Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም

የውሻ ጩኸት ደመናን አይጎዳም
በነብያችን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ላይ የሚሳለቅ እራሱን እንጂ እሳቸውን ምንም ሊያደርጋቸው አይችልም፡፡ የላካቸው አምላክ (መወሳትህን/ዝናህን ከፍ አደረግንልህ) ብሏቸዋል፡፡ ይሄው የዝናቸው ከፍ ማለትም ነው ዛሬ በርካታ ውሾችን እያስጮኻቸው ያለው፡፡ ትላንትም የዛሬዎቹ ውሾች አያቶች የመልእክተኛውን ክብር ሊያንቋሽሹ ሞክረው ነበር፡፡ አላህ ግን እራሱ ለመልእክተኛው ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ተከላካይ ጠበቃ ይሆንና መልእክተኛው ግን ነገሩን ንቀው እንዲተውት እንዲህ ይጠቁማቸዋል፡- {የታዘዝክበትንም ነገር በይፋ ግለፅ፤ አጋሪዎችንም ተዋቸው፡፡ እኛ ተሳላቂዎችን ሁሉ በቅተነሃል፡፡ (እነሱም) እነዚያ ከአላህ ጋር ሌላ አምላክን ያደረጉ ናቸው፤ በርግጥም (የስራቸውን ዋጋ) ወደፊት ያውቃሉ፡፡ አንተም በሚሉት ነገር ልብህ የሚጠብ መሆኑን በርግጥም እናውቃለን፡፡ ጌታህንም ከማመስገን ጋር አጥራው፤ ከሰጋጆቹም ሁን፡፡ እውነቱም (ሞት) እስከሚመጣህ ድረስ ጌታህን አምልክ፡፡} (አልሒጅር 94-99)
ስለዚህ ተሳላቂዎች ውሾች ቢሳለቁም የነብያችን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ዝና የበለጠ ይገናል፡፡ የውሾቹ ስም ይከስማል፡፡ውሻ ደግሞ ምን ታሪክ አለውና!! እስኪ የነብያችንና የትላንት ጠላቶቻቸውን ዝና አወዳድሩ፡፡ ሲጀመር መወዳደር ይችላሉ በጭራሽ!! “የሰማይና የመሬት ያክል ነው” ብንል እንኳ በትክክል አይገልፀውም፡፡
ግን የነብያችንን ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ክብር ለማጉደፍ ተፍ ተፍ የሚሉ ሰዎች አላማቸው ምን ይሆን መልሱ ግልፅ ነው፡፡
1. አንዳንዶቹ በነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እውቅና ሂሳብ እውቅና መሸመት የሚፈልጉ ናቸው፡፡ “አንዳንዶች ታዋቂዎችን በመተቸት ታዋቂ መሆን ይፈልጋሉ” ሲባል አልሰማችሁም
2. ሌሎቹ ደግሞ የኢስላም ውበቱና ሁለንተናዊነቱ የሚያስቀናቸው፤ ከፍተኛ ግስጋሴው የሚያስበረግጋቸው ናቸው፡፡ ስለሆነም ሙሐመድን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ሲያንቋሽሹ የኢስላም ውበቱ የሚደበዝዝ፣ ግስጋሴው የሚገታ ይመስላቸዋል፡፡ እውነታው ግን ተቃራኒው ነው፡፡ ኢስላም ዛሬ ጠላቶቹን እንቅልፍ በሚነሳ መልኩ በከፍተኛ ፍጥነት እየገሰገሰ ነው!!!! ስለዚህ ውሾቹ አመል ሆኖባቸው ይጩሁ እንጂ የኢስላምን ግስጋሴ ሊገቱት አይችሉም!! ውሾቹ ይጮሃሉ፣ ዋው! ዋው!....፡፡ ግመሉ ግን ጉዞውን ቀጥሏል፡፡ ውሻ ግመልን ማስቆም ከቻለች ትሞክር፡፡
ባይሆን ከኛ አንድ ነገር ይጠበቃል፡፡ ከሃዲዎችን የነብያችንን ስም ለመዘለፍ ያበቃቸው ለነብዩ አስተምሮ ያላቸው ጥላቻ መሆኑ ይታወቃል፡፡ አዎ የነቢዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ሱና እጅጉን ያስቆጫቸዋል!! እውነቱ ይህ ከሆነ ከሃዲዎችን የበለጠ ለማስቆጨት የሚጓጓ፤ ለሙሐመድ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እውነተኛ ወዳጅነቱን ማንፀባረቅ የሚፈልግ፣ ብሎም የአላህን ውዴታ ማትረፍ የሚሻ የበለጠ ወደመልእክተኛው ሱና ይቅረብ፤ ትእዛዛቸውንም ይፈፅም፤ ከከለከሉትም ይራቅ፡፡ ይህን የሚያደርግ ጠላቱን የበለጠ ያስቆጫል፡፡ የአላህንና የመልክተኛውንም ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም ውዴታ ያፍሳል፡፡ ያ ሱብሓላህ!!! የአላህና የመልክተኛውን ውዴታ ያገኘ ምን የቀረበት ነገር አለ!!!! ያ ወሃቡ አንተ ወፍቀን!!! ኣሚን

Post a Comment

0 Comments