Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

መውሊድ ለሚያከብር ሰዉ ጥያቄ

መውሊድ ለሚያከብር ሰዉ ጥያቄ
*) ቁርዓን ላይ መውሊድ አክብሩ የሚል የለም፣
*) የነብዩ ሙሃመድም(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይሁን ሰሃባዋቻቸው አስተምሮት፣ ተግባር ላይ መውሊድ አክብሩ የሚል የለም።
ታድያ አንተ የአላህ ባርያ ሆይ! አላህ ማስረጃ አምጣ ለስራህ ብሎ ቢጠይቅህ "ሸህ እገሌ ናቸው ይቻላል ያሉኝ" ብለህ መልስ የሚሆንህ ይመስልሃል?
በል እንዲያውም አላህ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያላዘዙትን በመስራት የሚቃረኗቸውን እንዲህ ሲል ከባድ ዛቻ ዝቷል
فَلْيَحْذَرِ الَّذِينَ يُخَالِفُونَ عَنْ أَمْرِهِ أَنْ تُصِيبَهُمْ فِتْنَةٌ أَوْ يُصِيبَهُمْ عَذَابٌ أَلِيم
እነዚያ (የአላህ መልክተኛን) ትእዛዙን የሚጥሱ (በዱንያ) መከራ እንዳትደርስባቸው ወይንም (በአኸይራ) አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ።
አላህ መልክተኛውን በመቃረንህ ይህን እየዛተብህ እንዴት ሸይጧን (የሰው እና የጂን) ነብዩን መውደድ በሚል ስም ሲጫወትብህ አእምሮህ ማሰብ ተሳነው።
አንተ/ቺ መውሊድ አክባሪ ሆይ!
በናንተ/ቺው ሎጂክ "ሰሀባዎች መውሊድን ስላላከበሩ ነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አይወዱም ማለት ነው?"
ቢድዓ ሁሉ ጥመት ነው፣ ጥመት ሁሉ የእሳት ነው።
አላህ መልክተኛው እና ሰሃባዎች ከቆሙበት ላይ የሚቆሙ ያድርገን።