Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ ሰዎች የሚሰጡ ብይኖችና እና ስያሜዎች ከሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ድንቅ አስተምህሮቶች

'‎ስለ ሰዎች የሚሰጡ ብይኖችና እና ስያሜዎች  

ከሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ድንቅ አስተምህሮቶች

ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በመልእክተኛው በባልደረቦቻቸውና በቤተሰባቸው ላይ ይሁን። 

የዲነል ኢስላምን ውበት ከሚያሳዩ ነገሮች መካከል በማንኛውም ጉዳይና ሁኔታ ላይ ፍትሀዊነትን ማዘዙ ነው።

አላህ እንዲህ ብሏል፤

 ﴿يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّـهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّـهَ ۚ إِنَّ اللَّـهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ ﴾
سورة المائدة ٨ 

«እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በፍትህ መስካሪዎች ሆናችሁ ለአላህ የምትቆሙ ሁኑ፤ የሰዎችም ጥላቻ ፍትህን እንዳትፈፅሙ እንዳይገፋፋችሁ፤ ፍትህን ተግብሩ፤ ይህ ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፤ አላህንም (ህግጋቱን በማክበር) ተጠንቀቁት፤ አላህ ስለምትሰሩት ሁሉ ወስጠ-አዋቂ ነውና!»      [አል-ማኢዳህ 8]

ይህ ፍትሀዊነት በሁሉም የሙስሊም የህይወት መስኮች ሊንፀባረቅ ይገባል። ከዚህም መካከል ሸሪዓዊ የሆነ ሰዎችን በማሞገስ ወይም በማውገዝ ብይን መስጠት የ (አል አስማእ ወል አህካም) ደንብና ስርአት ይገኝበታል። 

በሰዎች ላይ የሚሰጡ ትችቶችም ይሁኑ የሚገለፁባቸው ብይኖችና ስያሜዎች የተስተካከለ ሸሪአዊ መሰረት ሊኖራቸው ይገባል።
ሸሪዓዊ መሰረት የሌላቸውን ስያሜዎች መጠቀም ጥፋትንና ኢፍትሀዊነትን ያስከትላል።
ለዚህና ለሌሎችም ታያያዥ ጉዳዮችን በሱና የታወቁ ታላላቅ ኡለማዎች ፍንትው ያሉ 
ማብራሪያዎችን ሰጥተዋል። ከነዚህም መካከል ታላቁ አሊም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ይገኙበታል። ከዚህ በተች ከድንቅ አስተምህሮቶቻቸው ጥቂቶቹን እናያለን፤ 

1) ስያሜና ብይኖችን በተመለከተ፤ 

 قال شيخ الإسلام رحمه الله :' وَالْأَسْمَاءُ الَّتِي يَتَعَلَّقُ بِهَا الْمَدْحُ وَالذَّمُّ مِنْ الدِّينِ : لَا تَكُونُ إلَّا مِنْ الْأَسْمَاءِ الَّتِي أَنْزَلَ اللَّهُ بِهَا سُلْطَانَهُ وَدَلَّ عَلَيْهَا الْكِتَابُ وَالسُّنَّةُ أَوْ الْإِجْمَاعُ كَالْمُؤْمِنِ وَالْكَافِرِ وَالْعَالِمِ وَالْجَاهِلِ وَالْمُقْتَصِدِ وَالْمُلْحِدِ... فَأَمَّا الْأَسْمَاءُ الَّتِي لَمْ يَدُلُّ الشَّرْعُ عَلَى ذَمِّ أَهْلِهَا وَلَا مَدْحِهِمْ فَيُحْتَاجُ فِيهَا إلَى مَقَامَيْنِ: أَحَدُهُمَا: بَيَانُ الْمُرَادِ بِهَا. وَالثَّانِي: بَيَانُ أَنَّ أُولَئِكَ مَذْمُومُونَ فِي الشَّرِيعَةِ ' 'مجموع الفتاوى 4/146' .

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ብለዋል፤ « ከማውገዝና ከማወደስ ጋር የተያያዙ ስያሜዎች የዲን አካል ናቸው፤ አላህ ማስረጃ ያወረደበት እና ቁርአን፣ ሱና እና ኢጅማእ የጠቆሙት ሊሆን ይገባል። ሙእሚን፣ ካፊር፣ ዓሊም፣ ጃሂል፣ ሙቅተሲድ እና ሙልሂድ (Atheist)...፤  ሸሪዓው የአንድን ስያሜ ባለቤቶች ካላወደሰና ካላወገዘ ግን ሁለት እርምጃዎች ያስፈልጋሉ፤ የመጀመሪያው በስያሜው ምን እንደተፈለገ ግልፅ ማድረግ፤
ሁለተኛው የስያሜው ባለቤቶች በሸሪዓ የተወገዙ መሆናቸውን ግልፅ ማድረግ» 

2) አንድ ሰው ከሱና ዉጭ እንደሆነ ብይን የሚሰጥበት መቼ ነው? 

ኢብኑ ተይሚያህ በሁለት ወርቃማ ንግሮች ይህንን ጥያቄ ይመልሳሉ፤

قال شيخ الإسلام: (البدعة: التي يعد بها الرجل من أهل الأهواء ما اشتهر عند أهل العلم بالسنة مخالفتها للكتاب والسنة؛ كبدعة الخوارج، والروافض، والقدرية، والمرجئة). "الفتاوى" (35/414)

«አንድ ሰው ከስሜት ተከታዮች  የሚመደብበት የቢድዓ አይነት፤ በሱና የታወቁ የእውቀት ባለቤቶች ዘንድ ቁርአን እና ሱናን እንደሚፃረር የታወቀ የቢድዓ አይነት ነው።  ልክ እንደ ኽዋሪጅ፣ ረዋፊድ(ሺዓ)፣ ቀደሪያና ሙርጂአዎች አይነት ቢድዓ» መጅሙዕ አልፈታዋ ቅፅ 35 ገፅ 414 

وقال: (ومن خالف الكتاب المستبين، والسنة المستفيضة أو ما أجمع عليه سلف الأمة خلافًا لا يعذر فيه فهذا يعامل بما يعامل به أهل البدع). "الفتاوى" (24/172).

«ለሁሉም ግልፅ የሆነውን የቁርአን መልእክት፣ የተሰራጨን ሱና ወይም የኡማው አበው ትውልዶች (ሰለፎች) የተስማሙበትን "ኢጅማዕ" ምክኒያታዊ ባልሆነ (ኡዝር በማይሰጠው) መልኩ የተፃረረ፤ እንደ የቢድዓ ሰዎች ይቆጠራል!» 
  መጅሙእ አልፈታዋ ቅፅ 24 ገፅ 172

ይህ ሁለተኛው ንግግር እጅግ የተብራራ ገለፃ ሲሆን፤  አንድ ሰው እንደ ቢድዓ ሰዎች የሚቆጠረው፤  የሰራው ስህተት ቁርአንና ሱናን እንዲሁም ኢጅማእን የተፃረረ መሆኑ ግልፅ በሆነ መልኩ የተብራራና በስፋት የታወቀ ከሆነ፤ ይህ ስህተቱ እንዲታለፍ  የሚያደርግ ተቀባይነት ያለው ምክኒያት ከሌለው ነው።  

3) ማሳሰቢያ! 
ወደ ቢድዓ ጥሪ በሚያደርግ የቢድዓ አራማጅ እና ሸሪአን መሰረት አድርጎ መነሻ ባለው ኢጅቲሀድ ሳቢያ ቢድዓ ላይ በወደቀ ሰው መካከል ያለውን ልዩነት ልብ ልንል ይገባል።
 
قال شيخ الإسلام: (وكثير من مجتهدي السلف والخلف قد قالوا وفعلوا ما هو بدعة، ولم يعلموا أنه بدعة، إما لأحاديث ضعيفة ظنوها صحيحة، وإما لآياتٍ فهموا منها ما لم يرد منها، وإما لرأي رأوه وفي المسألة نصوص لم تبلغهم) انظر"الفتاوى" (19/191).

ይህንን  በማስመልከት ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላል፤ «ከሰለፎችም ይሁን ከኸለፎች ብዙ  ሙጅተሂዶች፤ ቢድዓ የሆነን ነገር ቢድአነቱን ሳያውቁ  ተናግረዋል ሰርተውታልም!  የዚህም ምክኒያት ሰሂህ የመሰሏቸው ደኢፍ ሀዲሶች፤ ወይም ከአንዳንድ የቁርአን አንቀፆች ያልተፈለገባቸውን መልእክት ተገንዝበው፤ ወይም ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ ሌሎች ሸሪዓዊ መረጃዎች ሳይደርሷቸው የያዙት አቋም ይሆናል» አልፈታዋ 19/191

ስለዚህ ጥፋቶች ሁሉ እኩል አይደሉም! የሚሰጧቸው ፍርድም እንደሁኔታው ይለያያል!! 

አላህ ፍትሀዊነትን ይለግሰን!‎'
ስለ ሰዎች የሚሰጡ ብይኖችና እና ስያሜዎች

አላህ ፍትሀዊነትን ይለግሰን!