Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል ዘጠኝ

ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል ዘጠኝ
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ ፦
★ከሀዲስ. መረጃ ¹
«ዱአ የኢባዳ አስኳል ነው» ²
አላህ እንዲህ ይላል ፦ « ጌታችሁም አለ ለምኑኝ
እቀበላቹሀለው እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩትን የተዋረዱ
ሢሆኑ ጀሀነምን ይገባሉ»³ ጋፊር
_________
አጭር ማብራሪያ
___________
¹ ዱአ ከኢባዳ አይነቶች ውስጥ እንደሚካተት የሚያሣይ
መረጃ ለማለት ነው
² ይህ ሀዲስ ሀሣቡ ትክክል ቢሆንም ሀዲሱ ከነብዩ
ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አልተገኘም ይህንን ቃል
የሚደግፍ.ሠሒህ የሆነ ሀዲስ ተዘግቧል « ዱአ እሡ ኢባዳ
ነው» የሚል
³ ዱአ ከኢባዳ አይነቶች መካከል አንዱና ዋነኛው የኢባዳ
አይነት ነው ዱአ ኢባዳ ለመሆኑ የተለያዩ የቁርአን አያዎች
እና ሠሒህ ሀዲሦች ያመላክታሉ ከእነዛም ውስጥ ሼሁ
የጠቀሡት የቁርአን አያ ግልፅ.የሆነ አመላካች ነው
አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ዱአን ኢባዳ ብሎ ጠራው
« ጌታችሁም አለ ለምኑኝ እቀበላቹሀለው እነዚያ እኔን
ከመገዛት የሚኮሩትን የተዋረዱ ሢሆኑ ጀሀነምን ይገባሉ»³
ጋፊር
★ ለምኑኝ ብሎ ካነሣሣን ቡሀላ በኩራት እሡን
የማይለምኑት ለማስፈራራት «እኔን ከመገዛት »በሚል ቃል
ገልፆታል.
★ ቁርአን እና ሀዲስ የሚደጋገፋ ነገሮች መሆናቸውንም
ግልፅ ማሣያ ነው
አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ዱአን በሌላ ቦታ ላይ ዲን
(ሀይማኖት) ሢል ይጠራዋል
አላህ እንዲህ ይላል
«ሀይማኖትን ለሡ ጥርት ያደረጋችሁ ስትሆኑ ለምኑት »
ጋፊር
★ ይህ የሚያመላክተው የዱአን ትልቅነት ነው
★ ይህን ታላቅ የኢባዳ አይነት ከአላህ ውጪ ላለ አካል
አሣልፎ መስጠት ፈፅሞ ደተከለከለ ነገር ከመሆኑም ባለፈ
ይህንን የተገበረ ሠው ከእስልምና በቀይ ካርድ ይሠናበታል
አልህ እንዲህ ሲል ያዘና « መስገጃ ስፍራዎች በአጠቃላይ
የአላህ ናቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትለምኑ»
★ በሌላም ቦታ ላይ አንድ አካል ቢያንስ አራት ነገሮችን
እንደማያሞሉ እና ደካማዎች መሆናቸውን ከመንገር ጋር
መለመን እንደሌለባቸው እንዲሆ ሲል ይነግረናል ፦
«እነዛ (ከአላህ ሌላ አማልክት )ብላችሁ የምታስቧቸውን
ጥሩ በሠማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ታክልን
አይችሉም ፡ከእነሡም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና
የላቸውም ፡ ከእነሡም ለእርሡ ምንም አጋዥ የለውም።
በላቸው (23) ምልጃም እርሡ ለፈቀደለት ሠው ቢሆን
እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም»
★እዚህ የቁርአን አንቀፅ ውስጥ ከአላህ ውጪ የሚለመኑ
አካላት ደካማዎች ለመሆናቸው ለማሣያነት የሚሆኑ አራት
ነገሮችን ጠቅሦል እነሡም ከአላህ ውጪ የሚለመኑ
አካላቶች
① ሠማይና ምድር ሢፈጠሩ የብናኝ ታክልን አልሠሩም
② ሠማይና ምድር ሢሠሩ ሸሪካም አልነበሩም
③ አላህም ከነሡ አጋዥ የለውም (አጋዥም አልነበሩም)
④ ምልጃቸውም በራሣቸው ፍቃድ ሣይሆን ከአላህ ፍቃድ
ቡሀላ ነው ተሰሚነት ሊኖረው የሚችለው
★ ከአላህ ውጪ ያለን ሊሠማ የማይችልን ደካማ ፍጥረት
ከሚለምን ሠው ይበልጥ የጠመመ መንገዱንም የሣተ
የለም
አላህ እንዲህ ይላል « እስከ ትንሣኤ ድረስ ለእርሡ
የማይመልስለትን (ጣኦት)ከአላህ ሌላ ከሚለምን ሠው.
ይበልጥ የተሣሣተ ማነው? እነርሡም ከጥሪያቸው
ዝንጉዎች ናቸው»
★ ሙት (ግኡዝ) የሆነ አካል ብትለምነውም
የሚጠራቸውን ሠው ጥሪአይሠሙም አላህ እንዲህ ይላል
«ብትጠሯቸው አይሠሟቹም» »
★ምክንያቱም የሚጠሩት አካላቶች ሙት ግኡዝ ስለሆኑ
(ፈርደን) እንደው ይሠማሉ እንኳን ብንል መልስ አይሠጡም
« ቢሠሙ እንኳን ምላሽ አይሠጡም»
★ ይባስ ብሎ እነዚህ የሚለመኑ አካላቶች የቂያማ ቀን
የተገዟቸውን ሠዎች ይከዷቸዋል ምክንያቱም ለምኑን
ብለው አላዘዙማ
« በትንሣኤው ቀንም እነርሡን ከአላህ ጋር ማጋራታችሁን
ይክዳሉ
★ ይህን ከባድ ሚስጥር (የሚለመኑት አካላቶች
እንደማይሠሙ ፡ መልስ እንደማይሠጡ ፡ የቂያማ ቀንም
ከአላህ ጋር ያጋራቸውን እንደሚከዱ) ከውስጥ አዋቂው
በቀር ማንም አያውቅም
« እንደ ውስጥ አዋቂው ማንም አይነግርህም» ሡረቱል
ፋጢር
♂ ታድያ ለምን??? እነዚህ የማይሠሙ ግኡዝ አካላቶች
ይለመናሉ እንዴትስ ተብሎ አላህን መለመን ይተዋል???
∞ የሠው ልጆች አቅል ምን ሆኗል ሀያሉና ሠሚውን ጌታ
ትቶ የማይሠማውን አካል ይጣራል??
∷ ይህንን ማድረግ የለበትም!!
በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

share ማድረጉን እንዳይረሡ!!
ኡሡሉ ሠላሣ ፦ ክፍል ዘጠኝ
የኪታቡ ፀሀፊ እንዲህ አሉ ፦
★ከሀዲስ. መረጃ ¹
«ዱአ የኢባዳ አስኳል ነው» ² አላህ እንዲህ ይላል ፦ « ጌታችሁም አለ ለምኑኝ እቀበላቹሀለው እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩትን የተዋረዱ ሢሆኑ ጀሀነምን ይገባሉ»³ ጋፊር
_________
አጭር ማብራሪያ
___________
¹ ዱአ ከኢባዳ አይነቶች ውስጥ እንደሚካተት የሚያሣይ መረጃ ለማለት ነው
² ይህ ሀዲስ ሀሣቡ ትክክል ቢሆንም ሀዲሱ ከነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም አልተገኘም ይህንን ቃል
የሚደግፍ.ሠሒህ የሆነ ሀዲስ ተዘግቧል « ዱአ እሡ ኢባዳ
ነው» የሚል
³ ዱአ ከኢባዳ አይነቶች መካከል አንዱና ዋነኛው የኢባዳ አይነት ነው ዱአ ኢባዳ ለመሆኑ የተለያዩ የቁርአን አያዎች እና ሠሒህ ሀዲሦች ያመላክታሉ ከእነዛም ውስጥ ሼሁ የጠቀሡት የቁርአን አያ ግልፅ.የሆነ አመላካች ነው አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ዱአን ኢባዳ ብሎ ጠራው
« ጌታችሁም አለ ለምኑኝ እቀበላቹሀለው እነዚያ እኔን ከመገዛት የሚኮሩትን የተዋረዱ ሢሆኑ ጀሀነምን ይገባሉ»³ ጋፊር
★ ለምኑኝ ብሎ ካነሣሣን ቡሀላ በኩራት እሡን የማይለምኑት ለማስፈራራት «እኔን ከመገዛት »በሚል ቃል ገልፆታል.
★ ቁርአን እና ሀዲስ የሚደጋገፋ ነገሮች መሆናቸውንም ግልፅ ማሣያ ነው አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ዱአን በሌላ ቦታ ላይ ዲን (ሀይማኖት) ሢል ይጠራዋል አላህ እንዲህ ይላል
«ሀይማኖትን ለሡ ጥርት ያደረጋችሁ ስትሆኑ ለምኑት » ጋፊር
★ ይህ የሚያመላክተው የዱአን ትልቅነት ነው
★ ይህን ታላቅ የኢባዳ አይነት ከአላህ ውጪ ላለ አካል አሣልፎ መስጠት ፈፅሞ ደተከለከለ ነገር ከመሆኑም ባለፈ ይህንን የተገበረ ሠው ከእስልምና በቀይ ካርድ ይሠናበታል አልህ እንዲህ ሲል ያዘና « መስገጃ ስፍራዎች በአጠቃላይ የአላህ ናቸው ከአላህ ጋር አንድንም አትለምኑ»
★ በሌላም ቦታ ላይ አንድ አካል ቢያንስ አራት ነገሮችን እንደማያሞሉ እና ደካማዎች መሆናቸውን ከመንገር ጋር መለመን እንደሌለባቸው እንዲሆ ሲል ይነግረናል ፦
«እነዛ (ከአላህ ሌላ አማልክት )ብላችሁ የምታስቧቸውን ጥሩ በሠማያትም በምድርም ውስጥ የብናኝ ታክልን አይችሉም ፡ከእነሡም በሁለቱም ውስጥ ምንም ሽርክና የላቸውም ፡ ከእነሡም ለእርሡ ምንም አጋዥ የለውም። በላቸው (23) ምልጃም እርሡ ለፈቀደለት ሠው ቢሆን እንጂ እርሱ ዘንድ ምንም አትጠቅምም»
★እዚህ የቁርአን አንቀፅ ውስጥ ከአላህ ውጪ የሚለመኑ አካላት ደካማዎች ለመሆናቸው ለማሣያነት የሚሆኑ አራት ነገሮችን ጠቅሦል እነሡም ከአላህ ውጪ የሚለመኑ አካላቶች
① ሠማይና ምድር ሢፈጠሩ የብናኝ ታክልን አልሠሩም
② ሠማይና ምድር ሢሠሩ ሸሪካም አልነበሩም
③ አላህም ከነሡ አጋዥ የለውም (አጋዥም አልነበሩም)
④ ምልጃቸውም በራሣቸው ፍቃድ ሣይሆን ከአላህ ፍቃድ ቡሀላ ነው ተሰሚነት ሊኖረው የሚችለው
★ ከአላህ ውጪ ያለን ሊሠማ የማይችልን ደካማ ፍጥረት ከሚለምን ሠው ይበልጥ የጠመመ መንገዱንም የሣተ የለም አላህ እንዲህ ይላል « እስከ ትንሣኤ ድረስ ለእርሡ
የማይመልስለትን (ጣኦት) ከአላህ ሌላ ከሚለምን ሠው. ይበልጥ የተሣሣተ ማነው? እነርሡም ከጥሪያቸው ዝንጉዎች ናቸው»
★ ሙት (ግኡዝ) የሆነ አካል ብትለምነውም የሚጠራቸውን ሠው ጥሪአይሠሙም አላህ እንዲህ ይላል
«ብትጠሯቸው አይሠሟቹም» »
★ምክንያቱም የሚጠሩት አካላቶች ሙት ግኡዝ ስለሆኑ (ፈርደን) እንደው ይሠማሉ እንኳን ብንል መልስ አይሠጡም « ቢሠሙ እንኳን ምላሽ አይሠጡም»
★ ይባስ ብሎ እነዚህ የሚለመኑ አካላቶች የቂያማ ቀን የተገዟቸውን ሠዎች ይከዷቸዋል ምክንያቱም ለምኑን ብለው አላዘዙማ « በትንሣኤው ቀንም እነርሡን ከአላህ ጋር ማጋራታችሁን ይክዳሉ
★ ይህን ከባድ ሚስጥር (የሚለመኑት አካላቶች እንደማይሠሙ ፡ መልስ እንደማይሠጡ ፡ የቂያማ ቀንም ከአላህ ጋር ያጋራቸውን እንደሚከዱ) ከውስጥ አዋቂው በቀር ማንም አያውቅም
« እንደ ውስጥ አዋቂው ማንም አይነግርህም» ሡረቱል ፋጢር
♂ ታድያ ለምን??? እነዚህ የማይሠሙ ግኡዝ አካላቶች ይለመናሉ እንዴትስ ተብሎ አላህን መለመን ይተዋል???
∞ የሠው ልጆች አቅል ምን ሆኗል ሀያሉና ሠሚውን ጌታ ትቶ የማይሠማውን አካል ይጣራል??
∷ ይህንን ማድረግ የለበትም!! በአላህ ፍቃድ ይቀጥላል

share ማድረጉን እንዳይረሡ!!