Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አብሬት



አብሬት
።።።

በየ ዓመት ረጀብ 15 ይከበራል ። ምንም ታስቦ ይመስረት በኢስላም መነፅር ሲታይ ክብረ በዓሉ ቢድዓ ነው ነብዩ ያልሰሩት አዲስ ፈጠራ ። አዒሻ ባስተላለፈችውና ሙስሊም በዘገቡት ሀዲስ የአላህ መልክተኛ እንዲህ ብለዋል " የኛ ትዕዛዝ የሌለበት የትኛውም አይነት ስራ የሰራ ስራው ተመላሽ ነው ።" ፈጠራ ደግሞ ጥመት ነው የጥመት መጨረሻው እሳት ነው የአላህ መልክተኛ እንዳስጠነቀቁት
በአጭር የዚህ ቢድዓዊ ክብረ በዓል ውጤቱ ይህን ይመስላል ። ከፈጠራነቱ በሻገር ይህ ነው የማይባል ተቆጥሮ የማይዘለቅ የሽርክ አይነት ይሰራል። የአላህ ሀቅ ለፍጡር ይሰጣል ። በተለያዩ አቅጣጫዎች በሬና ምኩት እየተነዳ ስለታቸውን ለመሙላት መሰዋት ያቀርባሉ ፤ ከመቃብሩ ዙርያ በማጎብደድ ስሮንደ (ድረሱልን) እያሉ ይማፀናሉ ፤ ያገኛቸውን ችግር አንድ በአንድ በዝርዝር ያቀርባሉ ሰምተው ምላሽ መስጠት ባይችሉም እንኳ ። የተለያዩ የውዳሴ ዜማዎችንም በግሩፕ ያዜማሉ ፤ ዘላለማዊ ህይወት የተሰጠው ባይኖርም ዘላለማዊ ሕይወትን ለሸይኹ ይመኛሉ

" አበራሙዝ ሸሊላህ ሰንብቶኒ
አበራሙዝ ሸሊላህ ደውሞኒ "

እየከመሩ የሚያስቀምጡት ነገር ውጤቱ መራራ መሆኑን ባያውቁም እንዲህ በማለት ያንጎረጉራሉ

" አብሬት ጀፎረ ቲኮሬ
የጀነት ሸረት ይወሬ "

አብሬት መንደሩ ላይ የጀነት ምግብ ይበላል እነደማለት

ኢስቲጋሳ ይደረግባቸዋል በመንዙማ መልክ

"አጊስና ሰይዲ የአበል ኩመላ
ሚፍታሁ ሊልኸይሪ ሂጃቡ ሊልበላ "

አላህ ግን ከሱ ውጭ ያሉ ነገሮች በአጠቃላይ መድረስና መርዳት እንደማይችሉ በምሳሌ እንዲህ እያለ ያስረዳል

يأيها الناس ضرب مثل فاستمعوا له إن الذين تدعون من دون الله لن يخلقوا ذبابا ولو اجتمعوا له وإن يسلبهم الذباب شيئا لا يستنقذوه منه ضعف الطالب والمطلوب

الحج 73

እናንተ ሰዎች ሆይ ምሳሌ ተደርጎላችዋልና አዳምጡ እነዚያ ከአላህ ውጭ የምትጠሯቸው ነገሮች ዝንብ እንኳ መፍጠር አይችሉም ቢሰባሰቡም እንኳ (ተጋግዞ ለመፍጠር) (ከምግባቸው ላይ) ዝንብ አንዳች ነገር አንስቶባቸው ቢሄድ ማስጣል አይችሉም ፈላጊውም ተፈላጊውም ደካማ ተደረገ


የዚህ ከንቱ ልፋት መጨረሻው ምን ይሁን ? እውን እነሱ እንደሚሉት የአብሬት ሸይኽ በሕይወት ኑረው ጥሪውን ሰምተው ምላሽ ይሰጣሉ ወይስ የሉም?

መ) ያለምንም ጥርጥር በሕይወት የሉም የአካባቢው ተወላጅ ( ሙሪዱ) ሲሞቱ ባያይም አላህ ደግሞ ዘለዓለማዊ ሕይወት ለማንም አልሰጠምና የሉም ብለን እንደመድማለን ።

"ካንተ በፊት ለማንም ዘላለማዊ ሕይወት አልሰጠንም አንተ ብትሞት አነሱ ዘውታሪ ይመስሉሃልን? " አል አንቢያእ 34
አስከትሎም አንቀጽ 35 ላይ ሁሉም ነፍስ ሞት ቀማሽ መሆኗን ይናገራል ።
አይ መኖር የሉም ካሉበት ሆነው ምላሽ ይሰጣሉ የሚል ካለ አላህ እንዲህ ይላል

والذين تدعون من دونه ما يملكون من قطمير إن تدعوهم لا يسمعون دعاءكم ولو سمعوا مااستجاب لكم ويوم القيامة يكفرون بشرككم ولا ينبئك مثل خبير

فاطر 13-14

እነዚያ ከአላህ ውጭ የምትጠሯቸው ነገሮች የቴምር ከፈፍ ቢሆንም እነኳ አይቆጣጠሩም ፤ ብትጠሯቸው ጥሪያችሁ አይሰሙም ፤ እንደው ቢሰሙ እንኳ አይመልሱላችሁም ፤ በትንሳዔው ቀን ስታጋሩት በነበረው ነገር ይክዳሉ ፤ ይህን የመሰለ ዜና የሚነግርህ ማንም የለም

አላህ የአብሬት ሸይኽ እና መሰል የሚመለኩ አካላቶች ወደ ራሳቸው አምልኮ ተጣርተው ቢሆንም ባይሆንም በቂያማ ቀን ይጠይቃቸዋል ። ሆኖም
እነዚህ አካላቶች ተገዙኝ ያላሉ እንደሆነ ተከታዮች ያላቸው እጣ ፈንታ ይህ ነው አላህ እንደሚነግረን

" እነዚያ በአላህ ላይ ሲያጋሩ የነበሩ ቢያዩ ኖሮ ( በቂያማ ቀን የሚሆኑት ነገር ) ፦
የአላህ ቅጣት ባዩ ጊዜ ፣ ኃይል ( ስልጣን ) በአጠቃላይ የአላህ መሆኑን እና ለአላህ እጅግ የበረታ ቅጣት እንዳለው ባዩ ጊዜ ፤ አስከታዮች (በአላህና ላይ የሚጋሩት ) ከተከታዮቻቸው (ከአጋሪዎች) ሽርክ በጠሩ ጊዜ ፣ ቅጣትንም ባዩ ጊዜ መንገዶች (በአጋሪና በተጋሪው መዳረሻ) በተቋረጡ ጊዜ ፤ ተከታይ የነበሩ ሰዎች ይላሉ " ለኛም ወደ ዱንያ የመመለስ እድል ቢኖረን ኖሮ እነኚህ ከኛ እንደጠሩት እኛም ከነሱ እንጠራ ነበር ።" ልክ እንደዚሁ የከሰሩ ሲሆኑ ሥራቸው (አላህ) ያሳያቸዋል እነሱም ከእሳት የሚወጡ አይደሉም "
አል በቀራህ 165–167

ስናጠቃልል
*********

* እኔ የምሄድው ለኢባዳ እንጂ ምንም ፈልጌ አይደለም የሚል አይጠፋም

መ) የአላህ መልክተኛ " ኮርቻ ወደ ሦስት ቦታዎች እንጂ አይጫንም ወደ አላህ ቤት ፣ ወደ መስጂድ አቅሷ እኔ ወደ መስጂዴ (መዲና) "

እኛም ደግሞ ስንቅ ሰንቆ መኪና ነድቶ ወደ ቀብር ቢድዓ እና ሽርክ ለመስራት አይኬድም እንላለን ሀዲሱ መረጃ በማድረግ

* የሚያጋጥመንን በዝርዝር በማስቀመጥ እንደምንቆጭ ተቆጭተን እንኳ ዳግም የመመለስ እድል እንደሌለን አላህ አበክሮ ነግሮናልና የቂያማ ቀን ጸፀት የሚያከናንበን አንስራ

* አብዛኞቹ ባለ ማወቅ ይሰራሉ ብለን ባናከፍራቸውም እንኳ ተግባሩ የኩፍር ነውና ጥንቃቄ እናድርግ

* አሻራኪ ምንም ያህል መልካም የሚያስበው ስራ ቢኖ የተፀፀተ ሲሆን ጀሀነም ውስጥ ዘውታሪ ነው ።

በመጨረሻም
።።።።።።።።

አብሬት የሚተገበረው ሽርክ በአጭሩ ፎቶግራፉ ላይ የተመለከተው ይመስላል
ሁለት አድሪሀዎች የባልና የሚስት ሰዎች በዙርያቸው ይጠውፋሉ ፣ በግንባራቸው ይደፋሉ ፣ አፈሩን ይቅማሉ ፣ በጀመዓ ብዙ ረከዓ ይሰግዳሉ… ወዘተ ።
አላህ ትርፍ ከሌለው ስራ ይጠብቀን አሚን

Post a Comment

0 Comments