Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

‹‹ያላዋቂ ሳሚ…›› ሱብሃነላህ እዚሁ ፌስቡክ ላይ ሃድራ ስለሚሉት በኢስላም ....

‹‹ያላዋቂ ሳሚ…››
ሱብሃነላህ እዚሁ ፌስቡክ ላይ ሃድራ ስለሚሉት በኢስላም እና በሰለዋት ስም የሚደረግ ጭፈራ ማስረጃ ቢጤ ይሆንልና ብለው የሚከተለውን ገጠሙ አላህ እነሱንም እኛንም ያቅናን
‹‹እንኳን ለነብዩ
ለአለሙ መሪ
ለአንድ ብር ብሎ
ይዘላል አዝማሪ››
ጥያቄዎች
1) አላህ ለነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጨፍሩለት፤ ዝለሉለት ብሏልን???
2) ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዝለሉልኝ፤ ጨፍሩልኝ ብለዋልን???
3) በነፍሳቸውም፤ በገንዘባቸውም ፊዳ የሆኑላቸው ሰሃባዎች በዝላይ ነበር ለሳቸው ያላቸውን ፍቅር ይገልፁ የነበረው???
በሸሪዓችን የታዘዝነው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይ ወሰለም) ላይ ሰለዋት እና ሰላም እንድናወርድ ነው፡፡ ሰለዋት ስናወርድ ደግሞ ሰለዋት ኢባዳ እንደመሆኑ እና አላህ የሚለመንበት እንደመሆኑ ሳንጮህ፤ አስተንትነን እና ተናንሰን ነው ሰለዋት የምናወርደው፡፡ ከነብዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ስር የነበሩት ሰሃባዎች ያልሰሩትን በመስራት ወደ አላህ ለመቃረብ መሞከር ከባድ አደጋ ነው፡፡
ሱናን ተከተሉ፤ መጤ ነገሮችን ራቁ ብለውን ነበር ምርጦቹ ሰለፎቻችን፡፡
ዋና ልብ ሊባል የሚገባው ሰዎች ከሱና ሲርቁ ምን ያህል የሸይጧን መጫወቻ እንደሚሆኑ ለማየት የፈለገ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ላይ የሚወርድ ሰለዋት ለብር (ለገንዘብ) ብሎ ከሚደለቅ እና ከሚዘል አዝማሪ ጋር ለማወዳደር መሞከር???
ሰይፍን ‹‹ይህ ሰይፍ እኮ እንጨት ይቆርጣል›› ቢባል፤ የሰይፉን ክብር ወይንም ደረጃ ይገልፃል ወይንስ ክብሩን ያጎድፋል???
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን፡፡ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሁላችን ጥርት ወዳለው የነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና እንመለስ ለሁሉም ነገር መፍትሄ አለው፡፡