Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ነፃ ካልወጡ ነፃ አውጪዎች ተጠንቀቂ

'ነፃ ካልወጡ ነፃ አውጪዎች ተጠንቀቂ
የፊታችን ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው አሉ፡፡ ወይ ፈረንጅ! አመቱን በሙሉ እኮ “የምንትስ ቀን” እያሉ ሊዘጉት ነው፡፡ ፈረንጅ ሲስል የሚስለው ሌላው ክፍል ነጩ ሰው “የግብረ ሰዶማውያን ቀን” ብሎ ቢጀምር ያለምንም ማመንታት ይከተላል፡፡ አሁንም ስላለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ብቻ ማርች ስምንትን ለሴቷ ሰጧት አሉ፡፡ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት!!” እለቱን ሳስታውስ አንድ ነጭ አስተማሪ ስለ ሴቶች “መብት” እንቅስቃሴ እያወራ የተናገረው ነገር ከአመታት በኋላ ትዝ አለኝ፡፡ የሴቶችን መብት ካፋጠኑ ነገሮች አንዱ ብስክሌት ነው ነበር ያለው፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ይደንቀኝ ነበርና ኢንተርኔት ገብቼ ሳስስ ለካንስ ሀሳቡ የሱ ብቻ አይደለም፡፡ ይሄ ነገር ሰዎቹ ምን ያክል ቂሎች እንደሆኑ እና ነፃነት ሲሉም ግርማ ሞገስ ያለውን አለባበሷን ማስጣል እና በቤት እመቤትነቷ እንድትሸፍት ማድረግ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ብቻ አላማቸው የሴቶችን መብት ማክበር እንዳልሆነ ከሙስሊም ሴቶች አንፃር ያላቸው አተያይና ፖሊሲ በተጨባጭ አይን ላየው ሁሉ እያሳየ ነው፡፡ እርቃንነትን እስከ ጥግ እየፈቀዱ ሙስሊሟን ግን አለባበሷን ምክኒያት በማድረግ፣ ከትምህርት ገበታ፣ ከስራ ቦታ ማፈናቀሉን ተያይዘውታል፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ስለ ሴቶች መብት የሚያቀነቅኑት፡፡ ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ አለባበሶች ላይ ትንፍሽ ሳይሉ ለሙስሊሟ ሲሆን ግን በየመንገዱ ይጎነትላሉ፡፡ አልፈውም ህገ-ደንብ ያወጣሉ፡፡ ፖሊሲ ያረቃሉ፡፡ ከዚያም አያፍሩም ስለ ሴቶች መብት ይሰኩራሉ፡፡ “የምትለብሺውን እኔ ካልመረጥኩልሽ” ከማለት በላይ ምን አፈና አለ?!!
እህቴ ሆይ!!! ተጠንቀቂ!! ብዙዎቹ የሴቶች “ነፃ አውጪዎች” የሰይጣን ተልእኮ አራማጅ የሆኑ የሀሰት ጥሩንባዎች ናቸው፡፡ እውነት ተቆርቁሮልሽ እንዳይመስልሽ፡፡ ቢሆንማ ለእርቃን እሩብ ጉዳይ መሆንን ፈቅዶ መልበስሽን ለምን ይቃወምሻል፡፡ እውነት ለመብትሽ ተሟጋች ከሆነ ስትራቆቺ ገልፍጦ ስትለብሺ ለምን ደሙ ይፈላል? ለምንስ በየመንገዱ ይጎነትላል? ለምንስ ከየተቋሙ ያባርራል? እመኚኝ፡፡ “ነፃ ውጪ” የሚለው በየጎዳናው በነፃነት በነፃ ወይም በርካሽ እንዲያገኚሽ ነው፡፡ አስተውይ! ልብስሽን ስለጣልሽ ነፃ አትወጭም፡፡ ነፃ መሆን ልብስ በመጣል ከሆነ ነፃ ሰዎች ማለት እብዶች ናቸው፡፡ የሚጮኸው ስለ ክቡር ማንነትሽ ሳይሆን ስለ እርቃን ገላሽ ነው፡፡ የነቁበት ነቅተውበት እየተመለሱ ነው፡፡ ይሄውና በምዕራቡ አለም ከሚሰልሙት ውስጥ 80% ሴቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች ለሀጫቸው የሚዝረበረብለትን የምዕራቡን “ነፃነት” ሸሽተው ወደ ኢስላም “ጭቆና” ይጎርፉ ይዘዋል፡፡ በጊዜ ንቂ፡፡ ብልጥ ማለት በሌሎች ላይ ከደረሰው ቀድሞ የሚማር ነው፡፡ ምሳሌሽን በትክክል ምረጪ፡፡ በአኢሻ ስብእና እያፈርሽ አሊሻን መሆን ካማረሽ ግን ግፊበት፡፡ ጀሀነምን የሚቋቋም ገላ ካለሽ መንገዱን ጨርቅ ያርግልሽ፡፡
ንቂ!!! ያለበለዚያ ይሄ በስጋዊ ፍላጎት የታወረው “ጠበቃሽ” የኮንዶም ማስታወቂያ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ!!! ያለበለዚያ ይሄ ካንገት በታች እንጂ ካንገት በላይ የሌለው ርካሽ በድን ከምንም በታች አርክሶሽ የሱ ርካሽ ሸቀጥ ማሻሻጫ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ! ሙስሊም ወንድምሽ ስለበደለሽ በኢስላም ላይ ብታምጪ ኢስላምን ቅንጣት ታክል አትጎጂውም፡፡ ብቻ በዱንያም ላታተርፊ ሁለቱንም አገር የከሰርሽ ከሁለት ያጣሽ ትሆኛለሽ፡፡ እራስሽን ሁኚ፡፡ የገደል ማሚቶ አትሁኚ፡፡ ሌሎች ስለሳሉ አትሳይ ስላነጠሱም አታነጥሺ፡፡ የተፈጠርሺው ለክቡር አላማ ነው፡፡ አላማ ቢስ አትሁኚ፡፡ ያለበለዚያ ኮምፓስ እንደሌለው መርከብ ዋለሽ ዋለሽ አስከፊ ፍፃሜ ላይ ትደርሻለሽ፡፡ 
ተጠንቀቂ!! ከሸሪአው አጥር ውጭ ያለ የመብት ጥያቄ አትጠይቂ፡፡ የፈጠረሽ ጌታ አንቺ እራስሽን ከምታውቂው በላይ ያውቃሻል፡፡ ላንቺም ከተኩላው “እንባ ጠባቂ” ቀርቶ ከራስሽም በላይ ያዝንልሻል፡፡ ደግሞም አትዘንጊ፡፡ ህይወት ማለት የአኺራ ህይወት ነው፡፡ አላህ አድሎሽ ሰማንያ ዘጠና አመት ብትኖሪ እንኳ በጊዜ ከሱናው ባቡር ውስጥ ካልተሳፈርሽ ሲመሽ ይቆጭሻል፡፡ ምን ብትኖሪ ህይወትሽ መጨረሻ አለው- ሞት፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ዘላለማዊ ህይወት፡፡ የዛሬው ቅቤ አንጓች “እንባ ጠባቂ” ተኩላ ግን የአኺራ ምንነቱም አይገባውም፡፡ ለዚያ ቀርቶ ለዱንያ እንኳ ጤነኛ ህልም የለውም፡፡ ለአኺራማ እንኳን ላንቺ ለራሱም አይሆንም፡፡ የአህያ ባል ከጂብ አያስጥልም፡፡ ለናቱ፣ ለሚስቱ፣ ለልጁ፣ ለእህቱ የማይሆን ሰካራም ነፃ ያወጣኛል ብለሽ ከገመትሽ የመጨረሻ ቂል ነሽ፡፡ እሱ እራሱ በስሜቱ የሚገዛ የስሜት ባሪያ ሆኖ በየትኛው ሞራሉ ነው አንቺን ነፃ የሚያወጣሽ? ቀድሞ ነገር ምን ሲደረግ ለሰካራም ጆሮሽን ሰጥተሽ፡፡ ቦታ ከሰጠሽውማ የአለም እዝነት የሆኑትን ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠላትሽ እንደሆኑ ቀስ እያለ እያዋዛ ያሰርፅብሻል፡፡ በጊዜ ካልነቃሽ መውጣት ከማትችይበት የስሜት አሮንቃ ውስጥ ይነክርሻል፡፡ በደጋሚ ምላሱ ጭንቅላትሽ ላይ ተብትቦብሽ የስሜት ባሪያ ሆነሽ ረክሰሽ፣ ከማንም በላይ ብቁና ንቁ የሆንሽ ይመስልሻል፡፡  ተቆርቋሪ መስሎ ስለቀረበ እንዳያታልልሽ፡፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ሀያእሽ ባለመሟጠጡ በግልፅ ባታወጪው እንኳ ውስጥሽ ለኢስላም ይደፈርሳል፡፡ ለነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ያለሽ ክብርም ምናልባት ካልጠፋ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ግን እስቲ እኔ ልጠይቅሽ፡፡ እውነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላንቺ ስለማይቆረቆሩ ነው ከመቶ ሺ በላይ  ሶሐቦቻቸው በተሰበሰቡበት ታላቅ ቀንና ታላቅ ቦታ ላይ “የሴቶችን ነገር አደራ” እያሉ አዋጅ ያሰሙት? እርግጥ ነው ብዙ በደል አለብሽ፡፡ ግን አስተውይ ከበደሎቹ ሁሉ የከፋው ዘላለማዊ ክብር የሚያጎናፅፍሽን ኢስላምሽን እንዳታውቂ መደረግሽ ነው፡፡ እናም እልሻለሁ፡ በኢስላም ከኢስላም መብትሽን ፈልጊ፡፡ ለወዳኛው ህይወትሽም ትጊ፡፡ የተኩላ ሰለባ እንዳትሆኚ ንቂ፡፡ የአላህ ሰላም ላንቺ ይሁን፡፡'
ነፃ ካልወጡ ነፃ አውጪዎች ተጠንቀቂ
የፊታችን ማርች 8 አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ነው አሉ፡፡ ወይ ፈረንጅ! አመቱን በሙሉ እኮ “የምንትስ ቀን” እያሉ ሊዘጉት ነው፡፡ ፈረንጅ ሲስል የሚስለው ሌላው ክፍል ነጩ ሰው “የግብረ ሰዶማውያን ቀን” ብሎ ቢጀምር ያለምንም ማመንታት ይከተላል፡፡ አሁንም ስላለመኖሩ እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ብቻ ማርች ስምንትን ለሴቷ ሰጧት አሉ፡፡ “ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት!!” እለቱን ሳስታውስ አንድ ነጭ አስተማሪ ስለ ሴቶች “መብት” እንቅስቃሴ እያወራ የተናገረው ነገር ከአመታት በኋላ ትዝ አለኝ፡፡ የሴቶችን መብት ካፋጠኑ ነገሮች አንዱ ብስክሌት ነው ነበር ያለው፡፡ ባስታወስኩ ቁጥር ይደንቀኝ ነበርና ኢንተርኔት ገብቼ ሳስስ ለካንስ ሀሳቡ የሱ ብቻ አይደለም፡፡ ይሄ ነገር ሰዎቹ ምን ያክል ቂሎች እንደሆኑ እና ነፃነት ሲሉም ግርማ ሞገስ ያለውን አለባበሷን ማስጣል እና በቤት እመቤትነቷ እንድትሸፍት ማድረግ እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ብቻ አላማቸው የሴቶችን መብት ማክበር እንዳልሆነ ከሙስሊም ሴቶች አንፃር ያላቸው አተያይና ፖሊሲ በተጨባጭ አይን ላየው ሁሉ እያሳየ ነው፡፡ እርቃንነትን እስከ ጥግ እየፈቀዱ ሙስሊሟን ግን አለባበሷን ምክኒያት በማድረግ፣ ከትምህርት ገበታ፣ ከስራ ቦታ ማፈናቀሉን ተያይዘውታል፡፡ እነዚህ ናቸው እንግዲህ ስለ ሴቶች መብት የሚያቀነቅኑት፡፡ ከባህልም ከሞራልም ያፈነገጡ አለባበሶች ላይ ትንፍሽ ሳይሉ ለሙስሊሟ ሲሆን ግን በየመንገዱ ይጎነትላሉ፡፡ አልፈውም ህገ-ደንብ ያወጣሉ፡፡ ፖሊሲ ያረቃሉ፡፡ ከዚያም አያፍሩም ስለ ሴቶች መብት ይሰኩራሉ፡፡ “የምትለብሺውን እኔ ካልመረጥኩልሽ” ከማለት በላይ ምን አፈና አለ?!!
እህቴ ሆይ!!! ተጠንቀቂ!! ብዙዎቹ የሴቶች “ነፃ አውጪዎች” የሰይጣን ተልእኮ አራማጅ የሆኑ የሀሰት ጥሩንባዎች ናቸው፡፡ እውነት ተቆርቁሮልሽ እንዳይመስልሽ፡፡ ቢሆንማ ለእርቃን እሩብ ጉዳይ መሆንን ፈቅዶ መልበስሽን ለምን ይቃወምሻል፡፡ እውነት ለመብትሽ ተሟጋች ከሆነ ስትራቆቺ ገልፍጦ ስትለብሺ ለምን ደሙ ይፈላል? ለምንስ በየመንገዱ ይጎነትላል? ለምንስ ከየተቋሙ ያባርራል? እመኚኝ፡፡ “ነፃ ውጪ” የሚለው በየጎዳናው በነፃነት በነፃ ወይም በርካሽ እንዲያገኚሽ ነው፡፡ አስተውይ! ልብስሽን ስለጣልሽ ነፃ አትወጭም፡፡ ነፃ መሆን ልብስ በመጣል ከሆነ ነፃ ሰዎች ማለት እብዶች ናቸው፡፡ የሚጮኸው ስለ ክቡር ማንነትሽ ሳይሆን ስለ እርቃን ገላሽ ነው፡፡ የነቁበት ነቅተውበት እየተመለሱ ነው፡፡ ይሄውና በምዕራቡ አለም ከሚሰልሙት ውስጥ 80% ሴቶች ናቸው፡፡ ብዙዎች ለሀጫቸው የሚዝረበረብለትን የምዕራቡን “ነፃነት” ሸሽተው ወደ ኢስላም “ጭቆና” ይጎርፉ ይዘዋል፡፡ በጊዜ ንቂ፡፡ ብልጥ ማለት በሌሎች ላይ ከደረሰው ቀድሞ የሚማር ነው፡፡ ምሳሌሽን በትክክል ምረጪ፡፡ በአኢሻ ስብእና እያፈርሽ አሊሻን መሆን ካማረሽ ግን ግፊበት፡፡ ጀሀነምን የሚቋቋም ገላ ካለሽ መንገዱን ጨርቅ ያርግልሽ፡፡
ንቂ!!! ያለበለዚያ ይሄ በስጋዊ ፍላጎት የታወረው “ጠበቃሽ” የኮንዶም ማስታወቂያ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ!!! ያለበለዚያ ይሄ ካንገት በታች እንጂ ካንገት በላይ የሌለው ርካሽ በድን ከምንም በታች አርክሶሽ የሱ ርካሽ ሸቀጥ ማሻሻጫ ነው የሚያደርግሽ፡፡ ንቂ! ሙስሊም ወንድምሽ ስለበደለሽ በኢስላም ላይ ብታምጪ ኢስላምን ቅንጣት ታክል አትጎጂውም፡፡ ብቻ በዱንያም ላታተርፊ ሁለቱንም አገር የከሰርሽ ከሁለት ያጣሽ ትሆኛለሽ፡፡ እራስሽን ሁኚ፡፡ የገደል ማሚቶ አትሁኚ፡፡ ሌሎች ስለሳሉ አትሳይ ስላነጠሱም አታነጥሺ፡፡ የተፈጠርሺው ለክቡር አላማ ነው፡፡ አላማ ቢስ አትሁኚ፡፡ ያለበለዚያ ኮምፓስ እንደሌለው መርከብ ዋለሽ ዋለሽ አስከፊ ፍፃሜ ላይ ትደርሻለሽ፡፡
ተጠንቀቂ!! ከሸሪአው አጥር ውጭ ያለ የመብት ጥያቄ አትጠይቂ፡፡ የፈጠረሽ ጌታ አንቺ እራስሽን ከምታውቂው በላይ ያውቃሻል፡፡ ላንቺም ከተኩላው “እንባ ጠባቂ” ቀርቶ ከራስሽም በላይ ያዝንልሻል፡፡ ደግሞም አትዘንጊ፡፡ ህይወት ማለት የአኺራ ህይወት ነው፡፡ አላህ አድሎሽ ሰማንያ ዘጠና አመት ብትኖሪ እንኳ በጊዜ ከሱናው ባቡር ውስጥ ካልተሳፈርሽ ሲመሽ ይቆጭሻል፡፡ ምን ብትኖሪ ህይወትሽ መጨረሻ አለው- ሞት፡፡ ከዚያ በኋላ ደግሞ ዘላለማዊ ህይወት፡፡ የዛሬው ቅቤ አንጓች “እንባ ጠባቂ” ተኩላ ግን የአኺራ ምንነቱም አይገባውም፡፡ ለዚያ ቀርቶ ለዱንያ እንኳ ጤነኛ ህልም የለውም፡፡ ለአኺራማ እንኳን ላንቺ ለራሱም አይሆንም፡፡ የአህያ ባል ከጂብ አያስጥልም፡፡ ለናቱ፣ ለሚስቱ፣ ለልጁ፣ ለእህቱ የማይሆን ሰካራም ነፃ ያወጣኛል ብለሽ ከገመትሽ የመጨረሻ ቂል ነሽ፡፡ እሱ እራሱ በስሜቱ የሚገዛ የስሜት ባሪያ ሆኖ በየትኛው ሞራሉ ነው አንቺን ነፃ የሚያወጣሽ? ቀድሞ ነገር ምን ሲደረግ ለሰካራም ጆሮሽን ሰጥተሽ፡፡ ቦታ ከሰጠሽውማ የአለም እዝነት የሆኑትን ነብይ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጠላትሽ እንደሆኑ ቀስ እያለ እያዋዛ ያሰርፅብሻል፡፡ በጊዜ ካልነቃሽ መውጣት ከማትችይበት የስሜት አሮንቃ ውስጥ ይነክርሻል፡፡ በደጋሚ ምላሱ ጭንቅላትሽ ላይ ተብትቦብሽ የስሜት ባሪያ ሆነሽ ረክሰሽ፣ ከማንም በላይ ብቁና ንቁ የሆንሽ ይመስልሻል፡፡ ተቆርቋሪ መስሎ ስለቀረበ እንዳያታልልሽ፡፡ ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው፡፡ ከዚያ በኋላ ሀያእሽ ባለመሟጠጡ በግልፅ ባታወጪው እንኳ ውስጥሽ ለኢስላም ይደፈርሳል፡፡ ለነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ያለሽ ክብርም ምናልባት ካልጠፋ በእጅጉ ይቀንሳል፡፡ ግን እስቲ እኔ ልጠይቅሽ፡፡ እውነት ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ላንቺ ስለማይቆረቆሩ ነው ከመቶ ሺ በላይ ሶሐቦቻቸው በተሰበሰቡበት ታላቅ ቀንና ታላቅ ቦታ ላይ “የሴቶችን ነገር አደራ” እያሉ አዋጅ ያሰሙት? እርግጥ ነው ብዙ በደል አለብሽ፡፡ ግን አስተውይ ከበደሎቹ ሁሉ የከፋው ዘላለማዊ ክብር የሚያጎናፅፍሽን ኢስላምሽን እንዳታውቂ መደረግሽ ነው፡፡ እናም እልሻለሁ፡ በኢስላም ከኢስላም መብትሽን ፈልጊ፡፡ ለወዳኛው ህይወትሽም ትጊ፡፡ የተኩላ ሰለባ እንዳትሆኚ ንቂ፡፡ የአላህ ሰላም ላንቺ ይሁን፡፡