Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የጀበና ጣጣ

'‎የጀበና ጣጣ
بسم الله الرحمن الرحيم
ቅድመ-ነገር
በማነሳቸው ጉዳዮች ውስጥ ብዙ የጋራ ነገሮች ቢኖሩም ከቦታ ቦታ እንደሚለያዩ እሙን ነው፡፡ በዚህም ምክኒያት ከተነሱት ጉዳዮች ከፊሎቹ አንዳንድ አካባቢዎች ላይኖሩ ይችላሉ፡፡ ሌሎች አካባቢዎች ደግሞ በከፋ መልኩ ብዙ ኮተቶችን ጨምረው አሉ፡፡ ስለዚህ ለነዚህ ነገሮች እንግዳ የሆነ ሰው እሱ ስላላወቀ ብቻ ወደ ማስተባበል እንዳይዳዳው ላስታውስ እወዳለሁ፡፡
. . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . . .. . 
ከጎረቤት የተጠሩ እንግዶች ቦታ ቦታቸውን ይይዛሉ፡፡ ስኒና ጀበና ከነረከቦቱ፣ ጋቻና እጣኑ፣ ቆሎ፣ የቡና ቁርስ እና መሰል ነገሮች አቅም እንደፈቀደ ከሞላ ጎደል የስርኣቱ ማድመቂያ ናቸው፡፡ ከቆሎው እየዘገኑ ወደ ውጭም ወደ ውስጥም የሚረጩበት ሁኔታ አለ፡፡ ወደ ውጭ ሲረጭ “ሸር ውጣ” ሲባል ወደ ውስጥ ሲበተን ደግሞ “ኸይር ግባ” ይባላል፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የምንመገበው ምግብ እንኳን ቢወድቅ ቢቻል አፅድተን እንድንበላው ያዛሉ እዚህ ግን እህል እንደ ዋዛ ይበተናል፡፡ አስቸጋሪ ህዝብ!! ሲያገኝ እህል ይበትናል፡፡ ሲያጣ ሙታን ይማፀናል፡፡
ባለ ቡናዋ ከተጠሩ ጎረቤቶች ፊት ለፊት ጀበናዋን ይዛ ትቀመጣለች፡፡ አንዳንዷ እስኪ “ያንን ጉፍታ አቀብይኝ” ብላ ለቡናው ስርኣት ብቻ ላመል ያክል አጠፍ አጠፍ አድርጋ አናቷ ላይ ጣል ታደርገዋለች፡፡ ከዚያም ከተቀመጠችበት በመነሳት ሁለት እጆቿን ከጀበናው አንገት ላይ አድርጋ “አወል ጀባ፣ ቀሃ ጀባ” ትላለች፡፡ ከታዳሚዎች ምርቃት የሚችለው ወይም በእድሜ አንጋፋ የሆነው ወይም የጠመጠመው ምርቃቱን ይጀምራል፡፡ “አማን ኢማን ጀባ! በረካ ጀባ፣ ሰፊ ሪዝቅ ጀባ፣ ወዘተ ጀባ” እያለ ያዥጎደጉደዋል፡፡ እሷስ “አወል ጀባ” ብትል ቡናውን በእጇ ይዛ ነው፡፡ እሱ ከየቱ ነው ይሄን ሁሉ ተአምር የሚጀባው? ወይ ጣጣ!!
ታዳሚዎቹም ስራ አይፈቱም፡፡ “ይሁን ይሁን” እያሉ እጃቸውን ያርገበግባሉ፡፡ መራቂው፡- ሁሉ በእጁ ሁሉ በደጁ ሆኖ አማን አይቀረው፣ ኢማን አይቀረው፣ ልጅ አይቀረው ሁሉን “ያስረክባታል፡፡” ዙሪያውን የተጣዱት “የፓርላማ” አባላትም “በቃ ይሁን ተስማምተናል” እያሉ እንዲሰጣት ያፀድቃሉ፡፡ ምርቃቱ ሲጠናቀቅ የመራቂውን እጅ ይዛ አገላብጣ ትስማለች፡፡ ይህ ሁሉ ሲሆን “ለምን?” ብሎ የሚጠይቅ የለም፡፡ ቤሳቤስቲን የሌለው አንድ ባተሌ ግን እንደ ዋዛ “ኢማን ጀባ” ይላል፡፡ አይደለም እሱ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንኳን ስንት መስዋእትነት ለከፈለላቸው አጎታቸው አቡ ጧሊብም ኢማን አልጀቡትም፡፡ እንዳውም “አንተ የወደድከውን አታቀናም” ብሎ ሀያሉ ጌታ አስረግጦ ነግሯቸዋል፡፡ አጅሬ ግን ሳይኖረው ያከፋፍላል፡፡ “ሰባት ወንድ ልጅ ጀባ” ይላል፡፡ ሱብሓነላህ!! ባህል ለካ እንዲህ እፍረት ያሳጣል?!! ልጅ የሚሰጠው ሁሉ በእጁ የሆነው ጌታ ብቻ ነው፡፡ 
]يَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ إِنَاثًا وَيَهَبُ لِمَنْ يَشَاءُ الذُّكُورَ[
“ለፈለገው ሴቶችን ይለግሳል፡፡ ለፈለገው ደግሞ ወንዶችን ይለግሳል፡፡” [አሽሹራ፡ 49] 
እንዲህ አይነት ድንበር ዘለል ምርቃት የሚመርቁ ሰዎች ያለ ጥርጥር እራሳቸውን ለአላህ ባላንጣ አድርገዋል፡፡ እራሳቸውንም ከአላህ ጋር ሰጪ ነሺ አድርገዋል፡፡ ይሄ እጅግ አደገኛ ጥፋት ነው፡፡
በጥቅሉ ከባህል ባህል፣ ከቤት ቤት ቢለያይም የቡና ስርኣት ብዙ ጊዜ በአደገኛ ጥፋቶች የታጨቀ ነው፡፡ ከአጅነቢ ጋር ተፋጦና ተቀላቅሎ መቀመጥ አለው፡፡ ዱንያ አኺራን በሚያጠፉ ሺርኮች የተጨማለቁ ምርቃቶች ያጅቡታል፡፡ ይስተዋል! ሺርክ ጭራሽ ምህረት የሌለው አደገኛ ወንጀል ነው!! ጌታችን አላህ እንዲህ ይላል፡-
]وَمَنْ يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَكَأَنَّمَا خَرَّ مِنَ السَّمَاءِ فَتَخْطَفُهُ الطَّيْرُ أَوْ تَهْوِي بِهِ الرِّيحُ فِي مَكَانٍ سَحِيقٍ[
“በአላህም የሚያጋራ ሰው ልክ ከሰማይ እንደወደቀ እና በራሪ እንደምትጠልፈው ወይም ነፋስ በሩቅ ስፍራ እንደምትጥለው ብጤ ነው፡፡” [አልሐጅ፡ 31]
“ይሁን” ባዮቹም ለጥፋቱ እውቅና የሚሰጡ የጥፋቱ ተጋሪዎች ናቸው፡፡ ለአጅነቢ እጁን ዘርግቶ የሚያስመው የጥፋት አውራም ወንጀሉን እየደራረበ ነው፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡- 
[ لأن يطعن في رأس رجل بمخيط من حديد خير له من أن يمس امرأة لا تحل له ]
“አንድ ሰው ያልተፈቀደችለትን ሴት ከሚጨብጥ በብረት መርፌ አናቱን ቢወጋ ይሻለዋል!!” [አስሶሒሐህ፡ 226]
ዛሬ መቀነስ ቢታይም ብዙዎቹ የቡና ስርኣቶች ቀናትን ለፍጡር ከፋፍሎ በመስጠት የሚከናወኑ ናቸው፡፡ ማክሰኞ ለኑራ ሑሴን፣ ረቡዕ ለጀይላኒ፣ ቅዳሜን ለኸዲር እያሉ የቡና ቁርስ ብለው ምግብ ያዘጋጃሉ፡፡ “ምነው?” ሲባሉ የሞቱ ወላጆቻቸውን በሶደቃ ያላሰቡትን “ሶደቃ ነው” እያሉ ራሳቸውን ሸውደው ሌሎችን ሊሸውዱ ይሞክራሉ፡፡
በተለይ ዛሬ ደግሞ የቡና ስርኣት በጫት የታጀበ ስለሆነ በምርቃና እየታገዙ አሰቃቂ ሺርኮችን የሚፈፅሙት ቀላል አይደሉም፡፡ የሚተርኳቸው የአውሊያእ ቂሳዎችም በውሸት የታጨቁ፣ ዘግናኝ በሆኑ ሺርኪያት የተጨማለቁ ናቸው፡፡ “እከሌ ወልይ እከሌ የሚባሉትን ወልይ በመዐና ገደሏቸው፣ በአንድ ሌሊት አርባ አባውራ ጨረሱ፣ የአንድ አካባቢ ነዋሪዎችን ድንጋይ አደረጓቸው፣…” አቤት የወልይ ነገር!!!! እውነት አድርገውት ከሆነ እነዚህ ነፍሰ-በላ ጭራቆች ናቸው፡፡
የቡና ስርኣት ከዚህ ሁሉ ኮተት ከተረፈም የሃሜት ጉባኤ የሚሆንበት አጋጣሚ ሰፊ ነው፡፡ የሆነ አካል “ሆሆይ! ምን ዙሪያውን ትዞራለህ ሐራም ነው በለንና እረፍ” የሚለኝ መሰለኝ፡፡ ኧረ እኔ አልወጣኝም!! እኔ እኮ ያወራሁት ቡናው ጋር ስለሚያያዙ ኮተቶች እንጂ ስለራሱ ስለቡናው አይደለም፡፡ ነው ወይስ በነዚህ ኮተቶች ካልታጀበ ቡናው ከጉረሮ አልወርድም ይላል? ባይሆን ለዚያ ጥቁር ሸክላ የሚሰጠው ክብር ነው የሚደንቀው፡፡ አንዳንዱማ ጭራሽ ከክፉ የመጠበቅ ሃይል እንዳለው የሚያምን አለ፡፡ ይሄ እምነት ደግሞ ዱበርቲዎች ላይ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡ አስታውሳለሁ ሃይ እስኩል በምማርበት ጊዜ ሁለት ጓደኞቼን አሳቻ ቦታ ላይ ሰካራሞች አግኝተዋቸው አንገላተዋቸው ለጥቂት ይተርፋሉ፡፡ አንድኛው ቁና ቁና እየተነፈሰ “ዛሬ የናቴ ጀበና ነው ያተረፈኝ” አለ፡፡ ደነገጥኩ፡፡ ግንዛቤው ብዙም እንዳልሆነ ባውቅም አንድ በስባሳ ሸክላ “ይጠብቀኛል” ብሎ እስከማመን ይወርዳል ብዬ ግን አልገምትም ነበር፡፡ ሀያሉ ጌታ እንዲህ ይላል፡- 
]أَمَّنْ يُجِيبُ الْمُضْطَرَّ إِذَا دَعَاهُ وَيَكْشِفُ السُّوءَ وَيَجْعَلُكُمْ خُلَفَاءَ الْأَرْضِ أَإِلَهٌ مَعَ اللَّهِ قَلِيلًا مَا تَذَكَّرُونَ[
(ወይስ ያ ችግረኛን በለመነው ጊዜ የሚቀበል፣ መከራንም የሚያስወግድ፣ በምድርም ላይ ምትኮች የሚያደርጋችሁ (ይበልጣል ወይስ የሚያጋሩት?) ከአላህ ጋር ሌላ አምላክ አለን? ጥቂትንም አትገሰፁም!!) [አንነምል፡ 62]
ይሄ ውሽልሽል እምነት ዛሬም ድረስ በደንብ አለ፡፡ ከብዙዎች ቤት የሚደመጥ አንድ መንዙማ ላይ እንዲህ የሚል ስንኝ ይሰማል፡
“ቅመን ተቃቅመን …. ታመጣው ክዳቱን
ስኒና ጀበና ይብላው ዳኝነቱን፡፡” 
አላሁልሙስተዓን!! እስኪ ስኒና ጀበና ምን የሚሉት ዳኝነት ነው ያላቸው? ህፃን ሲሰብራቸው የድረሱልን ጥሪ እንኳን ማሰማት የማይችሉ በድኖች?!! እንዲህ የሚያምኑ ሰዎች ያለ ጥርጥር እነዚህን ደካማ እቃዎች ጣኦት አድርገው እንደያዟቸው ነው የሚያሳየው፡፡ ይሄ ከንቱ የጃሂሊያህ ውርስ ነው፡፡ ሀያሉ ጌታ ለመልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ይላቸዋል፡-
]قُلْ أَفَرَأَيْتُمْ مَا تَدْعُونَ مِنْ دُونِ اللَّهِ إِنْ أَرَادَنِيَ اللَّهُ بِضُرٍّ هَلْ هُنَّ كَاشِفَاتُ ضُرِّهِ أَوْ أَرَادَنِي بِرَحْمَةٍ هَلْ هُنَّ مُمْسِكَاتُ رَحْمَتِهِ قُلْ حَسْبِيَ اللَّهُ عَلَيْهِ يَتَوَكَّلُ الْمُتَوَكِّلُونَ[
(ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውን አያችሁን? አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነሱ ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?!” በላቸው፡፡ “አላህ በቂዬ ነው፡፡ በርሱም ላይ ተመኪዎች ይመካሉ” በል፡፡) [አዝዙመር፡ 38]
وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم‎'

وصلى الله على نبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم