Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የመውሊድ ትክክለኛ ገፅታ እና የሚስተዋሉ ብዠታዎች

****የመውሊድ ትክክለኛ ገፅታ እና የሚስተዋሉ ብዠታዎች****
~~~~በመሠረቱ በሀቅ እና መልካም ነገር መተባበር እንዲሁም ስህተትና ወንጀል ነክ ነገሮችን እንደሁኔታው አግባብነት ባለው መልኩ ማስተካከል፣ማስወገድ••• የኢስላም መመሪያ ስለመሆኑ እሙን ነው።
~~~~~በመሆኑም በበርካታ ሙስሊም ወንድሞቻቻንና እህቶቻችን ዘንድ የሚከበረውን የመውሊድ ክብረ በዐል አስመልክቶ ያለውን ገፅታ በአላህ ፈቃድ እንደሚከተለው ለመዳሰስ እንሞክራለን።
~~~~ አምላካችን አላህ በዕዝነቱና ቸርነቱ የሠው ልጆች ዐይነታ፣የነብያት መደምደሚያ፣የሩሱሎች ቁንጮ የሆኑትን ነብያችንን(ሠለላሁ ዐለይሂ ወሠለም) ወደ እኛ ልኮልናል።እሳቸውም እንዴት አላህን መገዛት እንዳለብን በሚገባ አስተምረዋል። በጎ የተባለን ሁሉ አመላክተዋል:ከመጥፎ ሁሉም አስጠንቅቀዋል።አላህም በሳቸው አማካይነት ዲናችንን የተሟላ አድርጎታል።አላህም(ሱብሃነሁ ወተዓላ)እንዲህ ይላል "ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ•••" "መልዕክተኛው የሠጣችሁን ተቀበሉ:ከከለከላችሁም ነገር ታቀቡ•••"
~~~~ኢስላም ከትንንሽ ተግባራት እስከ ታላላቅ ዒባዳዎች(በዐላትን ጨምሮ)በግልፅና በማያሻማ መልኩ አስተምሯል።ይሁን እንጂ የመውሊድ በዐልን አስመልክቶ አንዳችም መመራያ የለም።ኢባዳ ደግሞ መሠረቱ ተውቂፊያ(በመመሪያ የተገደበ)ነው።ከዚህ ውጭ ከሆነ ውድቅና ተመላሽ መሆኑ እንደሚከተለው በሃዲስ ተጠቅሷል፡"የኛ መመሪያ የሌለበትን አንዳች ተግባር የሠራ እርሱ ተመላሽ ነው"
~~~~የተከበራችሁ ወንድምና እህቶቼ የመውሊድ በዐል በቁርዓንም ሆነ ሃዲስ በኢጅማዕም ሆነ ትክክለኛ ቂያስ ምንም ዓይነት መረጃ የለውም።ታዲያ ረሱላችን(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም)፣ሠሃቦች፣ አህለል በይት፣ታብዒዮች፣የታብዒይ ተከታዮች•••አራቱ ዕውቅ አኢማዎች(አቡ ሃኒፋ፣ማሊክ፣ሻፊዕ፣አህመድ)በፍፁም አላከበሩትም፡አላዘዙምም•••ኸይር ቢሆን እነሱ አይቀድሙንም ነበርን?ወይስ እነሱ ያላወቁትን እኛ አወቅን?ሠሃቦች የተጔዙበት ጎዳና አይበቃንም?አልያስ ከነሡ በበለጠ መልዕተኛውን እንወዳለን?ዐብደላ ኢብኑ ዑመር/ዐባስ/(ረዲየላሁ ዐንሁ)እንዲህ ይል ነበር"አርአያነት የፈለገ የነዛ ያለፉ ሠሀቦችን መንገድ ይከተል•••"ከዚህ አስቀድመውም ነብያችን(ሰለላሁ ዐለይሂ ወሠለም)እንዲህ ብለዋል"ወደ ፊት ከኔ በኋላ የሚኖር ሠው በርካታ ሌዪነቶችን ይመለከታል፡እናም አደራችሁን የኔንና የተቀኑትን የኹለፋኡ ራሺዲንን መንገድ አጥብቃቻሁ ያዙ•••በዲን ላይ ከሚመጡ አዳዲስ ፈጠራዎችም ተጠንቀቂ፡ፈጠራ ሁሉ አዲስ ነገር ነው፡አዲስ ነገር ሁሉም ጥመት ነው"በሌላ ሃዲስ"ጥመት ሁሉ የእሳት ነው"
~~~ውድ ወገኖቼ አስተውሉ እንግዲህ ነገሩን ሁሉ የአላህ መልዕክተኛ ቀደም ብለው እንዴት እንዳመላከቱና እንዳስጠነቀቁን!!አላሁ አክበር ችግሩን ከነመፍትሄው።የመውሊድን በዐል ጨምሮ ከሌሎችም በዲናችን ላይ ከተፈጠሩ የተረጋገጠ መሠረት ከሌላቸው አዳዲስ ነገሮች የአንድ ሙስሊም አቋም ምን መሆን እንዳለበት የሚጠቁም ነብያዊ ተግሳፅ!
ወደ ማንም ግለሠብና ቡድን አመለካከት፣ወደ የትኛውም ፀረ ሱና አቋም •••መዘንበል ሣይሆን በመልዕክተኛውና ኹለፋኡ ራሺዲን(ሠሃቦች) ፈለግ መጓዝ!!!
~~~~~~ታዲያ ይህ በዲችን መሠረት የሌለውና ቢድዓ መሆኑ በሚያከብሩት ወገኖቻችን ዘንድ ሁሉ የተረጋገጠው የመውሊድ በዐል መቼ ተፈጠረ ?ከተባለ
ራሳቸውን ፋጢሚይን ብለው በሚሠይሙት ዑበይዲዮች በሂጅራ አቆጣጠር ከ350 እና 400 ዓመታት በኋላ ነው።በሌላ የታሪክ ዘገባ ንጉስ ሙዝፈር የተባለ ግለሠብ በ6ኛው ቀርንመጨረሻ ወይም በ7ኛው ቀርን መጀመሪያ አካባቢ መሆኑ ተጠቆሷል።
ሡብሃነላህ!!!ተመልከቱ የግዜውን ርቀት፣ከመሆኑም ጋር መውሊድ ለመከበሩ መረጃ አለ
በማለት ከሚነገሩ ሹብሃቶች(ማመሣሠያ ማደናገሪያዎች)መሃከል አበይት የሆኑትን በቀጣይ እንመለከታለን ኢንሻ አላህ••••ይቀጥላል