Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ወንዶች ሴቶች ላይ አላህን እንፍራ

★♥ወንዶች ሴቶች ላይ አላህን እንፍራ♥★

አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህና አዛኝ በሆነው፤የአላህ ሰላምና ውዳሴ በመጨረሻውና የነብያቶች ሁሉ መደምደሚያ ተደርገው በተላኩት ነብያችን ላይ ይሁን።

ወንድሞቼ ጥቂት ስለ ሴቶች እንድንማማር ፈለግኩኝ የፈለኩበትም ምክንያት ቢኖር ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ ግሩፖች ላይ ሴትን ልጅ መስደብና ማንቋሸሽ ስራቸው አድርገው የያዙ ወንዶች ብቅ ብቅ ማለታቸው ነው።
 ወገኖቼ ሆይ! ኢስላም ለሴት ልጅ ትልቅ ቦታን ሰጥቶዋታል ለታላቅ አላማም አጭቶዋታል።

በጨለማው ዘመን(በጃሂሊያ ዘመን) የመካ አጋሪያን(ሙሽሪኮች) ጋር ሴት ልጅ ይታፈርባት እንደነበርና አልፎ ተርፎም እንደ ውርደት ተቆጥራ ከነ ህይወቷ ይቀብሯት ነበር። አላህም ይህን የአጋሪያንን(ሙሽሪኮችን) አስከፊ ባህሪ ቁርዓን ላይ ሲነግረን «አንዳቸውም በሴት ልጅ በተበሰረ ጊዜ እርሱ የተቆጨ ኾኖ ፊቱ ጠቁሮ ይውላል * በእርሱ ከተበሰረበት ነገር መጥፎነት በውርደት ላይ ሆኖ ይያዘውን ወይስ በአፈር ውስጥ ይደብቀውን(በማለት እያምታታ) ከሰዎች ይደበቃል።  ንቁ! የሚፈርዱት(ፍርድ) ምንኛ ከፋ!»(ሱረቱ አን ነህል 58–59) 

ከዚህ የቁርዓን አንቀፅ ብዙ ልንማራቸው የሚገቡ ነገሮች ቢኖሩም ሁለት አንኳር ነገሮችን ላነሳላችሁ እወዳለሁ፤
 
☞ የመጀመሪያው፦ ኢስላም ለሴት ልጅ ክብር የቆመ ፍትሀዊ የሆነ መለኮታዊ እምነት መሆኑን፤ እህቴ ሆይ!  ኢስላም የአንቺን ክብር ከፍ አድርጎልሻል ኢስላም የሰጠሽን ክብር ደግሞ አንቺው ነሽ ልትጠብቂው የሚገባው ኢስላም የሰጠሽን ክብር ሊቀሙሽ የመጡትን የሰይጣን ጭፍራዎች ልትርቂያቸው ይገባሻል። እኩልነት ሲባል ሴት ልጅ የሌላትን መብት ሰጥቶ አይዞሽ እያሉ ማጨብጨብ ብቻ እንዳልሆነ አንቺም ተረጂልኝ። እየጮሁ ያሉት የእውነት ለአንቺ መብት ተቆርቁረውልሽ መስሎሽ እንዳትሸወጂ ይልቁንስ አንቺን ከዲንሽ (ከእምነትሽ) ወደ ኋላ አስቀርተውሽ ትውልድን መግደል የሚፈልጉ አረመኔዎች ናቸውና ተጠንቀቂ። 

☞ ሁለተኛው፦ አላህ የሴት ልጅን መወለድን ብስራት ብሎ ነው የገለፀው፤ ታዲያ አላህ ብስራት ናት ያላትን ድንቅ ፍጥረት አንተ ማን ሆንክና ነው የምታንቋሽሻትና የምትሰድባት???

 የአንተ ክፋይ መሆኗን ዘነጋህን??? 

ቲርሚዚይ በዘገቡት ሀዲስ ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም)  እንዲህ ይላሉ፤  «ሴቶች የወንድ ልጅ ክፋዮች ናቸው።» ብለዋል። አላህም በቁርዓኑ እንዲህ ይላል «ምዕመናንና ምዕመናትም ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው ፤በመልካም ነገር ያዛሉ፤ከመጥፎም ይከለክላሉ፤ሰላትንም ይሰግዳሉ፤አሏህንና መልዕክተኛውን ይታዘዛሉ። እነዚያን አላህ በእርግጥ ያዝንላቸዋል አሏህ አሸናፊ ጥበበኛ ነውና።» (ሱረቱ አት ተውባህ 71) 

☞ ወንድሜ ሆይ! 

ከዚህ የቁርዓን አንቀፅ የመተሳሰብና የመብት እኩልነትን እንጂ ሌላን አትረዳም። ስለዚህም አወህቶችን ዘክብር።
በወንድነትህ አትኩራራ። አላህ ዘንድ ማንነትህ የሚለከሰው ባለህ ተቅዋ እንጄ በፆታ አይደለም። ወንድ በመሆንህ የተለዪ ህግጋት ይመለከቱሀል። ሴትም እንዲሁ። ነገር ግን ሴቶችን ማክበርና መንከባከብ ኢስላማዊ ስልጣኔ ሲሆን ሴቶችን መናቅ ግን የጃሂሊያ ቅሪት መሆኑን አትርሳ። 

☞ ወንድሜ ሆይ! አደብ ይኑርህ አትቅለብለብ ያማረብህ መስሎህ ሴትን እየሰደብክና እያዋረድክ የጃሂሊያውን ዘመን እየደገምከው እንደሆነ አትርሳ።

 ይህን የነብይህን ኑዛዜ አጥብቀህ ያዝልኝማ፤

 ☞ ኢማሙ አት ቲርሚዚይ በአስተላለፉት ሀዲስ ረሱል(ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፤ «ለሴቶቻችሁ ጥሩን(ነገር) በመስራት አደራ እላችኃለው…» አሉ።

 ☞ በሌላ ዘገባ አንድ ሰውዬ ረሱል (ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር መጥቶ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው ሚስት ባል ላይ ያላት ሀቅ ምንድን ነው??? አለ። 

 እሳቸውም ምግብ ስትበላ ልታበላት፣ልብስ ስትለብስ ልታለብሳት፣ፊቷን ላትመታት፣ላታነውራት(ላትሰድባት) እና ከቤት ውጪ በማኩረፍ ላትርቃት በማለት መለሱለት።» 
                     ኢማሙ አት ቲርሚዚይ ዘግበውታል 

 አየህ ሴት ልጅ ምን አይነት ደረጃ እንዳላት??? አንተ ልታሞካሻትና ልትንከባከባት ሲገባ አላህና መልዕክተኛው የሰጧትን ክብር ለምን ይሆን የማታከብራት??? 

በመጨረሻም ሴት ልጅን ስትሰድብና ስታንቋሽሽ እነዚህ ነገሮችን ቆም ብለህ አስተውል፤

☞ከምንም ነገር በፊት እናትህ ሴት መሆኗን
☞ክፋይህ መሆኗን
☞ያለእሷ ህይወትህ በከፊል ጎዶሎ መሆኑን
☞ከሀራም መጠበቂያ መሸሸጊያህ(መሰተሪያህ) መሆኗን
☞የልጆችህ እናት መሆኗን አውቀህ አክብራት!!! 

ተንከባከባት አታስከፋት መልዕክቴ ነው
አቡ አቲካህ
★ወንዶች ሴቶች ላይ አላህን እንፍራ★