Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለት ...ለፍጡራን መሳል ይፈቀዳልን?

'‎ስለት ...ለፍጡራን መሳል ይፈቀዳልን?
በማህበረሰባችን ውስጥ ከሚንፀባረቁት የሽርክ አይነቶች አንዱ ዑለማዎች ከትልቁ ሽርክ አይነት የሚመድቡት ስለትን ከአላህ ሌላ ላለ አካል ማድረስ ነው፡፡ ስለት ማለት አንድ ሰው በእርሱ ላይ ግዴታ ያልሆነበትን ነገር በራስ ተነሳሽነት እራሱ ላይ ግዴታ ማድረጉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከአላህ በቀር ለማንም የማይፈፀም አምልኮ መሆኑን የሚጠቁሙ የቁርአንና የሀዲስ መረጃዎች ብዙ ናቸዉ፡፡ አላህ በሱረቱል ሀጅ እንዲህ ይላል፡-
 (وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ (الحج:٢٩
‹‹ስለቶቻቸውን ይሙሉ…›› አል ሀጅ 29
በሌላውም የቁርአን አንቀፅ አላህ ደጋግ የሆኑ ባሮቹን ባህሪ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-
(يُوفُونَ بِالنَّذْرِ وَيَخَافُونَ يَوْمًا كَانَ شَرُّهُ مُسْتَطِيرًا(الإنسان: ٧
‹‹ስለቶቻቸውን ይሞላሉ፡፡ መከራው ተሰራጭ የኾነንም ቀን ይፈራሉ፡፡›› ኢንሳን 7
 عن عائشة رضي الله عنها قالت: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "من نذر أن يطيع الله فليطعه. ومن نذر أن يعص الله فلا يعصه". رواه البخاري
 እናታችን ዓኢሻ በአስተላለፉት ሐዲስ ላይ የአላህም መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ፡- 
“አላህን ለመታዘዝ (የአላህ ህግ ለመተግበር) የተሳለ ሰው ስለቱን ያሟላ፣ በአላህ ላይ ለማመፅ (የአላህ ህግ ለመጣስ) የተሳለ ሰው ግን እንዳይስጥ” ቡኻሪ ዘግበውታል
እነዚህ የቁርአን የሐዲስ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ስለት ከአምልኮት አይነቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በተለይ በመጀመሪያው አንቀፅ ላይ ስለትን መሙላት ግዴታ መሆኑን በሚያጎላ መልኩ አላህ ካዘዘ ዒባዳ መሆኑን ያመለክታል፡፡ አንድን የአምልኮ ክፍል ከአላህ ሌላ አካል መስጠት ሽርክ ነው፡፡ ስለዚህም ስለትን ከአላህ ሌላ ለፍጡራን ማድረግ ከኢስላም የሚያስወጣ የሽርክ ተግባር ነው፡፡ ለደጋግ የአላህ ባሮች ፣ ለጅብሪልም ይሁን ለሌሎች መላእክት፣ ለሙታኖች፣ ለጂኖችና ለመሳሰሉት መሳል ግልፅ የሆነ የሽርክ ተግባር ነው፡፡ አላህ ከሽርክ ይጠብቀን!!‎'
ስለት ...ለፍጡራን መሳል ይፈቀዳልን?
በማህበረሰባችን ውስጥ ከሚንፀባረቁት የሽርክ አይነቶች አንዱ ዑለማዎች ከትልቁ ሽርክ አይነት የሚመድቡት ስለትን ከአላህ ሌላ ላለ አካል ማድረስ ነው፡፡ ስለት ማለት አንድ ሰው በእርሱ ላይ ግዴታ ያልሆነበትን ነገር በራስ ተነሳሽነት እራሱ ላይ ግዴታ ማድረጉ ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከአላህ በቀር ለማንም የማይፈፀም አምልኮ መሆኑን የሚጠቁሙ የቁርአንና የሀዲስ መረጃዎች ብዙ ናቸዉ፡፡ አላህ በሱረቱል ሀጅ እንዲህ ይላል፡-
(وَلْيُوفُوا نُذُورَهُمْ (الحج:٢٩
‹‹ስለቶቻቸውን ይሙሉ…›› አል ሀጅ 29
በሌላውም የቁርአን አንቀፅ አላህ ደጋግ የሆኑ ባሮቹን ባህሪ ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-
(يُوفُونَ بِالنَّذْرِ وَيَخَافُونَ يَوْمًا كَانَ شَرُّهُ مُسْتَطِيرًا(الإنسان: ٧
‹‹ስለቶቻቸውን ይሞላሉ፡፡ መከራው ተሰራጭ የኾነንም ቀን ይፈራሉ፡፡›› ኢንሳን 7
عن عائشة رضي الله عنها قالت: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : "من نذر أن يطيع الله فليطعه. ومن نذر أن يعص الله فلا يعصه". رواه البخاري
እናታችን ዓኢሻ በአስተላለፉት ሐዲስ ላይ የአላህም መልዕክተኛ እንዲህ ይላሉ፡-
“አላህን ለመታዘዝ (የአላህ ህግ ለመተግበር) የተሳለ ሰው ስለቱን ያሟላ፣ በአላህ ላይ ለማመፅ (የአላህ ህግ ለመጣስ) የተሳለ ሰው ግን እንዳይስጥ” ቡኻሪ ዘግበውታል
እነዚህ የቁርአን የሐዲስ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ስለት ከአምልኮት አይነቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ በተለይ በመጀመሪያው አንቀፅ ላይ ስለትን መሙላት ግዴታ መሆኑን በሚያጎላ መልኩ አላህ ካዘዘ ዒባዳ መሆኑን ያመለክታል፡፡ አንድን የአምልኮ ክፍል ከአላህ ሌላ አካል መስጠት ሽርክ ነው፡፡ ስለዚህም ስለትን ከአላህ ሌላ ለፍጡራን ማድረግ ከኢስላም የሚያስወጣ የሽርክ ተግባር ነው፡፡ ለደጋግ የአላህ ባሮች ፣ ለጅብሪልም ይሁን ለሌሎች መላእክት፣ ለሙታኖች፣ ለጂኖችና ለመሳሰሉት መሳል ግልፅ የሆነ የሽርክ ተግባር ነው፡፡ አላህ ከሽርክ ይጠብቀን!!

Post a Comment

0 Comments