Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ውድ ... ነጫጭቢስቶች ፣ አርቴፊሻሊስቶች ፣ ለውጥ-ናፋቂዎች

'ውድ ...
ነጫጭቢስቶች ፣ አርቴፊሻሊስቶች ፣ ለውጥ-ናፋቂዎች

- ደብዳቤው የሚመለከታቹ ተደብዳቢዎች
እንግዲህ ዛሬ ይህን ደብዳቤ የፃፈው ፀሃፊ ጠንከር ብሏልና ቂም አትያዙበት !!

« ነጫጭቢስቶች »
አዎን ሴቶች ናቸው ። የተፈጠሩበትን ከለር ስለማይወዱት ወደ ነጫጭባነት እራሳቸውን ይቀይራሉ ። ይህን የሚፈፅሙት በ “ቁንጅና” ስም ነው ። ምክንያታቱም በቴሌቪዥን የሚያዩዋቸው የምዕራባውያን ፣ የአረባውያን ፣ ቱርካውያን አርቲስቶች አብረቅራቂ በሜካፕ የተደፈደፈ ፊት ስለሚያስቀናቸው ። አንዳንዴ አገራችን ላይ ምን የሚሉት ተራራ ላይ የምትገኘው ቂጧ የተመለጠውን ጭላዳ ዝንጀሮ መስለው ያርፉታል ።

አላህ በፈጠራቹ አቋምና መልክ ትሳቀቃላቹን ? ፊታቹ ነጫጭባ ነው እግራቹ ጥቁር ነው ። ቆይ እኔ የምለው እስስቶች ናቹን ? ፊታቸውን በሜካፕ ነጫጭባነት አስለምደውት ከቆይታ በህዋላ እንደ እፍታ እንጀራ የተነፋፋባቸውና እንደ ኮብል ስቶን የተነቆረቆረው አሸዋ ግርፍ ፊት በሽተኞች አትማሩምን ? ፊታቹ ላይ የምትደፈድፉት ሜካፕ በጥፊ ነካ ብትደረጉ “ቡን!” ብሎ አካባቢ አይበክልም ?
ቆይ ግን ምንድን ነው ፋይዳው ?
እናንት ማለት እኮ ቀብራቹ ውስጥ የናንተን ሰውነት ለመመገብ በናፍቆት የሚጠብቁት ትላትሎች ጣፋጭ ምግብ ናችሁ ። ለዚህ ነው የምትዘጋጁት? ኻላስ!

« አርቴፊሻሊስቶች »
እነሱ ማለት በአርቴፊሻል የሚብቃቁ ፌክ ፍጡሮች ናቸው ። የተፈጥሮን አመጣጥ አይወዱትም ። በቃ ይነቀሳሉ.. ይበሳሳሉ.. ማንምን ። ነገረ ስራቸው ሁሉ አርቴፊሻል ነው
አርቴፊሻል ጥፍር
አርቴፊሻል ፀጉር
አርቴፊሻል አይን (አይናቸው ላይ የውሸት አይን ከለር ይለጥፋሉ)
አርቴፊሻል ጡት
አርቴፊሻል ፊት (አይናቸውን በእስራስ ይስሉታል ፣ ከንፈራቸውን በቅባት ይደፈድፉታል ወዘተ )
በቃ ሁለመናቸው አርቴፊሻል ነው ። ዛሬ ጥቁር ናቸው ነገ ቀይ ናቸው ። ዛሬ አፍሪካዊ ይመስላሉ ነገ ደግሞ ጃፓናዊ መስለው እርፍ ። ምናቸውም ኢስላማዊ ምልክት የለውም ። ቀጣይ የሚያስቡት ደግሞ ስማቸውን መቀየር ነው ። «መርየም» ወደምን ? «ሜሪ»

« ለውጥ-ናፋቂዎች »
ሃሎሎ...! የማወራው ስለፖለቲክ አይደለም ። የሰውን አይን ፍለጋ ሰውነታቸውን ለዋጮች እንጂ ። አልሰማውም እንዳትለኝ ። ዘንድሮ በሽ ናቸው ። ምናልባት ሚስጥርነት ተይዛ ነው ።
ጡታቸውን ያስተልቃሉ ( “እንዴት?” አትበለኝ ሂድና ዶክተሩን ጠይቀው!)
ዳሌያቸውን ያስተልቃሉ (አሁንም.. እንዴት አትበለኝ!!)
ቦርጫቸውን ያስቀንሳሉ
ምግብ አይበሉም በሁለት ወሩ ንፋስ ሲመጣ ስልክ እንጨት ይይዛሉ
ፀጉራቸውን ያስከረክማሉ ፣ ያስረዝማሉ ምናምን

ዛሬ ወፍራም ናቸው ። ነገ ቀጫጫ ። ዛሬ ረዥም ናቸው ነገ አጭር ናቸው ። ዛሬ ዛሬ አንዳንዶች አፍንጫቸውን ነጥብ ለማስመሰል ሚሊየን ብር እንደሚከፍሉ አልሰማህም ?
ስፌት ቤት ተወስዶ የሚጠበበው ልብስ ብቻ ይመስለኝ ነበር ። ዛሬ ግን ቆዳም እንደሚጠብ እየሰማን ነው ። የማይሰማ ጉድ የለምኮ እናንተዬ !!
ዘፋኞችን አላየህም በልብስ ውስጥ ያሉ አሻንጉሊቶች ። ዛሬ እህትህ እነሱን መሆን ተመኝታልሃለች። ካላመንክ ጠይቃት ። (አላህ ያዘነላት ስትቀር)
ቆይ ከሷ ጋር እናውራ እስኪ...
ቆይማ እህትዋ በሰላም ነው እንደዚህ የህፃን ልጅ መቻወቻ አሻንጉሊት የመሰልሺው? አላህ ቀጥ ያለ እግር ሰጥቶሽ አንቺ ግን አጣመሽው «ካት-ዎክ» (CAT WALK) እርምጃን መረጥሽ ። «ካት-ዎክ» ለማያውቅ «ካት-ዎክ» ማለት ቀጥተኛ ትርጉሙ የድመት ዕርምጃ ማለት ነው ። ዛሬ ሴቶቻችን እንደ ድመት መራመድ ጀምረዋል ። ያልሰማህ ስማ! ። አላህ የሰውን ልጅ ክብር ያለው አድርጎ ፈጥሮት ነበር ። ዛሬ ግን ድመትን መሆን ተመኝቷል ።
ወንዱ እንዲያይሽ ተመኝተሽ እንደዛ ስትሰባበሪ ወንዱ ግን ዞርም ብሎ አላየሽ ። ምስኪን
ያንን ታኮ መሰላል ጫማ ተጫምተሽ ለመራመድ ስትሳቀቂ ንፋስ የሚያወዛውዝሽ ኮባ እንጂ የምትራመጂ አትመስዪም ። አረረ.. ተመለሽ ሆሆ!

እንግዲህ..
እንዲህ ነው ፋሽን ባሪያው ያደረገሽ ። የወንድን አይን ፍለጋ ስትዳክሪ እስከዛሬ ለፋሽ

ለዚህም ነው«ኢስላማዊ ኑሮን» የማቀርብልሽ..... ተቀበዪኝ!
ነፃ ሴት ማለት ሙስሊሟ ሴት ናት ። ማንም እንዴት እንደምትለብስ አይነግራትም ። ማንም ምን መስራት እንዳለባትም አያስገድዳትም ። ምን መምሰል እንዳለባትም ማንም አይነግራትም ። አላህ ብቻ እንጂ!!

አንቺ አላህን በማመፅ ሕ ይወትሽን የምትመሪዋ እሕትዋ ...!
ካንቺ.. ከራስሽ... ከነፍስሽ... በላይ... የደከመ... ጠላት... የለሽም ።

አላህ በ'ንዲህ አይነቱ መሃይምነት ውስጥ ያሉ እሕቶቻችንን ይምራልን ።'
ውድ ...

አላህ በ'ንዲህ አይነቱ መሃይምነት ውስጥ ያሉ እሕቶቻችንን ይምራልን ።