Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል 17

አለይኩም ወራህመቱላሒ ወበረካቱ
ኡሡሉ ሠላሣ ክፍል 17
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ
የሠላት.ና የዘካ መረጃ እንዲሁሞ የተውሒድ ትርጓሜ አላህ እንዲህ ይላል
«ከጥመት ወደ ሀቅ የዘነበሉ ሲሆኑ አላህን ጥርት አድርገው በቡቸኝነት ሊያመልኩ ሠላትንም ሊሠግዱ ዘካንም ሊያወጡ ቢሆን እንጂ አልታዘዙም» አልበይና
የፆም መረጃ አላህ እንዲህ ይላል
«እናንተ ምዕመናን ሆይ! ከናንተ በፊት በነበሩት ህዝቦች ላይ ፆም እንደተደነገገው
በናንተም ላይ ተደነገገ ትጠነቀቁት ዘንዳ ይከጀልላቹሀል»
የሀጅ መረጃ ፦ « ለአላህም በሠዎች ላይ ለቻለ ሠው ቤቱ. መጎብኘት አለው ለካደ ሠው አላህ ከአለማት የተብቃቃ ነው »
――――――――
አጭር ማብራሪያ
★ ኢቃሙ ሠላት
ኢቃሙ ሠላት ከሚለው ቃል የምንረዳው ሠላትን መስገድ ብቻ የሚል አጭር ቃል
አይደለም ሠፊ ቃል ነው በየትኛውም የቁርአን አንቀፅ ውስጥ "ሠሉ ሠላት " አላለም "አቂሙ ሠላት" ነው ያለው. ይህም ማለት
① የሠላትን አርካኖች በተገቢው መልኩ መፈፀም
② አላህ ፊት ቆሞ መተናነስ
③ የሚቀራውን ቁርአን ማስተንተን
④ ጀመአ ሠላት ላይ መገኘት … ሌላም ሠላትን ከሚያጎሉ ነገራቶች በአጠቃላይ የፀዳ ሠላት መስገድ ማለት ነው
ሌሎች ከሠላት ጋር ግንኙነት ያላቸው ነገራቶች ≫
ሠላት
ሠላት ከኢስላም መሠረቶች መካከል ሁለተኛው መሠረት ነው የሶላት ጊዜ ፣ ቦታ፣ ልብስና ዓይነቶች የሶላት ጊዜያት እያንዳንዱ ሶላት ጊዜው እንደደረስ ወይም በጊዜ ክልሉ ውስጥ መከናወን አለበት፡ ዕለታዊና ግዴታ (ፈርድ) የሆኑ አምስት ሰላቶች አሉ፡፡
★ የፈጅር ሶላት ፈጅር ወይም የሱብሂ ሶላት ጊዜ ጎህ ከቀደደ ጀምሮ ፀሐይ ወይም የፀሐይ ጮራ እስኪወጣ ድረስ ነው፡፡
★ የዙሁር (የቀትር) ሰላት የዙሁር ወይም የቀትር ሰላት ጊዜ ፀሐይ ከእኩለ ቀን በኋላ
ከሰማይ እንብርት (ምዕራብ) ጋደል ስትል ይጀምርና የማንኛወም ነገር ጥላ መጠን
የነገሩ መጠን ሲያክል ያበቃል፡፡ በእኩለ ቀን ፀሐይን ስንመለከት ልክ በጭንቅላታችን አቅጣጫ ሆና እናገኛታለን፡፡ በዚህን ጊዜ ጥላችን ከእግራችን ሥር ይሆናል፡፡ ነገር ግን
ፀሐይ ወደ ምዕራብ ትንሽ ጋደል ስትል ጥላችንም ከእግራችን ሥር ወደ ምሥራቅ
አቅጣጫ ወጣ ማለት ይጀምራል፡፡ የዙሁር ሶላት ጊዜም ልክ ከዚህ ጊዜ ይጀምራል፡፡
ከፀሐይቱ ማጋደል ጋር ከእግራችን ሥር ወደ ምሥራቅ ወጣ ያለው ጥላችን እያደገ
ከራሳችን ቁመት ጋር እኩል ሲሆን የዙሁር ሰላት ወቅት ያከትማል፡፡ ጃቢር ኢብን
ዐብዱላህ እንደተናገሩት፡ "መልአኩ ጅብሪል ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ዘንድ ከቀትር በኋላ መጠና «ዙሁር ስግድ» አላቸው፡፡ የአላህ መልዕክተኛም (ሶ.ዐ.ወ) ተነሱና ዙሁር ሰገዱ፡፡ ከዚያም መልአኩ ጅብሪል እንደገና ከቀትር በኋላ ቆየት ብሎ መጣና (ተነስ ዐሱር (ድህረ ቀትር) ሰላት ስገድ አላቸው፡፡ ከዚያም ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የማንኛውም ነገር ጥላ መጠን ከራሱ ቁመት ጋር እኩል በነበረበት ወቅት የዐሱርን ሶላት ሰገዱ፡፡ አሁንም በሚቀጥለው ቀን ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ተነሱና የማንኛውም ነገር የጥላው መጠን ከራሱ ቁመት ጋር እኩል በነበረት ጊዜ የዙሁር ሶላት ሰገዱ፡፡ ከዚያም ጅበሪል እንደገና በዐሱር ሰዓት (ከቀትር በኋላ) መጣና ተነስና የዐሱር ሶላት
ስገድ አላቸው፡፡ ከዚያም እሳቸው ተነሱና የማንኛውም ነገር የጥላ ርዝመት የራሱን
ርዝመት ሁለት እጥፍ ሆኖ በነበረት ወቅት የዐስር ሶላት ሰገዱ፡፡... ከዚያም ጅብሪል
ለሁለት ተከታታይ ቀናት እየመጣ ከነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር ከሰገደ በኋላ የሁለቱ ሶላቶች ጊዚያት በነዚህ ሁለት ወቅቶች መካከል መሆኑን ተናገረ፡፡ (አሕመድ፣ ነሳኢይ፣ቲርሚዚና ቡኻሪ ዘግበውታል)
ሰላት የሶላት ጊዜ ፣ ቦታ፣ ልብስና ዓይነቶች ብዙ የሶላት መጻህፍት የማንኛውም ነገር ጥላ ርዝመት የራሱን ቁመት ሁለት ጊዜ ሲያጥፍ የዙሁርሶላት ጊዜ የሚያከትምና የዐሱር ሶላት ጊዜ የሚጀምር መሆኑን ያትታሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አባባል በመጀመሪያው ቀን መልአኩ ጅብሪል የማንኛውም ነገር ጥላ ከራሱ ጋር እኩል
በነበረት ወቅት መጥቶ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶ.ዐ.ወ) የዐሱር ሶላት እንዲሰግዱ
የጠየቀበትና የሰገዱበት ወቅት መሆኑን የሚገልፀውን ከላይ የሰፈረወን ሐዲስ
ይፃረራል፡፡ ይህም የዙሁር ሶላት ጊዜ መብቂያ ማለት መሆኑ ነው፡፡ ጊዜው ሳይደርስ ሶላት መስገድ የማይቻል መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ ሳናስታውስ አናልፍም፡፡
★ የዐሱር (ድህረ ቀትር) ሶላት የዐሱር ሶላት ጊዜ የሚጀምረው የአንድ ነገር የፀሐይ ጥላ ርዝመት ከራሱ ቁመት ጋር እኩል በሚሆንበት ወቅት ሲሆን የሚያበቃውም ፀሐይ ልትጠልቅ ስትል ነው፡፡ የዐሱር ሶላት ፀሐይቱ ለመጥለቅ ስትቃረብ መስገድ የሚቻል ቢሆንም ቅሉ ይህችን ሶላት እስከዚያ ጊዜ ድረስ ማጓተት የመናፍቃን ባህሪ መሆኑን ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) ጠቁመዋል፡፡
★ የመግሪብ ሶላት የመግሪብ ሶላት ጊዜ ፀሐይቱ ልክ እንደጠለቀች ይጀምርና ቀዩ
ወጋገን ሲጠፍ ያከትማል፡፡
★ የዒሻ ሶላት የዒሻ ወይም የምሽት ሶላት ጊዜ ቀዩ ውጋገን እንደጠፋ ይጀምርና
ከእኩለ ሌሊት ትንሽ አስቀድሞ ያበቃል፡፡ ይህን ሶላት ጐህ እስከሚቀድ ድረስ መስገድ ቢቻልም ከእኩለ ሌሊት በፊት መስገዱ የተመረጠ ነው፡፡
✔ ሡና ሠላቶች
ከእያንዳንዱ ፈርድ ሠላት ቡሀላ እገዳ ከመጣባቸው ሠላቶች ውጪ ሡና ሠላት አለ እነሡም ጠበቅ ያለ ሡና በመባል የተነጠሉም አሉ እነሡም ከሡብሒ በፊት 2 በዙሁር በፊት 4 ከዙሁር ቡሀላ 2 ከመግሪብ ቡሀላ 2 ከኢሻ ቡሀላ 2 በጥቅሉ አስራ ሁለት ሡናዎች ይሆናሉ
✔ ሶላት የተከለከለባቸው ጊዜያት
ዑቅባህ ኢብን ዓምር እንዳመለከቱት፡- «ሶላት እንዳንሰግድ ወይም ሙታንን እንዳንቀብር በአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) የተከለከልንባቸው ሶስት ጊዜያት አሉ፡፡ እነርሱም፡- -
ፀሐይ መውጣት ከጀመረች ጀምሮ ሙሉ በሙሉ እስክትወጣ ድረስ፣ - ፀሐይ ጨረር
አናት ላይ ስትሆን ጀምሮ ወደ ምዕራብ እስክታገድል ድረስ፣ - ፀሀይ መጥለቅ ስትቃረብ ጀምሮ እስክትጠልቅ ድረስ ናቸው»ሙስሊም
ዘካ
ዘካት የተወሰኑ መመዘኛዎች ሲሟሉ ለተለያዩ የሕብረተሰቡ አባላት በንብረትነት ከያዙት (ንብረት) የሚከፈል ግዴታ ነው፡፡ ዘካት ከእስላም አበይት መስፈርቶችና ከታላላቅ መዋቅሮቹ አንዱ ሲሆን ቅዱስ ቁርኣን ውስጥ ብዙ ቦታ ላይ ከሶላት ተጣምሮ ተወስቷል፡፡ በግዴታነቱ ላይ ሙስሊሞች ሙሉ በሙሉ በፍጹምነት የተስማሙበት ሲሆን ግዴታነቱን እያወቀ ያስተባበለ ሰው ከኢስላም ጎራ የወጣ ከሐዲ (ካፊር) ነው፡፡ ዘካትን የከለከለ ወይም ያጥላላውና ያንቋሸሸው ሰው ለአላህ ቅጣትና ቁጣ ከተጋለጡት
በደለኞቹ ይቆጠራል፡፡ ለዚህ ማስረጃ የሚከተሉትን እንመልከት፡-
አላህ (ሱወ) እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፤ ዘካትንም ስጡ፤…›› ‹‹አላህን፣ ሃይማኖትና
ለርሱ ብቻ አጥሪዎች፣ ቀጥተኞች ሆነው ሊግገዙት፣ ሶላትንም አስተካክለው ሊሰግዱ፣ ዘካትንም ሊሰጡ እንጅ ያልታዘዙ ሲሆኑ (ተለያዩ)፡፡ ይህም የቀጥተኛይቱ (ሃይማኖት) ድንጋጌ ነው፡፡
>> ቡኻሪና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ መሰረት ዘካት ከአምስቱ የኢሰላም አበይት አዕማድ አንዱ መሆኑን የአላህ መልክተኛ (ሰዐወ) ማግለጻቸው ተረጋግጧል፡፡ ሙዓዝ ብኑ ጀበል የተባሉትን ባልደረባ ነቢዩ (ሰዐወ) መልክተኛቸው
በማድረግ ወደ የመን ስለመላካቸው ታሪክ ቡኻሪ ሲዘግቢ ከሀብታሞቻቸው ተወስዶ
ለድሆቻቸው የሚከፈል የተወሰነ ክፍያ አላህ የደነገገባቸው መሆኑን እንዲያስተምሩ ነብዩ ማዘዛቸውን አውስተዋል፡፡ የዘካትን አስፍላጊነት በማስተባበል ክፍያውን የከለከሉ
ሰዎች ከሐዲ (ካፊር) መሆናቸዉን ከሚከተለው ቁርኣናዊ አንቀጽ እንረዳለን፡-
‹‹ቢጸጸቱም፣ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ፣የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው፤‹‹ ከአንቀጹ እደምንረዳው ሶላት የማይሰግድና ዘካት የማይከፍል ሰው የእምነት ወንድማችን ሳይሆን ከከሃዲዎት የሚቆጠር ነው፡፡ ከዚሁ በመነሳት ሶላትንና ዘካን ለያይተው ዘካን የከለከሉ ሰዎችን አቡበከር ተዋግተዋቸዋል፡፡ በዚህ አቋማቸው ላይ ሁሉም ያላንዳች ልዩነት ተስማምተውበታል፡፡ ብዙ ጥበቦችን ያቀፈ፣ታላላቅ ግቦችን ያለመ ከፍተኛ የጋራ ጥቅሞችን ያካተተና ቁርኣንና ሐዲስ ይህ ግዴታ ተፈጻሚ እንዲሆን ያዘዙባቸውን አንቀጾች በማጥናትና በማስተዋል በግልጽ የሚታይ ጥበባዊ ድንጋኔ ነው፡፡
ከነዚህ አንቀጾች መካከል በ‹‹አል-ተውባህ›› ምዕራፍ ውስጥ የሰፈረውንና የዘካት ባለመብቶችን የሚዘረዝረው አንቀጽና ምጽዋት እንዲሰጥና ለበጎ አድራጎት ገንዘብ እንዲለገስ በአጠቃላይ መልኩ የሚያዙና የሚገፋፉ ነቢያዊ ሐዲሶች ይገኛሉ፡፡ ከነዚህ መካከል የሚተሉትን እናገኛለን፡፡
1.ከኃጢአትና ከክፉ ሥራ የአማኙን መንፈስ ማጥራትና በሕሊና ላይ የሚያስከትሉትነ ተጽእኖዎች ማስወገድ፤ ከንፉግነትና ከቆንቋናነት መጥፎ ባህሪና ከሚያስከትሉት አፍራሽ ውጤቶች አማኝን ማጽዳት፡፡ ሃያሉ አላህ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹ከገንዘቦቻቸው ስትሆን በርሷ የምታጠራቸውና የምታፋፋቸው
የሆነችነ ምጽዋት ያዝ፤…››
2. ድሃ ሙስሊምን በመርዳት ችግሮቹን በማቃለል ማገዝና አላህ ብቻ እንጂ የማንን እጅ ተዋራጅ ሆኖ እንዳያይና እንዳይለምን ማስቻሉ፣
3. ዕዳ ያለበት መስሊም በሰው እዳ ጫና እንዳይጨነቅ ዕዳውን በመሸፈን ከወደቀበት የሰዎች እዳ ነፃ ማውጣቱ፤
4. እምነት ሥር ያልሰደደባቸውንና የእስላም የእምነት ጽኑ እውነታ
ማሸጋገሩ፣
5. በአላህ መንገድ የሚታገሉ ተጋዳዮችን ለማደራጀት፣ የእስላምን ትምህርት ለማሰራጨት አስፈላጊውን መሰናዶ ለማከናወን፣ ክህደትና መጥፎ ነገሮችን
በማስወግድ በሰዎች መካከል ፍትህን አንግሶ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን በማጥፋት የአላህ ኃይማኖት እንዲሰፍን ለማድረግ ማስቻሉ፤
6. ከቤቱ ወጥቶ በእንግድነት ላይ እያለ ወደ ሀገሩ መመለሻ ገንዘብና አስፈላጊ ነገሮች ማገኘት ያልቻለ ሙስሊም መንገደኛ ወደ አገሩ ለማስመለስ ከዘካት የሚበቃውን ያህል የሚሰጠው መሆኑ፤
7. የአላህ ትዕዛዝ ማክበርና ለፍጡራኑ በተግባር በመፈጸም ቃሉን መስማት የሚያስገኘው በረከት፤ የዘካ
ከፋዩን ንብረት ታዳጊ ምርታማ ማድረጉና ከክፋትና ከጥፋት መከላከያና መጠበቂያው መሆኑ፤ እነዚህ ከመጠቁ የዘካት ጥበባትና ከላቁ ክቡር ዓላማዎች፡ በከፊል ለመጥቀስ ብቻ ሲሆን፣ የአላህን ሸሪዓ ምስጢሮችና ጥበቦቹን ሙሉ በሙሉ የሚያካትት ዕውቀት የአላህ ብቻ እንደመሆኑ ዘካት ሌሎች አያሌ ጥበቦችና ምስጢሮችን አቅፎአል፡፡ ዘካት የሚከፈላቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች በተመለከተው የቁርኣን አንቀጽ የተዘረዘሩ ናቸው፡-
‹‹ግዴታ ምጽዋቶች (የሚከፈሉት) ለድሆች፣ ለምስኪኖችም፣ በርሷም ላይ ለሚሰሩ ሠራተኞች፣ ልቦቻቸውም (በእስልምና) ለሚለማመዱት፣ ጫንቃዎችንም ነፃ በማውጣት፡
በባለ ዕዳዎችም፣ በአላህ መንገድም በሚሰሩ፣ ለመንገደኛም ብቻ ነው፣ ከአላህ
የተደነገገች ግዴታ ናት፣ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው፡፡
★ፆም
ፆም ማለት ጎህ ከቀደደበት ወቅት አንስቶ ፀሀይ. እስክትጠልቅ ድረስ ከሚያስፈጥሩ
ነገራቶች መቆጠብ ማለት ነው
ከሚያስፈጥሩ ነገራቶች መካከል
መብላት. ፣መጠጣት ፣የግብረ ስጋ ግንኙነት እና ሌሎችም
ፆም ከሰው ልጆች አንፃር
1. ፆም በእያንዳንዱ ሙስሊም፣ ለአካለ መጠን የደረሰ፣ ጤናማ አዕምሮ ያለው፣ መፆም የሚያስችለው ጤና ያለው እና መንገደኛ ባልሆነ ሰው ላይ ሁሉ ግዴታ ነው፡፡
2. ሙስሊም ያልሆነ ሰው ፆም ግዴታ አይሆንበትም፡፡ እንዲሁም ወደ ኢስላም ቢመጣ ከመስለሙ በፊት ያለፈውን ፆም የመክፈል (ቀዳእ የማውጣት) ግዴታ አይኖርበትም፡፡
3. ለአካለ መጠን ያልደረሰ ህፃን ፆም ግዴታ ባይሆንበትም ነገር ግን እንዲለምደው በማሰብ እንዲፆም ይታዘዛል፡፡
4. የአዕምሮ በሽተኛ ፆምም ይሁን ለፆም ማካካሻ የሚሆን ፆም ግዴታ አይሆንበትም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ነገሮችን መለየት የተሳነው ዘገምተኛ ሰው እንዲሁም የጃጀ ሽማግሌ ፆም ግዴታ አይሆንባቸውም፡፡
5. እንደ እርጅናና ለመዳን ተስፋ እንደሌለው በሽታ ባሉ ዘውታሪ ምክንያቶች የተነሳ መፆም የተሳነው ሰው ለእያንዳንዱ ቀን አንድ አንድ ምስኪን ያበላል፡፡
6. መዳኑን ተስፋ በሚያደርግ ጊዜያዊ በሽታ የተያዘ ሰው መፆም ከከበደው ከበሽታው ሲያገግም በመፆም ያካክሳል፡፡
7. በእርግዝናና በማጥባት ላይ ያሉ ሴቶች በዚህ በእርግዝናው ወይም በማጥባቱ
ምክንያት ፆም ከከበዳቸው አሊያም በልጆቻቸው ላይ ጉዳት እንዳይከሰት ከሰጉ ፆምን በመፍታት ስጋቱ በተወገደና በገራላቸው ወቅት ይፆማሉ፡፡
8. በወር አበባና በወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች የማይፆሙ ሲሆን ያለፋቸውን የፆም
ቀናት በሌላ ጊዜ በመፆም ያካክሳሉ፡፡
9. በእሳት ቃጠሎ ወይም በውሃ የመስጠም አደጋ ላይ የወደቁ ሰዎችን ለመታደግ የነፍስ አድን ስራ ላይ በመሰማራቱ ፆም ለመፍታት የተገደደ ሰው ፆሙን በሌላ ጊዜ በመፆም ያካክሳል፡፡
10. መንገደኛ (ሙሳፊር) ሰው ከፈለገ ይፆማል ከፈለገም ፆሙን በመፍታት በሌላ ጊዜ ያካክሳል፡፡ ይህም ማለት በዘውታሪነት ሳይሆን በድንገት እንደዑምራ ላሉ ተግባራት የሚጓዘውንም ይሁን በዘውታሪነት ጉዞ ላይ የሚሆኑትን (የአገር አቋራጭ) የሕዝብ ማመላሻ ሠራተኞችን ይመለከታል፡፡ እነዚህ ሰዎች በመኖሪያ አገራቸው እስካልሆኑ ድረስ
ከፈለጉ ፆምን ይፈታሉ ማለት ነው፡፡
★ ሀጅ
በእድሜ ድ ግዜ በይቱላህን መጎብኘት ይህም ለቻለ ሠው ብቻ ነው መቻል
የሚረጋገጠው በእነዚህ ሦስት ነገሮች ነው ① ጤነኛ መሆን
② የመኖገዱ ሠላም መሆን
③ ለቤተሠቡም ትቶ የሚሄደው እና ለራሡ በቂ የሆነ ገንዘብ ያለው
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል!!!
share ማድረጎን እንዳይረሡ!