Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ፍጡራንን መማፀንና ዱዓን ለእነርሱ ማቅረብ

'‎ፍጡራንን መማፀንና ዱዓን ለእነርሱ ማቅረብ
አላህ እንጂ ሌላ ማንም በማይችለው ጉዳይ ላይ ከአላህ ሌላ የሆነን አካል መለመን፣ እርዳታን እና ጥበቃን መጠየቅ እንዲሁም ድረሱልን ማለት … እነዚህ የተለያዩ የዱዓእ ወይም የፀሎት ክፍሎች ናቸዉ፡ ኑዕማን ኢብኑ በሺር በአስተላለፉት ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ ዱዓእ ለአላህ ብቻ የሚገባ አምልኮ መሆኑን እንዲህ በማለት ይገልፁልናል፡- “ዱዓእ እርሱ እራሱ አምልኮ ነው፡፡” (ኢማሙ አህመድ፣ ቲርሚዚይ እና ሌሎችም ዘግበውታል)
ሽርክ ማለት ለአላህ ብቻ የሚገባን ዒባዳ (አምልኮ) ለሌላ አሳልፎ መስጠት ነው፡፡ ስለሆነም ከላይ የጠቀስናቸዉን የተለያዩ የዱዓእ ክፍሎች ለነብያት፣ ለመላኢኮች (መላእክት) ፣ ለጂኖች (ለአጋንንት)፣ ለሞቱም ሆነ በህይወት ሳሉ ደጋግ የአላህ ባሮች፣ ለአላህ ወዳጆች (ወልዮች) … ወዘተ ማዋል ከትልቁ ሽርክ ውስጥ የሚመደብ ተግባር ነው፡፡ ፍጡራንን “ያ ረሱለላህ፣ ያ ዐሊይ፣ ያ ሰይዳ ፋጡማ፣ ያ ሁሰይን፣ ያ አብዱልቃድር ጀይላኒ፣ ያ ሰይዳ ዘይነብ፣ ያ ነጃሺ፣ ያ ኑርሁሰይን፣ ያ አብሬት፣ ያ ቃጥባሪ፣ ያ አልከሰዬ፣ ያ ሐጂ አሊዬ … ወዘተ እያሉ አላህ እንጂ ሌላ ማንም ሊፈፅመው በደይችለው ጉዳይ ላይ ለምሳሌ፡- ልጅ የለኝምና ልጅ ስጡኝ ፣ ታምሜያለሁና ፈውሱኝ፣ ተርቤያለሁና ሲሳይን ለግሱኝ፣ ፣ ተጨንቂያሁና ከጭንቅ አውጡኝ፣ ፈርቼያለሁ እና ከአደጋ ጠብቁኝ፣ ከጀሀነም እሳት ጠብቁኝ፣ ለጀነት አብቁኝ፣ አማላጅ ጠበቃ ሁኑኝ… በማለት እነሱን መጠራትና መማፀን እና ድረሱልኝ ማለት በጥብቅ የተከለከለ ግልፅ የሽርክ ተግባር ነው፡፡
ይህ አይነቱ ጥሪ ሽርክ መሆኑን ከሚያመላክቱ እጅግ በጣም በርካታ የቁርአን እና የሐዲስ መረጃዎች መካከል ጥቂቶቹን ብቻ ለመጠቆም እምክራለሁ፡፡ አላህ እርሱ እንጅ ሌላ ማንም በማይችለው ጉዳይ ላይ ሌላን እርዳታ እንዳንጠይቅ ቃል ሲያስገባን እንዲህ ይላል፡- 
}إِيَّاكَ نَعْبُدُ وإِيَّاكَ نَسْتَعِينُ { الفاتحة: ٥
‹‹አንተን ብቻ እናመልካለን አንተንም ብቻ እርዳታ እንለምናለን፡፡›› አል ፋቲሀ 5
እንዲሁም አላህ የሰው ልጆች ከደጋሚ፣ ከመተተኛ እና ከጠንቋይ፣ ከአጋንንት እና ከሌሎች እርኩሳን አካላት ክፋት እና ሴራ በእርሱ ብቻ አንዲጠበቁ ያዛል፡፡ አላህ መልዕክተኛውን እንዲህ እንዲሉ አዟቸዋል፡፡
قُلْ أَعُوذُ بِرَبِّ الْفَلَقِ (1) مِنْ شَرِّ مَا خَلَقَ (2) وَمِنْ شَرِّ غَاسِقٍ إِذَا وَقَبَ (3) وَمِنْ شَرِّ النَّفَّاثَاتِ فِي الْعُقَدِ (4) وَمِنْ شَرِّ حَاسِدٍ إِذَا حَسَدَ (5) 
በል «በተፈልቃቂው ጎህ ጌታ እጠበቃለሁ፡፡ ከፈጠረው ፍጡር ሁሉ ክፋት፡፡ ከሌሊትም ክፋት ባጨለመ ጊዜ፤ በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (መተተኛ) ሴቶችም ክፋት፡፡ በተቋጠሩ (ክሮች) ላይ ተፊዎች ከኾኑት (ደጋሚ) ሴቶችም ክፋት፡፡›› አል ፈለቅ 1-5
አላህ ብቻ እንጂ ሌላ ማንም በማይችለው ጉዳይ ላይ አንድ ሰው ከችግር እንዲያወጣውም ይሁን ጥቅምን እንዲያስገኝለት ሌላን አካል ድረሱልኝ ብሎ መማፀኑ ችግሩን እንደማያስወግዱለት ወይም ጉዳቱን እንደማይመክትለት ከመግለፁም ባሻገር ይህ ተግባርና እምነት ክህደት እንደሆነ ተናገሯል፡፡
قال تعالى :(وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُو مِن دُونِ اللَّهِ مَن لا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَى يَومِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَن دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ) الأحقاف: ٥ – ٦
‹‹እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን (ጣዖት) ከአላህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡ ሰዎችም በተሰበሰቡ ጊዜ (ጣዖቶቹ) ለእነርሱ ጠላቶች ይኾናሉ፡፡ (እነሱን) መገዛታቸውንም ከሓዲዎች ይኾናሉ፡፡›› አል አህቃፍ 5-6
عن ابن مسعود رضي الله عنه أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال: (من مات وهو يدعو مندون الله نداً دخل النار) رواه البخاري 
ዓብድላህ ኢብኑ መስዑድ በአስተላለፉት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ “ከአላህ ውጭ ሌላን አካል ለአላህ አጋር አድርጎ መለመንን ሳይተው (ተውበት ሳያደርግ) የሞተ ሰው እሳት ገባ፡፡” ቡኻሪ ዘግበውታል

ففي الحديث الصحيح قال النبي صلى الله عليه وسلم لابن عباس رضي الله عنهما : (...إذا سألت فاسأل الله وإذا استعنت فاستعن بالله) رواه الترمذي وقال حديث حسن صحيح 
በሌላ ሐዲስም የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “መለመንን ስትፈልግ አላህን ብቻ ለምን፣ እርዳታንም ብትፈልግ በአላህ ብቻ ተረዳ” ቲርሚዚይ ዘግበውታል‎'

በሌላ ሐዲስም የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “መለመንን ስትፈልግ አላህን ብቻ ለምን፣ እርዳታንም ብትፈልግ በአላህ ብቻ ተረዳ” ቲርሚዚይ ዘግበውታል

Post a Comment

0 Comments