Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጁሙአህ

'ጁሙአህ 

"እናንተ ያመናችሁ ሆይ በአርብ ቀን ወደ ስግደት  በተጠራ ግዜ አላህን ወደ ማውሣት ሂዱ  መሸጥንም ተው ይህ የምታውቁ ከሆነ ለናንተ በላጭ ነው "ቁርአን (ሡረቱል ፦ አል ጁሙአህ)
"በላጭ ቀናቹ የጁመዐ ቀን ነው "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም 
"ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዐ ቀን ነው "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም 

★ከላይ ያለፋት መለኮታዊ ንግግሮች በአጠቃላ ኢስላም ከሌሎች ቀናቶች ለይቶ  ለጁመአ ለት  የሠጠውን ደረጃ ያሣዩናል ይህን የተከበረ ቀን በምን መልኩ ማሣለፍ እንዳለብን ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ዘንድ የመጡት በማውሣት እንተዋወስ "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ እንደሠራው ነው" ይባል የለ 

☞ የጁመአ ለት ሡብሒ ሠላት ያለው ደረጃ "አላህ ዘንድ በላጩ ሠላት የጁመአ ቀን ሡብሒ በጀመአ መስገድ ነው "ሢልሢለቱ ሰሒህ 

☞ ጁመአ ለት ሡብሒ ሠላት ላይ ምን ምን ሡራ ይቀሩ ነበር 
"የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም  በጁመአ ሡብሒ ላይ (አሊፍ ላም ሚም ተንዚሉ: ሠጅዳ) እና (ሀል አታ አለል ኢንሣኒ) ይቀሩ ነበር "ቡሀርና ሙስሊም 

☞ በጁመአ ቀን ሠለዋት ማውረድ ያለው ጥቅም 
"የጁመአ ቀን እና ማታ በኔ ላይ ሠለዋትን አብዙ "በይሀቅይ 
."በላጭ ቀናቹ የጁመአ ቀን ነው የዛ ቀን:  አደም ተፈጠረ ፣ ሞተ ፣ ጡሩንባ ይነፋል ፣በህይወት ያለ ሁሉ ይሞታል በኔ ላይ ሠለዋትን አብዙ ሠለዋታቹ በኔ ላይ የምትቀረብ ናት "(አስሀቡ ሡነን) ነወውይ ሰሒህ ብለውታል 

☞ የጁመዓ ቀን ገላን መታጠብ "አንደኛቹ ወደ መስጂድ ሢመጣ ገላውን ይታጠብ "ቡሀርና ሙስሊም 

☞ የጁመአ ቀን ሽቶ መቀባት ፣ ጥሩውን መልበስ ፣ረጋ ብሎ (ሣይጣደፍ)  ወደ መስጂድ መሔድ በሁጥባ ወቅት ዝም ብሎ ማዳመጥ  ያለው ጥቅም "የጂመአ ቀን የታጠበ ፣ ሽቶ ካለውና ከተቀባ ፣ ጥሩ ልብስ የለበሰ ፣ ወደ መስጂድ ሢሔድ በተረጋጋ መንፈስ ከሔደ ፣ ከተመቸውና ከሠገደ ፣ አንድንም ሠው ካላስቸገረ ፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ  ከወጣበት እስኪሠገድ ድረስ ዝም ያለ  በሁለት ጁመአዎች መሀል ያለውን ወንጀል ይማርለታል "

 ☞ በግዜ መስጂድ መሔድ "የጁመአ ቀን መላይካዎች የመስጂድ በር ላይ ይቆማሉ ከዛ መጀመርያ ቀድሞ የሚገባውን ይፅፋሉ : መጀመርያ መስጊድ የሚገባው ግመል እንደሠጠ ከሱ ቀጥሎ ከብት ከሡ ቀጥሎ በግ ከዛም ዶሮ ከዛም እንቁላል ኢማሙ ሚንበር ላይ ሢወጣ መዝገቡን ዘግተው ሊያዳምጡ ይገባሉ  "ቡኸርና ሙስሊም 

★ የጁመአ ቀን የተከለከሉ ነገሮች

☞ ኢማሙ ሁጥባ ሢያደርግ ማንኛውም አይነት ንግግር ክልክል ነው በመልካም ማዘዝም ከመጥፎ መከልከልም  ቢሆን  "ለጎደኛህ የጁመአ ቀን ኢማሙ ሁጥባ እያደረገ ዝም በል ካልከው ውድቅ የሆነ ነገር ሠርተሀል "ቡሀርና ሙስሊም አህመድ "ውድቅን ነገር የሠራ ከጁመአው ምንም ነገር የለውም "የሚል ጨምረው ዘግበዋል 

☞ ዘግይቶ መስጂድ መምጣት እና ሠዎች አዛ ማድረግ "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሁጥባ እያደረጉ አንድ ሠው በሠዎች ጀርባ ላይ እየተረማመደ ሢመጣ "ተቀመጥ! ሠዎችን አስቸገርክ" አሉትኝ

☎ አደራህን ይች ወቅት እንዳታመልጥህ 

☞ አላህ የተጠየቀውን ነገር የሚመልስባት አንድ ወቅት አለች "በጁአ ለት አንድ ሠአት አለች እሧን ሠአት አንድ ሙስሊም የሆነ ባርያ አያገኛትም  እሡ የሚሠግድ ሢሆን አላህን አንዳች ነገር አይጠይቀውም የሠጠው ቢሆን እንጂ " ቡኻር እና ሙስሊም 

☞ ያቺ ሠአት መቼ ናት?? 
በዚህ ዙርያ ኡለሞች የተለያየ አመለካከት ሠንዝረዋል ከሙስሊም በተዘገበ ሀዲስ ኢማሙ ሁጥባ ከጨረሰበት ሠላት እስኪሰገድ ያለው ክፍተት ነው "አቡ ዳውድ እን ነስእይ በዚህ መልኩ ዘግበዋል "ከጁመአ የመጨረሻው ወቅት ላይ ፈልጓት "በሌላ ዘገባ "ከአስር ቡሀላ " የትኛውም ወቅት ሆነ የትኛው አላህ ሁላችንንም ያችን ወቅት እየዘክርን የምናገኛት ያድርገን'
ጁሙአህ
"እናንተ ያመናችሁ ሆይ በአርብ ቀን ወደ ስግደት በተጠራ ግዜ አላህን ወደ ማውሣት ሂዱ መሸጥንም ተው ይህ የምታውቁ ከሆነ ለናንተ በላጭ ነው "ቁርአን (ሡረቱል ፦ አል ጁሙአህ)
"በላጭ ቀናቹ የጁመዐ ቀን ነው "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም
"ፀሀይ ከወጣችባቸው ቀናቶች ሁሉ በላጩ ቀን የጁመዐ ቀን ነው "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም
★ከላይ ያለፋት መለኮታዊ ንግግሮች በአጠቃላ ኢስላም ከሌሎች ቀናቶች ለይቶ ለጁመአ ለት የሠጠውን ደረጃ ያሣዩናል ይህን የተከበረ ቀን በምን መልኩ ማሣለፍ እንዳለብን ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ዘንድ የመጡት በማውሣት እንተዋወስ "ወደ መልካም ነገር ያመላከተ እንደሠራው ነው" ይባል የለ
☞ የጁመአ ለት ሡብሒ ሠላት ያለው ደረጃ "አላህ ዘንድ በላጩ ሠላት የጁመአ ቀን ሡብሒ በጀመአ መስገድ ነው "ሢልሢለቱ ሰሒህ
☞ ጁመአ ለት ሡብሒ ሠላት ላይ ምን ምን ሡራ ይቀሩ ነበር
"የአላህ መልዕክተኛ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም በጁመአ ሡብሒ ላይ (አሊፍ ላም ሚም ተንዚሉ: ሠጅዳ) እና (ሀል አታ አለል ኢንሣኒ) ይቀሩ ነበር "ቡሀርና ሙስሊም
☞ በጁመአ ቀን ሠለዋት ማውረድ ያለው ጥቅም
"የጁመአ ቀን እና ማታ በኔ ላይ ሠለዋትን አብዙ "በይሀቅይ
."በላጭ ቀናቹ የጁመአ ቀን ነው የዛ ቀን: አደም ተፈጠረ ፣ ሞተ ፣ ጡሩንባ ይነፋል ፣በህይወት ያለ ሁሉ ይሞታል በኔ ላይ ሠለዋትን አብዙ ሠለዋታቹ በኔ ላይ የምትቀረብ ናት "(አስሀቡ ሡነን) ነወውይ ሰሒህ ብለውታል
☞ የጁመዓ ቀን ገላን መታጠብ "አንደኛቹ ወደ መስጂድ ሢመጣ ገላውን ይታጠብ "ቡሀርና ሙስሊም
☞ የጁመአ ቀን ሽቶ መቀባት ፣ ጥሩውን መልበስ ፣ረጋ ብሎ (ሣይጣደፍ) ወደ መስጂድ መሔድ በሁጥባ ወቅት ዝም ብሎ ማዳመጥ ያለው ጥቅም "የጂመአ ቀን የታጠበ ፣ ሽቶ ካለውና ከተቀባ ፣ ጥሩ ልብስ የለበሰ ፣ ወደ መስጂድ ሢሔድ በተረጋጋ መንፈስ ከሔደ ፣ ከተመቸውና ከሠገደ ፣ አንድንም ሠው ካላስቸገረ ፣ ኢማሙ ሚንበር ላይ ከወጣበት እስኪሠገድ ድረስ ዝም ያለ በሁለት ጁመአዎች መሀል ያለውን ወንጀል ይማርለታል "
☞ በግዜ መስጂድ መሔድ "የጁመአ ቀን መላይካዎች የመስጂድ በር ላይ ይቆማሉ ከዛ መጀመርያ ቀድሞ የሚገባውን ይፅፋሉ : መጀመርያ መስጊድ የሚገባው ግመል እንደሠጠ ከሱ ቀጥሎ ከብት ከሡ ቀጥሎ በግ ከዛም ዶሮ ከዛም እንቁላል ኢማሙ ሚንበር ላይ ሢወጣ መዝገቡን ዘግተው ሊያዳምጡ ይገባሉ "ቡኸርና ሙስሊም
★ የጁመአ ቀን የተከለከሉ ነገሮች
☞ ኢማሙ ሁጥባ ሢያደርግ ማንኛውም አይነት ንግግር ክልክል ነው በመልካም ማዘዝም ከመጥፎ መከልከልም ቢሆን "ለጎደኛህ የጁመአ ቀን ኢማሙ ሁጥባ እያደረገ ዝም በል ካልከው ውድቅ የሆነ ነገር ሠርተሀል "ቡሀርና ሙስሊም አህመድ "ውድቅን ነገር የሠራ ከጁመአው ምንም ነገር የለውም "የሚል ጨምረው ዘግበዋል
☞ ዘግይቶ መስጂድ መምጣት እና ሠዎች አዛ ማድረግ "ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሁጥባ እያደረጉ አንድ ሠው በሠዎች ጀርባ ላይ እየተረማመደ ሢመጣ "ተቀመጥ! ሠዎችን አስቸገርክ" አሉትኝ
አደራህን ይች ወቅት እንዳታመልጥህ
☞ አላህ የተጠየቀውን ነገር የሚመልስባት አንድ ወቅት አለች "በጁአ ለት አንድ ሠአት አለች እሧን ሠአት አንድ ሙስሊም የሆነ ባርያ አያገኛትም እሡ የሚሠግድ ሢሆን አላህን አንዳች ነገር አይጠይቀውም የሠጠው ቢሆን እንጂ " ቡኻር እና ሙስሊም
☞ ያቺ ሠአት መቼ ናት??
በዚህ ዙርያ ኡለሞች የተለያየ አመለካከት ሠንዝረዋል ከሙስሊም በተዘገበ ሀዲስ ኢማሙ ሁጥባ ከጨረሰበት ሠላት እስኪሰገድ ያለው ክፍተት ነው "አቡ ዳውድ እን ነስእይ በዚህ መልኩ ዘግበዋል "ከጁመአ የመጨረሻው ወቅት ላይ ፈልጓት "በሌላ ዘገባ "ከአስር ቡሀላ " የትኛውም ወቅት ሆነ የትኛው አላህ ሁላችንንም ያችን ወቅት እየዘክርን የምናገኛት ያድርገን

Post a Comment

0 Comments