ሕዝብ ላይ እየተጫወቱበት ይገኛል። ከዚህ ቀደም “ሕገ – መንግስት እናስተምራቿለን” በማለት ሕዘቡን በኩፍር ሲጠምቁ የነበሩት እኚው የሱና ጠላቶች ዛሬም ቅድሚያ ለተውሒድ ስጡ የሚለውን ነቢያዊ ትውፊትና ቡራኬ ጥለው የአይሁዳውያንን ባሕል ለማስተማር ደፋ ቀና በማለት ላይ ይገኛሉ ።

አሁንም እንላለን ....!
ጥሪያችንን ሊሰማን የሚችለው ሰምቶም መልስ ሊሰጠን የሚችለው የፈጠረን ጌታ ሰሚውና ተመልካቹ አንድ አላህ ነው ። ስለዚህም በአይሁድ ባሕል ተውራቹ እከሌ ዟሊም ባለስልጣን አልሰማንምና ሕዝቡን “እምቢኝ እናስተምረው” ከምትሉ ታላቁ የአላህ መልዕክተኛ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሄዱበትን በተውሒድ መንገድ ሄዳቹ የፈጣሪን ብቸኛ ተመላኪነት ለሕዝቡ በማስተማር ሽርክና ቢድዓን በማስጠንቀቅ የጌታችንን እርዳታ ተቀናጁ ።

ጌታችን ይናገራል ስሙት ..

وَلَيَنْصُرَنَّ اللَّهُ مَنْ يَنْصُرُهُ
ይሄ ነው ሚስጥሩ !!!

አላህ በተውሒድና በሱና ከሚተሳሰሩት ያድርገን 
አሚን አላሁመ አሚን‎'

አሚን አላሁመ አሚን