Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል አስር

ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል አስር

የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ

የሀውፍ (የፍራቻ) መረጃ ¹
አላህ እንዲህ ይላል
«« እውነተኛ አማኞች ከሆናችሁ እነሡን አትፍሯቸውቸው እኔን ፍሩኝ»

የረጃእ (የክጃሎት) መረጃ ²

አላህ እንዲህ ይላል ፦

«የጌታውን መገናኘት ለሚከጅል ሠው መልካም የሆነን ስራ ይስራ ጌታውን በማምለክ ላይም አንድንም አያጋራ»

_________
አጭር ማብራርያ
_________
¹ ሀውፍ (ፍራቻ) ከኢባዳ አይነቶች መካከል የሚቆጠር ነው.

★ ሀውፍ በልባችን ከምንሠራቸው የኢባዳ አይነቶች መካከል አንዱ ነው

★ ሀውፍ ማለት ,፦ የታዘዘውን መስራት ከተከለከለው  ነገር መቆጠብ

★ ሀውፍ ሦስት አይነታዎች አሉት 

① የድብቅ ፍራቻ ፦ ይህ የፍራቻ አይነት በውስጡ ማላቅንእና ውዴታን ያቀፈ ፍርሀት ነው ይህም ጂንን ፣ እቀብር
ውስጥ ያለን ሙት አካል ፣ ወይም ጣጉትን ሌላም ከአላህ ውጪ ያሉ ምንም ሊያደርጉ የማይችሉ ደካማ ፍጥረቶችን
ባሉበት ቦታ ሆነው ይጎዱኛል ብሎ ማሠብ ይህም ፍራቻ ሊፈጠር የሚችለው ጣኡቱ ፣የሦሊሁ ቀብር ፣ ወይም የጂኑ
አልያም ጣኡቱ ይጎዱኛል ብሎ የሚፈራቸው ሠው ዘንድ  እጅጉኑ የተወደዱ እና የተላቁ አካላቶች በመሆናቸው ነው ።

★ እነዚህ ጣኦት አምላኪያን የሚፈሯቸውን አማልክቶች ከራሣቸውም ባለፈ መልኩ ይህ ነገር መጥፎ እንደሆነ ፣
ሽርክ እነደሆነ የሚያስጠነቅቋቸውንም በነዚሁ ደካማ አማልክቶቻቸው ሊያስፈራሩ ይሞክራሉ. ይህን አስመልክቶ አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ስለ ሁድ ህዝቦች ሢናገር እንዲህ ይላል.
«««ከፊሎቹ አማልክቶቻችን በክፋ ነገር(በእብደት) ነክተውሀል እንጂ. ሌላን አንልም» አሉ»»

★ ነብዩላህ ሁድ ይህንን ማስፈራሪያቸውን ቦታ ሣይሠጡ
―
«እኔ አላህን አስመሰክራለሁ ከምታጋሩት ንፁህ መሆኔንመስክሩ» አላቸው» . ሡረቱል ሁድ

★ ሁድንም ባስፈራሩበት አምሣያ አሸረፈል ሀልቅ የሆኑትንም ሙሀመድ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለምንም
ለማስፈራራት ሞክረው ነበር አላህ እንዲህ ይላል
« አላህ ባርያውን በቂ አይደለምን? በእነዚያ ከእርሡ ሌላ በሆኑትም (ጣኦት) ያስፈራሩሀል ። » ዙመር

★ ከአላህ. ውጪን ያለ አካልን መፍራት ዛሬም ላይ የተለያዩ ሠዎች ወድቀውበት የሚገኙት ወሣኝ የኡማው ችግር ሆኖ ይታያል

★ ይህም ከመሆኑም ጋር አብዘሀኛውን አሊምና ዳኢ ቢዚ ያደረገው ጉዳይ ይህ ሆኖ አይታይም

★ ስለተለያዩ የኢስላም ክልክላቶች እና ትእዛዛቶች ሢያስተምሩ ስለ ሽርክ እና ስለ ቢድአ ማውራትን ግን እንደ ሁለተኛ ጉዳይ ተቆጥሮ ይታያል

★ የነብያቶች ገድል ግን በአጠቃላይ የሚያጠነጥነው ከሽርክ ማስጠንቀቅ ላይና ወደ ተውሒድ በመጣራት ላይ
ነው

★ እኛም የዳእዋችንን መጀመርያ ማድረግ ያለብን ወደ ተውሒድ በመጣራት እና ከሽርክ በማስጠንቀቅ ማድረግ
አለብን!!

② ሁለተኛው የፍራቻ አይነት ፦ ሠዎችን ፍራቻ አላህ ያዘዘውን አለመተግበር ወይም የከለከለውን  አለመከልከል ለምሣሌ   ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ
ወሠለም  ሡሪን ከቁርጭምጭሚት በላይ
ማድረግ እንደሌለብን ነግረውን ሣለ ሡሪዬን ካሣጠርኩ ሠዎች ይስቁብኛል ምናምን ብሎ የአላህን ትእዛዝ
መተላለፍ.

★ ይህ ከትንሹ ሽርክ ይመደባል

③ የተፈጥሮ ፍራቻ ፥ የሠው ልጅ በተፈጥሮ የተለያዩ ነገራቶችን ይፈራል ለምሣሌ አውሬ ፣ ጠላት ፣ በጣም ፈሪ
ከሆነ ደግሞ ጥላውንም ይፈራል ይህ የፍራቻ አይነት  (ያልተከለከለ) የፍራቻ አይነት ነው ።

² ረጀአ (ክጃሎት)
★ ረጃእ ማለት የሠው ልጆች የማይችሉት የሆነን ነገር ከአላህ ሡብሀነሁ ወተአላ መመኘት ነው ምኞት የሚባለውን ነገር ለሁለት ከፍለነው ልንመለከት
እንችላለን

① ምስጉን የሆነው የክጃሎት አይነት ፦ ከስራ ጋር የተያያዘ የክጃሎት አይነት ሲሆን አላህ ዘንድ ያለውን ነገር
የሚመኘው (የሚከጅለው) እጁን አጣጥፎ ቁጭ ብሎ ሣይሆን እየተንቀሣቀሠ ነው አላህ. እሡ ዘንድ ያለውን ነገር
የሚከጅል ሠው መልካም ስራ መስራት እንዳለበት እንዲህ ሢል ይነግረናል

② መሠረተ ቢስ ምኞት ፦ ይህ ደግሞ አላህ ዘንድ ያለውን ያለ ምንም ልፋትና ድካም መመኘት ማለት ነው ይህ
የክጃሎት አይነት የተወቀሰ የክጃሎት አይነት ነው የአላህ ሠላት እና ሠላም በመላዕክተኛው ላይ ይውረድ

★ በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

★ share. ማድረጎን እንዳይረሡ